የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፣ ኢትዮጵያ በፋሺስት ጣሊያን ወራሪ ሠራዊት ላይ ድል የተቀዳጀችበት 80ኛ ዓመት አስመልክቶ የተናገሩት፡፡ ፕሬዚዳንቱ በጋዜጣዊ መግለጫቸው፣ ኢትዮጵያ ከስምንት አሠርታት በፊት ከገጠማት የውጪ ወረራ የሚመሳሰል ችግር እየገጠማት መሆኑን አውስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በድል አድራጊነት ለሕዝቧ ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ሕዝብና በቅኝ አገዛዝ ሥር ለነበሩ ሁሉ ተስፋና ኩራት ሆና መቀጠሏንም አስምረውበታል፡፡