Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሰብዓዊነት ካስማ

የሰብዓዊነት ካስማ

ቀን:

በዚህ ዘመን ዓለምን ሥጋት ላይ የጣለውና የሰውን ሕይወት እየቀጠፈ ያለው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ዓይነት አገሮች ደግሞ ከኮሮና ወረርሽኝ በተጨማሪ የሰላም ማጣት ምክንያት በርካቶች እንደ ቅጠል እየረገፉ ይገኛሉ፡፡

በቁጥር እንኳን ቢሰላ ከቫይረሱ ይልቅ በተለያዩ ግጭቶች የሞቱ ንፁኃን ቁጥር ከፍ እንደሚል ይታወቃል፡፡ በዚህም ብዙ የዓለምና አገር አቀፍ ግብረ ሠናይ ድርጅቶች፣ ግለሰቦችና መንግሥት በተለያዩ አካባቢዎች በተነሱ አስከፊ ተግባራት ምክንያት ከየቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በሞት፣ በድርቅ፣ በጎርፍና በመሳሰሉ አደጋዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎችን ከሚያደርጉ ማኅበሮች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ማኅበሩ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሰጠውን አገልግሎት በተመለከተ ሚያዝያ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በተከበረው የቀይ መስቀል ቀይ ጨረቃ ቀን አጋጣሚ ሪፖርት አቅርቧል፡፡ ማኅበሩ በተወሳሰቡ ቀውሶች ሳቢያ ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጡ በአምስት ክልሎች የሚገኙ ወገኖችን ለመደገፍ ባደረገው ንቅናቄ የተለያዩ ተግባራትን ፈጽሟል፡፡

ከተደረጉት መጠነ ሰፊ ክንውኖች መካከል 46 ሚሊዮን ሊትር የመጠጥ ውኃ አቅርቦት፣ ከ26,170 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የሕክምና፣ የአንቡላንስና የሥነ ልቦና ድጋፍ፣ ከ1,200 በላይ ነፍሰጡርና ሚያጠቡ እናቶች፣ እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት አልሚ ምግቦች ድጋፍ ይገኙበታል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ከ65,400 በላይ ለሆኑ ሰዎች የተለያዩ ምግብ ነክ ቁሳቁሶችን፣ ከ70,300 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ደግሞ የመጠለያ አገልግሎት ድጋፍ ማድረጉን ማኅበሩ ገልጿል፡፡ ማኅበሩ የመጀመርያ ዕርዳታና አምቡላንስ አገልግሎት ለሚፈልጉ ለ230,000 ተጎጂዎች ዕርዳታ መስጠቱን አውስቷል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች በተነሱ ግጭቶች 63 የማኅበሩ አምቡላንሶች በቃጠሎ፣ በጉዳትና በስርቆት ምክንያት መጥፋታቸውን ሳይገልጽ አላለፈም፡፡

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ኮሚቴ በጋራ በመተባበር፣ በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ የነበረው የውኃ አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ፣ 333,000 ሰዎችን ተጠቃሚ ያደረገ 50 ሚሊዮን ሊትር የመጠጥ ውኃ ድጋፍ ተሰጥቷል፡፡

በኑሮ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች 772,239 ሰዎችን ተጠቃሚ ያደረገ መድኃኒት በማኅበሩ መድኃኒት ቤቶች አማካይነት አቅርቧል፡፡

አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት ኅብረተሰቡን አደጋ ካለባቸው አካባቢዎች በማንሳት የተጎጂ ቁጥር መቀነስ የተቻለ ሲሆን፣ 600 ሰዎችን ከተለያዩ አደጋዎች ቀድመው ራሳቸውን እንዲከላከሉ አስችሏል፡፡

በሌላ በኩልም ማኅበሩ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል 1.8 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ተደራሽ ያደረገ የተለያዩ መከላከል ሥራዎችን መሥራቱን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሰብዓዊ ድጋፎችን ጨምሮ ለተለያዩ ልማት ሥራዎች ከ443 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉንም አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት ቶፊቅ አብዱላሂ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ሲታይ ዓመቱ እጅግ የተወሳሰቡ ችግሮችና ዘርፈ ብዙ የሰብዓዊ ተግዳሮቶች ያለፉበትና አሁንም በዚሁ ሁኔታዎች ውስጥ እየታለፈ ነው፡፡

የኮሮና ወረርሽኝ፣ ጎርፍ፣ የአንበጣ መንጋ እንዲሁም በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶች በርካቶችን ለሞት፣ ለአካል ጉዳት፣ ለንብረት ውድመቶችና መፈናቀል እንደዳረጋቸው ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል፡፡

ማኅበሩ በእነዚህ የተወሳሰቡ ቀውሶች ሳቢያ ችግሮች የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሠራተኞች፣ በጎ ፈቃደኞችን በትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝና የደቡብ ክልሎች ማሰማራቱን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ ግጭቶች በተንሰራፉ ቁጥር የዕርዳታ ፈላጊው ቁጥር በዚያው መጠን እየጨመረና መጨረሻ ላይ ከአቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን ምክትል ፕሬዚዳንቱ አልሸሸጉም፡፡

የቀይ መስቀልና የቀይ ጨረቃ እንቅስቃሴ በ192 አገሮችና ከ80 ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኞችና ሠራተኞች የሚሰማሩበት ግዙፍ ሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ መረብ (ኔትወርክ) ነው፡፡

የዘንድሮው የዓለም የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ቀን የተከበረው ‹‹ፅናት›› በሚል መሪ ቃል ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...