ፖለቲከኛው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ዲስኩር እንዲያደርግ ተጋብዞ ንግግሩን ሲጀምር ከእንግዶቹ አንዳንዶቹ መጠጥ ወደተቀመጠበት ሌላ ክፍል ሾልከው መቀማመስ ጀመሩ፡፡ ከአንድ ሰዓት በኋላ ፖለቲከኛው ዲስኩሩን ስላልጨረሰ ሌላ የተሰላቸ ሰውዬ መጥቶ ተቀላቀላቸው፡፡
‹‹አሁንም እያወራ ነው?››
‹‹አዎን›› አለ ባጭሩ፡፡
‹‹ስለምንድነው ግን የሚያወራው?››
‹‹አላወቅኩም፤ አሁንም ድረስ’ኰ ራሱን እያስተዋወቀ ነው፡፡››
- አረፈ ዓይኔ ሐጎስ ‹‹ፖለቲከኞች እፈሩ – ቀልድና ቁም ነገር›› [2013]