Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊከልክ በላይ የሚጭኑ አሽከርካሪዎች እስከ 1,500 ብር ቅጣት እንደሚቀጡ ተገለጸ

  ከልክ በላይ የሚጭኑ አሽከርካሪዎች እስከ 1,500 ብር ቅጣት እንደሚቀጡ ተገለጸ

  ቀን:

  የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል በሚደረገው ርብርብ ከልክ በላይ የሚጭኑ አሽከርካሪዎች ከ500 እስከ 1,500 ብር ቅጣት እንደሚቀጡ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

  ቢሮው ይህንን የገለጸው ማክሰኞ ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሆን፣ በወቅቱም በፍጥነት እየተሠራጨ የመጣውን የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል የሚረዳ መመርያ ወጥቶ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ስጦታው አካለ (ኢንጂነር) እንደገለጹት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ላይ ከፍተኛ የሕዝብ መተፋፈግ በመኖሩና የተሽከርካሪዎች ቁጥር ከነዋሪዎች ጋር ባለመመጣጠናቸው ምክንያት የኮሮና ወረርሽኝ በስፋት ሊዛመት ችሏል፡፡

  መመርያው በከተማዋ በሚገኙ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን የገለጹት ኃላፊው፣ ይህም ወረርሽኙን ለመከላከል ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

  ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲዛመት ምክንያት ከሆኑ ነገሮች መካከል የትራንስፖርት ተጠቃሚው ዘንድ ማስክ በተገቢው መንገድ አለማድረግና ሳይኒታይዘር አለመጠቀም መሆኑን፣ ይህንን ችግር ለመፍታት ትኩረት በመስጠት እየተሠራ  እንደሚገኝ አቶ ስጦታው (ኢንጂነር) ተናግረዋል፡፡

  የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ያልሆኑ ተሽከርካሪዎች ተሳፋሪዎች ቁጥር ወይም የመጫን አቅም፣ በተሽከርካሪው ወንበር ልክ እንዲሆን መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

  ማኅበረሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ እንግልት እንዳይደርስበት ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶችን በየቦታው በማሰማራት አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡

  በሚኒባስ ታክሲ የተፈቀደው የተሳፋሪ ቁጥር ወይም የመጫን አቅም በተሽከርካሪ ወንበር ልክ ሲሆን፣ ለሃይገር ተሽከርካሪዎች ግን በወንበር ልክ፣ እንዲሁም ተጨማሪ አምስት ሰዎች ርቀታቸውን በመጠበቅ ቆመው እንዲሄዱ የሚፈቅድ መሆኑን ተገልጿል፡፡

  ለአንበሳ የከተማ አውቶቡስ፣ ለሸገር የብዙኃን ትራንስፖርትና ለመንግሥት ሠራተኞች ሰርቪስ አውቶቡሶች የተፈቀደው የተሳፋሪዎች ቁጥር ወይም የመጫን አቅም፣ በተሸከርካሪ ወንበር ልክና ቆመው እንደሄዱ የተፈቀደላቸው 50 በመቶ ያህል ነው፡፡

  የባለሦስት እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪዎች የተሳፋሪ የመጫን አቅም ልክ ከእነ ሾፌሩ ሦስት ሲሆን፣ ባለአራት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) የመጫን አቅም በወንበር ልክ እንደሆነና ሌሎች የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ወይም የሜትር ታክሲዎች የመጫን አቅም በወንበር ልክ መሆኑ ተብራርቷል፡፡

  የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችም ታሪፍ፣ ከዚህ በፊት በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት በተደረገው ጭማሪ መሠረት የሚቀጥል እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

  ከተፈቀደው ተሳፋሪ በላይ ለሚጭኑ ሚኒባሶች 1,000 ብር፣ ለሃይገር ወይም ለቅጥቅጥ 1,500 ብር፣ ለአውቶቡስ 1,500 ብር፣ ታክሲ (ላዳ፣ የሜትር ታክሲ) 500 ብር፣ ባለሦስት ወይም ባለአራት እግር ባጃጅ ወይም ሞተር ሳይክል 500 ብር ቅጣት እንደሚቀጡ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

  ከታሪፍ በላይ ለሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችም 1,500 ብር የሚቀጡ ሲሆን፣ አሽከርካሪም ሆነ ረዳት ማስክ ሳያደርጉ ከተገኙ 100 ብር፣ ማስክ ያላደረገ ተሳፋሪ በሚጭኑበት ወቅት 500 ብር እንደሚቀጡ ተጠቁሟል፡፡

  የከባድ ተሽከርካሪ የእንቅስቃሴ ገደብ በተመለከተ ከተፈቀደላቸው ሰዓት ውጪ ሲያሽከረክሩ የተያዙ አሽከርካሪዎች 500 ብር እንደሚቀጡ፣ አቶ ስጦታው (ኢንጂነር) አስታውሰዋል፡፡

  ከዚህ ቀደም በትራንስፖርት አገልግሎት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በከፍተኛ ሁኔታ እንዳይሠራጭ፣ ለማድረግ መመርያ ወጥቶ ተግባራዊ ለማድረግ ቢሞከርም ችግር ማጋጠሙ ይታወሳል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...