Sunday, February 25, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[የፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮችን በተመለከተ ክቡር ሚኒስትሩን በአስቸኳይ ስብሰባ ለማግኘት የጠየቁ አንድ ሹም በጠየቁት መሠረት በክቡር ሚኒስትሩ  ቢሮ ከሥራ መግቢያ ሰዓት በፊት በመገኘት እየተዋያዩ ነው]

 • አስቸኳይ ስብሰባ እያላችሁ ጊዜ ከምታባክኑ ሥራችሁን ብትሠሩ እኮ እንዲህ ጉልበታቸው አይበረታም ነበር።
 • የትኞቹን ነው የሚሉት ክቡር ሚኒስትር?
 • የተቸገርነው በአገር ወስጥ ኃይሎች ነው ስትል አልነበር እንዴ? እነሱን ነዋ፡፡  
 • ችግሩን አልተገነዘቡትም መሰለኝ. . .
 • እንዴት? 
 • ሰዎቹ. . . ማለቴ የአገር ውስጥ ኃይሎቹ 
 • እ. . .
 • ብቻቸውን እንዳልሆኑ የተረዱ አልመሰለኝም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ማለት ማን አለ አብሯቸው?
 • የውጭ ኃይሎች፡፡
 • እንደዚያ ነው ነገሩ?
 • እንደዚያ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡ በሐሳብም በፋይናንስም በውጭ ኃይሎች ስለሚደገፉ ነው ጉልበታቸው የበረታው።
 • ታዲያ አንዴ ዕርምጃ መውሰድ አይሻልም?
 • ዕርምጃ?
 • አሥሬ መግለጫ ከማውጣት ዕርምጃ ብትወስዱ አይሻልም? መግለጫ ምን ፋይዳ አለው? 
 • ዕርምጃውን እንዴት እንውሰድ በሚለው ነው የተቸገርነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምንድነው የተቸገራችሁት? 
 • ምን ዓይነት ዕርምጃ እንደምንወስድ ነው ግራ የገባን፡፡
 • ምን ዓይነት ዕርምጃ? መንግሥትን ለማዳከም፣ በአገር ላይ ጉዳት ለማድረስ ከውጭ ኃይሎች ጋር እያሴሩ አይደለም እንዴ?
 • ልክ ነው ክቡር ሚኒስትር፣ ይህንኑ የሚያሳይ በቂ ማስረጃ ይዘናል።
 • እና ዕርምጃ መውሰድ ለምን ተቸገራችሁ? 
 • ውጤቱ ተመሳሳይ እንዳይሆን ሠግተን ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • አልገባኝም ውጤቱ ምን ሊሆን ይችላል ብላችሁ ነው የሠጋችሁት?
 • መንግሥትን ማዳከም፡፡
 • እንዴት?
 • የካቢኔ አባላትም አሉበት ክቡር ሚኒስትር።
 • ምን?
 • ከካቢኔ ውጪ ያሉ የመንግሥት ኃላፊዎችና ርዕሰ መስተዳድሮችም ይገኙበታል።
 • እንዴት ሊሆን ይችላል? 
 • በክትትል ያገኘነው መረጃ የሚያስረዳው የአገር ውስጥ ክንፉን የሚመሩ የካቢኔ አባላት መኖራቸውን ነው።
 • እንደዚያ ነው ነገሩ?
 • በእርስዎ ላይ ነው ነገሩ ክቡር ሚኒስትር፡፡ 
 • ምን አልክ?
 • እንደዚያ ነው ነገሩ ማለቴ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 •  እንዴት. . . እንዴት. . . 
 •  ምን አሉኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • ይህ በዙሪያዬ ሲፈጸም እንዴት ማየት አልቻልኩም? እንዴት. . . እንዴት . . . እንዴት ማየት አልቻልኩም?
 • ዓይተዋል ግን. . .
 • ምን አልክ?
 • ባያስተውሉ ይሆናል እንጂ እንቅስቃሴው ግልጽ ነበር ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እንዴት. . .  ምን እያልክ ነው?
 • የማይመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎችበወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከምናምን አምባሳደር ጋር ተወያዩ› የሚል ዜና ሲተላለፍ ቢያንስ ይሰማሉ ብዬ ነው ክቡር ሚኒስትር። 
 • ታዲያ ዜና መተላለፉ እኛ ከምናወራው ጉዳይ ጋር ምን አገናኘው? 
 • ክቡር ሚኒስትር ከእርስዎ አላውቅም. . .
 • ይህ ባህሪዬ ነው የጎዳኝ፡፡
 • የቱ?
 • ከአንተ አላውቅም ያልከውን ተወውና የውጭ አምባሳደሮችን በተመለከተ የጀመርከውን ጉዳይ ቀጥል። 
 • የውጭ ግንኙነት ሥራ የማይመለከታቸው የፌዴራል መንግሥት ባለሥልጣናትና የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች አዲስ አበባ ከሚገኙ የውጭ አምባሳደሮች ጋር ደጋግመው ይገናኛሉ።
 • እና? 
 • ለምን እንደተገናኙ ጥርጣሬ እንዳይፈጠርምተመካከሩ› የሚል ዜና እንዲዘገብ ያደርጋሉ፣ ጀርባው ሲጠና ግን ውይይቱ ሌላ እንደሆነ ደርሰንበታል።
 • ምን አገኛችሁ?
 • አንዳንዶቹ ምርጫው ቢራዘም የተሻለ ነው ወይስ አይደለም በሚል አጀንዳ ላይ እንደተወያዩ ደርሰንበታል፣ አንዳንዶቹ የውስጥ መከፋፈል አለ ወይስ የለም በሚል ጉዳይ ላይ መወያየታቸው ታውቋል። 
 • እና የመንግሥት ኃላፊዎቹ አቋም ምን ነበር? ምርጫው ይራዘም ይላሉ?
 • በግልጽ አይናገሩም፡፡
 • የውጭ ግንኙነትን ከሚመራው ተቋም ያገኛችሁት መረጃ አለ?
 • ጠይቀናል፣ የመንግሥት ኃላፊዎቹም አምባሳደሮቹም ለዚህ ተቋም ያሳወቁት ወይም ከዚህ ተቋም የተሰጣቸው ፈቃድ የለም።
 • የውጭ ኤምባሲዎችም ሆኑ የመንግሥት ኃላፊዎች የውጭ ግንኙነት ተልዕኮ ሳይሰጣቸው እንዲህ ዓይነት ውይይት ማድረግ በፍፁም አይችሉም። 
 • እሱን በተመለከተ ተጨማሪ ጥናቶችን ማድረግ እንቀጥላለን ክቡር ሚኒስትር፡፡ 
 • እንዴት ማየት አልቻልኩም?
 • እሱን አልመረመርነውም ክቡር ሚኒስትር። 
 • እየቀለድክ ነው፣ ለማንኛውም ይህ ጉዳይ በሚስጥር ተይዞ ምርመራው ይቀጥል።
 • ጥሩ አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!

[ክቡር ሚኒስትሩ የሳምንቱን መጨረሻ ቀን ያለ ሥራ በእረፍት ለማሳለፍ አቅደው ያለ ወትሯቸው በመኖሪያ ቤታቸው መዋላቸውን የተመለከቱት ባለቤታቸው ጉዳዩን ለማወቅ እየጠየቁ ነው] 

 • ዛሬ ምን ተፈጠረ?
 • ምን ለማለት ነው?
 • ቤት ዋልክ ብዬ ነዋ? 
 • ቤቴ አይደለም እንዴ?
 • እንዲያው ያለ ወትሮህ ምን ሆነህ ብዬ ነው።
 • አገር ለማራመድ እየለፋን ዛሬን እረፍት ብናደርግ እንዴት ጥያቄ ይፈጥራል? 
 • እረፍት ማድረጋችሁ መቼ ጥያቄ ፈጠረ? ባይሆን . . . እ. . .
 • ባይሆን ምን?
 • ይሆን አገር ለማራመድ ያልከው ጥያቄ ይፈጥራል። 
 • እንዴት? አገር ለማራመድ እየለፋን አይደለም እንዴ?
 • ልፋትማ አለ። 
 • ታዲያ?
 • ርምጃው ወዴት እንደሆነ መለየት ተቸገርን እንጂ ልፋት አለ።
 • ዕርምጃውማ ወደፊት ነው።
 • ይመስላል እንጂ አይደለም። 
 • እንዴት?
 • ከፍረጃ ወጣን ብለን ወደ መፈራረጅ ገባን።
 • እሱም ቢሆን አገር ለማራመድ ነው።
 • ስደተኛውን መልሰን ስደተኛ ልንልክ ነው።
 • ያው አገር ለማራመድ ሲባል ነው።
 • የነዳጅ ዘይት ወጣ ብለን ተደስተን ሳናበቃ የምግብ ዘይት የተቸገርነውስ?
 • ቁጭት በራሱ ያራምዳል።
 • እኔም አልተራመድንም አላልኩም። 
 • ምንድነው ያልሽው ታዲያ?
 • ወደፊት ነው ወደኋላ?

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...

ሕወሓት በትግራይ ጦርነት ወቅት በፌዴራል መንግሥት ተይዘው ከነበሩት አባላቱ መካከል ሁለቱን አሰናበተ

በሕወሓት አባላት ላይ የዓቃቤ ሕግ ምስክር የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ...

የኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት ለመፈጸም የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማከናወን የሚያስችለውን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...

[ክቡር ሚኒስትሩ  የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላትን በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች እያዞሩ እያስጎበኙ ከአንድ ዲያስፖራ ጋር እየተወያዩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር የዛሬ ሁለት ዓመታት ገደማ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ ከተማዋን ጎብኝቼ ነበር። እውነት? አዎ። ታዲያ ልዩነቱን እንዴት አዩት? በጣም ይደንቃል። ሌላ ከተማ እኮ ነው የመሰለችው። አይደል? አዎ። እንዴት ነው...