Wednesday, September 27, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በማዕድን ልማት ዘርፍ የተሰማሩ የ27 ተቋማት ፈቃድ ተሰረዘ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በማዕድን ልማት ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ ወስደው የልማት እንቅስቃሴያቸው ችግር እንዳለበት የተለዩ የ 27 ኩባንያዎች ፈቃድ መሠረዙን የማዕድንና ነዳጅ ሚንስቴር አስታወቀ።

ሚንስቴሩ እንደገለጸው ፈቃዳቸው የተሰረዘው 27 ተቋማት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በማዕድን ልማት ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ ቢወስዱም በተደረገባቸው ማጣራት የማልማት ስራውን በተጓተተ መልኩ እያከናወኑ በመሆኑ ፣ ቃል የገቡትን ውጤት ማስመዝገብ ባለመቻላቸው እና ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ መግባት ባለመቻላቸው ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ምክንያት ሆኗል።

ከጥቂት ወራት በፊት በተደረገ ማጣራት ከላይ የተገለጹት ችግሮች የታዩባቸው 63 ተቋማት የማዕድን ልማት ፈቃድ መሠረዙ ይታወሳል።

የማዕድን የሀብት ብክነት በዝምታ የሚታለፍ እንቀዳልሆነ የገለጸው ሚንስቴሩ በቀጣይም ተመሳሳይ የማጣራት ስራ በማከናወን ተመሳሳይ እርምጃ መውሰድ እንደሚቀጥል የገለጸው ሚንስቴሩ ፤ ፍቃዳቸው በተሰረዘ ተቋማት ተይዘው የነበሩ የማዕድን ቦታዎችም ግልጽ በሆነ ዓለም አቀፍ ጨረታ በአፋጣኝ ወደ ስራ እንዲገቡ እንደሚደረግ አስታውቋል።

ሚንስቴሩ በዚህ እና በሌሎች የተቋሙ እንቅስቃሴ ላይ ከሰዓታት በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥም ታውቋል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች