Saturday, July 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊጎዳና ተዳዳሪ ሕፃናት አገልግሎት የሚያገኙበት ማዕከል በ400 ሚሊዮን ብር ሊገነባ ነው

ጎዳና ተዳዳሪ ሕፃናት አገልግሎት የሚያገኙበት ማዕከል በ400 ሚሊዮን ብር ሊገነባ ነው

ቀን:

ከኮሪያ ፍሬንድስ ኢትዮጵያ የዕርዳታ ድርጅት በተገኘ 400 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለተቸገሩ ወገኖች በተለይም ለጎዳና ተዳዳሪ ሕፃናት የሚያገለግል በጎ አድራጎት ማዕከል ለመገንባት ዝግጅት መጨረሱን ዘ ጉድ ሰመሪታት ትሬኒንግ ሴንተር የበጎ አድራጎት ድርጅት አስታወቀ፡፡

የግንባታውን ወጪ ሙሉ ለሙሉ የሚሸፍነው የኮሪያ ፍሬንድስ ኢትዮጵያ የዕርዳታ ድርጅት ሲሆን፣ ግንባታውም ተጠናቆ ሲያልቅ የጎዳና ተዳዳሪዎችና በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ልጆች አገልግሎት የሚያገኙበት ይሆናል ተብሏል፡፡

የዘ ጉድ ሰመሪታት ትሬኒንግ ሴንተር የበጎ አድራጎት ድርጅት መሥራች ወ/ሮ  ኤልሳቤት አበባ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በችግር ውስጥ የሚገኙ ልጆች የተሟላ አገልግሎት አግኝተው እንዲኖሩ ለማድረግና ለቁም ነገር ለማብቃት ፕሮጀክታቸው ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡

ግንባታው ተጠናቆ እስኪያልቅ ስድስት ወር እንደሚፈጅ የሚናገሩት ወ/ሮ ኤልሳቤት፣ ተጠናቆ ሲያልቅ በአካባቢው ላይ በሚገኘው ወረዳ አማካይነት የተቸገሩ ሕፃናት ተለይተው ወደ ማዕከሉ እንዲገቡ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡

በተለያየ አካባቢ ላይ በሚነሳ የፀጥታ ችግር ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው ወደ ጎዳና ሕይወት የሚገቡ ሕፃናት ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት መጨመሩንና ለችግሩ መፍትሔ ለመስጠት ድርጅቱ ከመንግሥት ጋር በመሆን ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝም አክለዋል፡፡

ድርጅቱ ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በከፍተኛ ሁኔታ የተቸገሩ ሰዎችን የማንሳት ሥራ የሚሠራ መሆኑንም ወ/ሮ ኤልሳቤት ጠቁመዋል፡፡

በአገሪቷ የሚገኙ ባሀብቶችና የሚመለከታቸው አካላት የተቸገሩ ወገኖችን ችግር እንደራሳቸው በማየትና ድጋፍ በማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በችግር ውስጥ የሚገኙ ልጆች ያሉበትን ሁኔታ በማጥናት አኗኗራቸውን ካረጋገጠ በኋላ ወደ በጎ አድራጎት ማዕከሉ እንዲገቡ የሚደረግ መሆኑን የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3 ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገነሞ ያችሶ ተናግረዋል፡፡

በወረዳው ወደ ጎዳና የወጡ ሕፃናት ልጆች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑንና ካሉበት ችግር ለመታደግ ሰፊ ሥራ እንደሚጠይቅም ሥራ አስፈጻሚው አስረድተዋል፡፡

የበጎ አድራጎት ድርጅቱም የሚፈልገውን ያህል ሕፃናት እንዲዘጋጅለት አቅጣጫ ባስቀመጠው መሠረት እንደሚከናወንም አቶ ገነሞ ገልጸዋል፡፡

ዘ ጉድ ሰመሪታት ትሬንኒግ ሴንተር የበጎ አድራጎት ድርጅት ከዚህ በፊት 3082 ልጆችን በልብስ ስፌት፣ በምግብ ዝግጅትና በፀጉር ሥራ አሠልጥኖ ሥራ እንዲይዙ ማድረጉን የግንባታ ፕሮጀክቱ ይፋ በተደረገበት ወቅት ተገልጿል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ የሚከናወነው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በዘ ጉድ ሰመሪታን ትሬዲንግ ሴንተር በጎ አድራጎት ድርጅት ግቢ ውስጥ በ1500 ካሬ ሜትር ስፍራ ላይ መሆኑም ተነግሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የሰብዓዊ መብት ጉዳይና የመንግሥት አቋም

ሰኔ ወር አጋማሽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የሰብዓዊ...

ከሰሜኑ ጦርነት አገግሞ በሁለት እግሩ ለመቆምና ወደ ባንክነት ለመሸጋገር የተለመው ደደቢት ማክሮ ፋይናንስ

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ በቀዳሚነት ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ ደደቢት...