Thursday, September 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየቀድሞው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር በድንገት ሕይወታቸው አለፈ

  የቀድሞው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር በድንገት ሕይወታቸው አለፈ

  ቀን:

  በቅርቡ ከኃላፊነታቸው የተነሱት የቀድሞው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ፣ በድንገት  ማክስኞ ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ሕይወታቸው አለፈ፡፡

  ኮሚሽነሩ ማክሰኞ ማለዳ የሕመም ስሜት ተሰማኝ ብለው ወደ ሆስፒታል ሄደው ሕክምና ላይ እንዳሉ ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል፡፡

  በባህር ዳር ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል ለኮሚሽነር አበረ ሕክምና የሰጡ የውስጥ ደዌ ሕክምና ስፔሻሊስትን አናግሬያለሁ ያለ አንድ የመንግሥት ሚዲያ፣ የኮሚሽነሩ ድንገተኛ ሕልፈት በልብ ጡንቻ መጎዳት ምክንያት መሆኑን ዘግቧል፡፡

  የጤናቸው ሁኔታ ከበድ ያለ ስለነበር በፍጥነት ወደ ድንገተኛ ሕክምና መስጫ ክፍል እንዲገቡ መደረጉን፣ ለኮሚሽነሩ ሕልፈተ ሕይወት ዋናው ምክንያት ልባቸው ቢሆንም፣ በወቅቱ ሆስፒታል ሲደርሱ የስኳር መጠናቸው ከ400 በላይ ደርሶ እንደነበር በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

  ከሳምንት በፊት ከሥልጣናቸው የተነሱትና ለሁለት ዓመታት ያህል በኃላፊነት ሲሠሩ የቆዩት ኮሚሽነር አበረ፣ የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር በነበሩት ተኮላ አይፎክሩ መተካታቸው አይዘነጋም፡፡

  አዲሱ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ተኮላ ከሦስት ዓመታት በፊት በፌደራል ፖሊስ ውስጥ በኃላፊነት ከመመደባቸው አስቀድሞ፣ በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግለዋል።

  ኮሚሽነር አበረ ከሥልጣናቸው እንዲነሱ ካደረጓቸው ምክንያቶች ውስጥ በተለይም በቅርቡ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶችና በተፈጸሙ ጥቃቶች፣ የበርካታ ሰዎች ሕይወት በመጥፋቱና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተጠቃሽ እንደሆነ ከክልሉ የተገኙ ምንጮች ያመላክታሉ፡፡

  ኮሚሽነር አበረ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውንና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በስዊድን የተከታተሉ ሲሆን፣ ‹‹የሕግ የበላይነት ለአገራዊ ልማት›› በሚል ርዕስ ያሳተሙትን መጽሐፍ በታኅሳስ ወር አስመርቀዋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img