Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየገዥው ፓርቲ ካድሬዎች እንደተቆጣጠሩት ቅሬታ በቀረበበት የሶማሌ ክልል የመራጮችን ምዝገባ የሚያጣራ ቡድን...

የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች እንደተቆጣጠሩት ቅሬታ በቀረበበት የሶማሌ ክልል የመራጮችን ምዝገባ የሚያጣራ ቡድን ሊላክ ነው

ቀን:

የምርጫ ምዝገባ ሒደቱ በገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ቁጥጥር ውስጥ መግባቱና የምርጫ ካርዶች ከምርጫ ጣቢያ ውጪ ሲታደል እንደነበር በማስረጃ የተደገፈ ቅሬታ የቀረበበት የሶማሌ ክልል፣ የምመራጮች ምዝገባ ሒደት በከፊል ታግዶ አጣሪ ቡድን ወደ ሥፍራው እንደሚሰማራ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰሞኑን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባ ሒደት ላይ ከፍተኛ ቅሬታዎች በማስረጃ ተደግፈው መቅረባቸውን፣ ቦርዱ የቀረበውን ማስረጃ መርምሮ የተባሉት ብልሹ አሠራሮች ተፈጸመው ሊሆን እንደሚችል ግንዛቤ መውሰዱንና ማጣራን ለመጀመር የሚያስችል እንደሆነ አስታውቋል።

በሶማሌ ክልል የምርጫ ምዝገባ ሒደት ላይ ተፈጥሯል የተባለው ችግር በምርጫ ሒደቱ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ የሚፈጥር መሆኑን ያስታወቀው ምርጫ ቦርድ፣ አቤቱታ በቀረበባቸው ሰባት የምርጫ ክልሎች ላይ የሚካሄደው የመራጮች ምዝገባ በጊዜያዊነት አንዲቆም መወሰኑን ገልጿል። 

በክልሉ የምርጫ ሒደት አፈጻጸም ላይ የተለያዩ ፓርቲዎች በተናጠልና በጋራ ሆነው በተለያየ ጊዜ ያቀረቧቸው አቤቱታዎች ያተኮሩባቸው አንኳር ጉዳዮችን የዘረዘረው ምርጫ ቦርድ፣ የክልሉ የመራጮች ምዝገባ ሒደት በገዥው ፓርቲ ዝቅተኛ እርከን ባሉ ሠራተኞች ከፍተኛ ጣልቃ ገብነት እንደሚፈጸም፣ በዚህም ምክንያት የመራጮች ምዝገባ ከምርጫ ቦርድ ቁጥጥር ሥር አለመሆኑ ይገኝበታል ብሏል። 

የመራጮች ምዝገባ ካርድ የማይገባቸው ሰዎች እጅ መግባቱ፣ ከምርጫ ጣቢያ ውጪ ካርዶች ሲታደሉ እንደነበርያልተሞሉ የመራጮች ምዝገባ ካርዶች ለዝቅተኛው መንግሥት እርከን (ቀበሌና ወረዳ ሠራተኞች) እና ዕጩዎች መሰጠቱ፣ እንዲሁም የምርጫ አስፈጻሚዎች ከመንግሥት አስተዳደር እርከን ሠራተኞችና ዕጩዎች ጋር በዝምድናና በተለያዩ መንገዶች የተያያዙ መሆናቸውን የሚገልጽ ቅሬታና በዚህም የገለልተኝነት ጥያቄ መነሳቱን አስታውቋል።

የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ዜጎች እንዳይመዘገቡ ክልከላ እየደተረገባቸው እንደሆነ፣ የመራጮች ካርድ ከወሰዱ ነዋሪዎች እጅ ካርዱ ተመልሶ እየተሰበሰበ መሆኑን፣ እንዲሁም የምርጫ ሳጥን ‹‹ብሉ ቦክስ›› ምርጫ ጣቢያዎች ሲደርስ በተገቢው ሁኔታ ያልታሸገ መሆኑ፣ በዚህም ሳቢያ ተከፍቶ ሊሆን እንደሚችል ቅሬታ መቅረቡን ቦርዱ አስታውቋል።

የተጠቀሱት አቤቱታዎች በጽሑፍ በዝርዝር መቅረቃቸውንና አቤቱታውን ሊደግፉ ይችላሉ የተባሉ የፎቶ፣ የቪዲዮና ሌሎች ማስረጃዎች መቅረባቸውንም አመልክቷል።

አቤቱታዎቹን መሠረት በማድረግ ቦርዱ በክልሉ ሰባት የምርጫ ክልሎች ላይ የሚካሄደው የመራጮች ምዝገባ እንዲታገድ የወሰነ ሲሆን፣ በሰባቱ የምርጫ ክልሎች ላይ ያለውን የመራጮች ምዝገባ ሒደት የሚያጣራ ቡድን አዋቅሮ እንደሚልክም ገልጿል።

አቤቱታ ያቀረቡ የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ የቦርዱ ሠራተኞችና ገለልተኛ ባለሙያዎች የማጣራት ሒደቱን እንዴት ሊያከናውኑ እንደሚገባ የሚመራ የቴክኒክ ዝርዝር መመርያ አዘጋጅቶ ወደ ማጣራት ተግባር የሚገባ መሆኑንም ቦርዱ አስታውቋል። 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...