ቼኮስሎቫኪያ ገበረች ራሷን ተላጭታ
ነምሳ ጧት ገበረች ራሷን ተላጭታ
ፖሎኝም ገበረች ራሷን ተላጭታ
ኢጣሊያ ገበረች በጧት እጇን ሰጥታ
ሁንጋሪያ ዐበረች እባርነት ገብታ
ሩማንያ ዐበረች እባርነት ገብታ
ቡልጋርያም ዐበረች እባርነት ገብታ
ሆላንድ ገበረች ራሷን ተላጭታ
ዳንማርክ ገበረች ራሷን ተላጭታ
ኖርቬዥም ገበረች ራሷን ተላጭታ
ዩጎዝላቭ ገበረች ራሷን ተላጭታ
ግሪክም ገበረች ራሷን ተላጭታ
ሉክሳምቡር ገበረች ራሷን ተላጭታ
ፈረንሳ ገበረች ራሷን ተላጭታ
እንቢ! አለች ኢትዮጵያ ቈንዳላ ተሠርታ።
ታረቀኝ፡ ተፈሪ
(የክብር ዘበኛ ፲ አለቃ ሰቈጤ)
ኻርቱም መስከረም ፲፯ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ.ም.