Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትመፍትሔ ያጣው የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች የገንዘብ ቀውስ

መፍትሔ ያጣው የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች የገንዘብ ቀውስ

ቀን:

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተጀምሮ በጅማ፣ በባህር ዳርና በድሬዳዋ ከተሞች ሲካሄድ ቆይቶ፣ አሁን ደግሞ በሐዋሳ ከተማ የመጨረሻውን መርሐ ግብር እያከናወነ ይገኛል፡፡ ይሁንና አሁን ላይ ቡድኖች ለሻምፒዮንነት ሳይሆን በሚቀጥለው የውድድር ዓመት ወደ ታችኛው ሊግ ላለመውረድ ከሚያደርጉት ትንቅንቅ ጎን ለጎን በፋይናንስ ችግር የሚታመሱ ክለቦች መኖራቸው ግልጽ ሆኗል፡፡

ሊጉ ሲጀመር ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ በማዘዋወር በከፍተኛ ደረጃ መንቀሳቀሱ ሲነገርለት የነበረው የሀድያ ሆሳዕና እግር ኳስ ክለብ የፋይናንስ ችግሩ ካጋጠማቸው ክለቦች የመጀመሪያው ሆኖ ለአንድ ጨዋታ የሚያስፈልጉ ተጫዋቾችን እንኳ ማሠለፍ ተስኖት በሐዋሳ ከተማ  ከሐዋሳ ከነማ ጋር ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ በዘጠኝ ተጫዋቾች ሲጫወት ታይቷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ብዙዎቹ የክለቡ ተጫዋቾች ቃል የተገባላቸው የፊርማና ወርኃዊ ክፍያ ስላልተከፈላቸው ወደ ሐዋሳ ለመጓዝ ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ነው ተብሏል፡፡

ችግሩ በሀድያ ሆሳዕና እግር ኳስ ክለብ ላይ ጎልቶ ይውጣ እንጂ፣ በቅርቡ ከክለቡ የወጣው መረጃ እንዳመለከተው ከሆነ፣ የሰበታ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች በተመሳሳይ ችግር ከሆቴል ለቀው መውጣታቸው ተሰምቷል፡፡ ቅርበት ያላቸው የክለቡ ምንጮች የሰበታ ተጫዋቾች ለሐዋሳው ጨዋታ ወደ ሥፍራው ያቀኑት ተጫዋቾቹ እንዲከፈላቸው የጠየቁት ክፍያ ከተፈጸመላቸው በኋላ ስለመሆኑ ጭምር ይናገራሉ፡፡

በውድድር ዓመቱ መጀመሪያ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ከአዳማ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ያስፈረመው ሀድያ ሆሳዕና በወቅቱ ‹‹ሀድያ ሆሳዕና አዳማ ከነማን ገዛው›› የሚል ትችትና ወቀሳ ሲያስተናግድ የነበረ ክለብ ነው፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከተፎካካሪዎቹ ተርታ ሆኖ መዝለቅ የቻለው ሀድያ ሆሳዕና፣ አሁን ለአንድ ጨዋታ የሚያስልጉ 11 ተጫዋቾችን እንኳ ወደ ሜዳ አስገብቶ መርሐ ግብር ማሟላት አለመቻሉ የክለቡን አመራሮች ክፉኛ እያስወቀሰ ይገኛል፡፡

የሀድያ ሆሳዕና ዋና አሠልጣኝ አሸናፊ በቀለ በክፍያ ምክንያት ወደ ሐዋሳ ባልተጓዙ ተጫዋቾች ምትክ በቅጣት ላይ የሚገኙ ተጫዋቾችን እንዲያስገቡ ከክለቡ ደጋፊዎችና አንዳንድ አመራሮች ግፊት ቢደረግባቸውም፣ ‹‹ለገንዘብ ብዬ በሙያዬ ወንጀል አልሠራም፣ በዚህ መልኩ ተገድጄ የምሠራው ሥራ ከባድ ነው፣›› በማለታቸው ምክንያት በሐዋሳ ቡድኑን እንዳይመሩ መደረጋቸው ጭምር እየተነገረ ነው፡፡

በጎደሎ ተጫዋቾች ሐዋሳ ከነማን የገጠመው ሀድያ ሆሳዕና 3ለ0 ተሸንፏል፡፡ በክለቡ ውስጥ እየታየ ባለው የገንዘብ እጥረት ምክንያት፣ የክለቡ አመራሮች አሠልጣኙ ሕገወጥ ተጫዋቾችን ወደ ሜዳ እንዲያስገቡ የተጠየቁበት አጋጣሚ ምናልባትም ሊጉን በበላይነት የሚያስተዳድረው ሊግ ካምፓኒ ቀጣዮቹ ጨዋታዎች የሚደረጉት ላለመውረድ በመሆኑ የተለየ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የሚያስገድዱት እንደሚሆን ጭምር የሚናገሩ አልጠፉም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...