Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልሁለገቡ ከያኒ መስፍን ጌታቸው (1963-2013)

  ሁለገቡ ከያኒ መስፍን ጌታቸው (1963-2013)

  ቀን:

  በቅርብ ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥንና በኢቢኤስ ጣቢያዎች በተከታታይ የቀረቡት ‹‹ገመና›› እና ‹‹ዘመን›› የቴሌቪዥን ድራማዎች በደራሲነትና በአዘጋጅነት በተዋናይነት ገንኖ ታውቆበታል፡፡ ደራሲም፣ ተዋናይም፣ አዘጋጅም ሆኖ በጥበቡ ዓለም የዘለቀው መስፍን ጌታቸው ነው፡፡

  ቀደም ባሉት ዓመታት በፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር አማካይነት በሬዲዮ ይቀርብ በነበረውና በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በሚያጠነጥነው መሰናዶም ከያኒ መስፍን ‹‹የቀን ቅኝት›› በተሰኙ ሥራዎቹ በኅብረተሰቡ ዘንድ ታዋቂ ማኅበረሰቡን ዘና እያደረገ ስለቤተሰብ ዕቅድ፣ ኤችአይቪ ኤድስን በመሰሉ ጉዳዮችን በማንሳት እያዋዛ የሚያስተምረው ጥበባዊ ትሩፋቱ በበርካቶች ዘንድ ሞገስ እንዲያገኙ ማድረጉ ይወሳል፡፡

  በሲኒማውም ዓለም በተለይ በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ የሚታየው አካባቢያዊና ጎጣዊ ስሜትን የሚከላ ‹‹ዙምራ›› የተሰኘው ፊልሙም ተጠቃሽ ነው፡፡

  ከያኒ መስፍን በመድረክ ቴአትርም ከአውድማው አልተለየም አንዱ የሚጠቀስለት ሥራው በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ባህል አዳራሽ ለስድስት ወራት፣ እንዲሁም በተለያዩ ከተሞች ለመንፈቅ በኅብረተሰቡ የታየው ‹‹ሰቀቀን›› ነው፡፡

  ከአባቱ ከአቶ ጌታቸው ደምሴና ከእናቱ ከወ/ሮ ሎሚናት ገብረመስቀል፣ በ1963 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ሰንጋ ተራ አካባቢ የተወለደው ከያኒው መስፍን፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በአዲስ አበባ፣ የሁለተኛ ደረጃን በሐረር ከተማ ተከታትሏል፡፡ በባህልና ቱሪዝም ቢሮ የቴአትር ሥልጠና በመውሰድ ወደ ኪነ ጥበቡ ሙያ በመቀላቀልና ኢትዮ ብሥራት የቴአትር ቡድንን ከጓደኞቹ ጋር በማቋቋም የአካባቢውን የጥበብ ጥማት ለማርካት መቻሉን ገጸ ታሪኩ ያሳያል፡፡

  በ1987 ዓ.ም. ‹‹ሰቀቀን›› የተሰኘ ቴአትር ከቡድኑ ጋር ይዞ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ውጣ ውረዶችን አልፎ በዓመቱ በተለያዩ መድረኮች ለዕይታ አብቅቷል፡፡ በመቀጠልም በራስ ቴአትር ‹‹የደመና ጉዞ›› ሲያቀርብ፣ ከፊልሙ ዓለም ጋር የተዋወቀበት ‹‹ዙምራ›› በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለተመልካቾች አቅርቧል፡፡

  በሬዲዮ የቅዳሜ መዝናኛ ፕሮግራም በርካታ ድራማዎችን በጸሐፊነትና በተዋናይነት ያቀረበ ሲሆን፣ ‹‹የልደት ጧፍ›› የተሰኘው ተከታታይ ሥራው እጅግ ተወዳጅ አድርጎት ነበር፡፡ በፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር በኩል ካቀረባቸው ሥራዎቹ መካከልም ማለዳ፣ ስብራት እና እግረኛ ይገኙበታል፡፡ ከጥበባዊ ሥራዎቹ ባሻገር ሐሳቡን በጋዜጣና በመጽሔት ከማቅረብም አልተቆጠበም፡፡

  ባደረበት ድንገተኛ የኮቪድ-19 ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ፣ ሚያዝያ 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ከያኒ መስፍን፣ ባለትዳርና የሁለት ሴቶችና የአንድ ወንድ (የሦስት ልጆች) አባት ነበር፡፡

  ሥርዓተ ቀብሩም በመንበረ ጸባâት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሚያዝያ 18 ቀን ተፈጽሟል፡፡  

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...