Tuesday, November 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትኢትዮጵያ የዞን አምስት አገሮችን በፕሬዚዳንትነት እንድትመራ ተመረጠች

  ኢትዮጵያ የዞን አምስት አገሮችን በፕሬዚዳንትነት እንድትመራ ተመረጠች

  ቀን:

  ኦሊምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

  የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር ዞን አምስት (አኖካ) በካምፓላ ዑጋንዳ ባደረገው ጉባዔ፣ ኢትዮጵያን የአኖካ-ዞን አምስት አገሮች ፕሬዚዳንት እንድትሆን መርጧል፡፡

  የአፍሪካ ዞን አምስት ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር በውስጡ 11 አባል አገሮችን ያስተዳድራል፡፡ የአኖካ የዞን አምስት አባል አገሮች ባለፈው ቅዳሜ ሚያዝያ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ካምፓላ ዑጋንዳ ላይ ባደረጉት ጠቅላላ ጉባዔ፣ በዕጩነት ከግብፅ ጋር የቀረበችው ኢትዮጵያ የፕሬዚዳንትነቱን ኃላፊነት ያገኘችው የሰባት አገሮችን ድምፅ አግኝታ ነው፡፡

  የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምርጫውን አስመልክቶ ባለፈው ሰኞ ሚያዝያ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ሰጥቷል፡፡

  በምርጫው መሠረት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር) የአኖካ ዞን አምስት ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሆነው የሚያገለግሉ ይሆናል፡፡

  ብቸኛዋ ኢትዮጵያዊት የኢንተርናሸናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ አባል፣ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖክ)፣ እንዲሁም የአኅጉራዊ አኖካ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማይም በቀጥታ ተመራጭ ሆነዋል፡፡

  አኖካ ከአራት አሠርታት በፊት ሲቋቋም የመጀመርያው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ያገለገሉት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንትና የስፖርት ኮሚሽነር ፀጋው አየለ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

  በሌላ በኩል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሒሩት ካሳው (ዶ/ር) እና የስፖርት ኮሚሸነር አቶ ኤልያስ ሽኩር ማክሰኞ ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ከአትሌቶች ምርጫና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር  በተገናኘ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች ጋር በሸራተን አዲስ ውይይት አድርገዋል፡፡

  በውይይቱ መሠረት ሁለቱ ተቋማት በቀጣይ በሚካሄደው ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በጋራ ለመሥራትም ተስማምተዋል፡፡

  ስምምነቱ ሚኒስትሯና ኮሚሽነሩ በሁለቱ ተቋማት መካከል የተከሰተውን አለመግባባት በመፍታት ተቋማቱ ለስፖርት ቅድሚያ ሰጥተው መሥራት እንዳለባቸው በሰጡት አቅጣጫ መሠረት የተፈጸመ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...