Wednesday, November 30, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊዋጋ እያስከፈለ ያለው መዘናጋት

  ዋጋ እያስከፈለ ያለው መዘናጋት

  ቀን:

  ኮቪድ-19 ከ3,600 በላይ ሰዎችን ለኅልፈት ዳርጓል

  የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል የወጣውን አገራዊ መመርያ በሚፈለገው መጠን ባለመተግበራቸው ስድስት ሺሕ በላይ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከቃል ማስጠንቀቂያ ጀምሮ ተቋማቱን እስከ ማሸግ የሚደርስ ዕርምጃ እንደተወሰደባቸው ጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

  በሚኒስቴሩ የጤናና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በሥሩ ከሚገኙ የፌደራል፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር ጤና መዋቅሮች ጋር ባዘጋጀው የምክክር መድረክ፣ የኮቪድ-19 መካለከልና ቁጥጥር በተመለከተ በጋራ ያከናወኗቸውን ተግባራት በተመለከተ ሚያዝያ 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ምክክር አድርገዋል፡፡

  በመድረኩ ሪፖርታቸውን ያቀረቡ አመራሮችና ተወካዮች እንዳስታወቁት፣ በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኮቪድ-19 ከመከላከልና ከመቆጣጠር ረገድ 29,852 ጊዜ ቁጥጥር ተደርጎ፣ 8,000 በላይ የሆኑት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የወጣውን መመርያ 30 መሠረት አድርገው ሲሠሩ፣ ከ6,000 በላይ የሚሆኑት ተቋማት ግን መመርያው በሚፈለገው መጠን አልተገበሩም፡፡ በነዚህ መመርያውን ባልተገበሩ ከቃል ማስጠንቀቂያ ጀምሮ ተቋማቱን እስከ ማሸግ የሚደርስ ዕርምጃ እንደተወሰደባቸው ገልጸዋል፡፡

  በምክክር መድረኩ የተገኙት የጤናና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳይሬክተር / ኤደን ወርቅነህ፣ በተለይ መዋቅሮች ያላቸውን አቅም ሁሉ ተጠቅመው የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከል ረገድ ለቫይረሱ የሚያጋልጡና የሥርጭት መጠኑን ሊጨምሩ የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ አተኩረው፣ ክትትልና ቁጥጥሩን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

  ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማትንም እያካተቱ እንዲሁም ከሌሎች አቻ ሴክተሮች ጋር ያለውን የተቀናጀ አሠራርም ማጠናከር እንዳለባቸውም ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡

  በሌላ በኩል፣ የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ክርስቲያኖች ዓመታዊውን የጸሎተ ሐሙስ በዓልን ባከበሩበት ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. አጋጣሚ፣ የኮቪድ-19 ቫይረስ ሥርጭት አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ኅብረተሰቡ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርግ፣ ሰዎች በሚበዙበት፣ በቂ አየር ዝውውር በሌለበት፣ ርቀትን መጠበቅ በማይቻልበት ቦታ አስገዳጅ ካልሆነ በቀር እንዳይገኝ የተማጽኖ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

  ኢንስቲትዩቱ በአሁናዊ ሪፖርቱ፣ እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በአጠቃላይ 2,568,346 ሰዎች የኮቪድ-19 ላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው፣ 255,288 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው፣ ከእነዚህም መካከል በአሁኑ ወቅት የኮቪድ ቫይረስ ያለባቸው ግለሰቦች ቁጥር 55,223 እንደሆነ አስታውቋል፡፡

  ከዚህም ሌላ 196,424 ሰዎች ከበሽታው ሲያገግሙ፣ 3,639 ሰዎች ደግሞ ለኅልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል፡፡ እስከ ሚያዝያ 20 ድረስ 940 ሰዎች በኮቪድ-19 ቫይረስ ተይዘው በጽኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡

  እያንዳንዱ ግለሰብ፣ ቤተሰብ፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የጤና ባለሙያዎች፣ መምህራንና ሌሎችም  ባለድርሻ አካላት ተደጋግሞ የሚገለጹትን የመከላከያ መንገዶችን እንዲተገብሩም አሳስቧል፡፡

  ‹‹ከኮቪድ ተጠበቁ!››

  እርስዎ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን በአግባቡ እየተገበሩ ነው?

  • ማስክ ሳያደርጉ በፍፁም አይንቀሳቀሱ
  • የእጅዎን ንፅህና በአግባቡ ይጠብቁ
  • በቂ የአየር ዝውውር በሌለበትና ሰው በተሰበሰበበት ቦታ አይገኙ

  ይኼንን በመተግበር ራስዎንና ቤተሰብዎን ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ይታደጉ።

  አራቱ ‹‹›› ሕጎች

  • መራራቅ፡- አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
  • መታጠብእጅን በተደጋጋሚ በውኃና በሳሙና መታጠብ፣
  • መቆየት፡- አስገዳጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት፣
  • መሸፈን፡- ከቤታችን ወጥተን ስንንቀሳቀስ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም፡፡
  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...