Monday, February 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየፖለቲካ ፓርቲዎች በደቡብ አፍሪካ የመጪውን ምርጫ ድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመት ጎበኙ

የፖለቲካ ፓርቲዎች በደቡብ አፍሪካ የመጪውን ምርጫ ድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመት ጎበኙ

ቀን:

ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ ቁጥሮች በሌሎች አካላት መገለጽ የለባቸውም አለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአምስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን አመራሮች ደቡብ አፍሪካ በመላክ፣ የመጪውን ምርጫ ድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመት እንዲጎበኙ ማድረጉን አስታወቀ። ፓርቲዎቹ ብልፅግና፣ አብን፣ ኅብር፣ ኢሶዴፓና መኢአድ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ከፓርቲዎቹ በተጨማሪ በስም ካልተገለጹ ሚዲያዎች ለተውጣጡ ተወካዮች የድምፅ መስጫ ወረቀት የኅትመት ሒደቱን፣ የቴክኒክና የደኅንነት አጠባበቅ ሥርዓቱን በዝርዝር ማሳየት መቻሉን ቦርዱ ገልጿል።

‹‹ቦርዱ የፍትሐዊ አሠራሩ አንዱ ማሳያ አድርጎ ከሚወስደው የድምፅ መስጫ ወረቀት የዕጩዎች አደራደር ቅደም ተከተል መወሰኛ ሎተሪን በይፋ ካስጀመረበት ከመጋቢት 25 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመቱ የተጀመረ ሲሆን፣ ይህንንም ሥራ ከሚያካሂዱት ሁለት የኅትመት ድርጅቶች አንዱ በሆነውና በደቡብ አፍሪካ የሚገኘውን የሬን-ፎርም ኅትመት ማኅበር ከፓርቲዎችና ከሚዲያዎች የተወጣጡ የታዛቢ ቡድኑ አባላት ጎብኝተውታል፤›› ሲል አስታውቋል።

በጉብኝቱም የሥራ ሒደትና የኅትመቱ የደኅንነት አጠባበቁን ምን እንደሚመስል በኅትመት ኩባንያው የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ መደረጉን ያስታወቀው ምርጫ ቦርድ፣ ጎብኝዎች ግልጽ እንዲሆንላቸው የሚፈልጉትን ነገር በሥራ ኃላፊዎቹና በቦርዱ አመራር አማካይነት ማብራሪያ መሰጠቱን ጠቁሟል፡፡

የኅትመት ሒደቱ ምን እንደሚመስል፣ ከጥሬ ማቴሪያል ምርት አንስቶ እስከ ኅትመት ሒደቱና የማሸግ ሥርዓቱ ድረስ ያለውን አጠቃላይ ሒደት የተመለከተ ጉብኝት ተካሂዷል ያለው ምርጫ ቦርድ፣ ‹‹ፓርቲዎቹም ከጉብኝቱ በኋላ ለብዙኃን መገናኛ አካላት በሰጡት አስተያየት ባዩት ነገር መደሰታቸውን፣ ጉብኝቱም የቦርዱን ግልጽ አሠራር ማሳያ እንደሆነ የገለጹ መሆኑን፣ የጉብኝት አጋጣሚውም ፓርቲዎቹ ተቀራርበው ለመወያየት አጋጣሚን የፈጠረ እንደነበር ገልጸዋል፤›› ሲል አስረድቷል።

በቦርዱ ገለጻ መሠረት በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው ኅትመት የድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመቱን 45 በመቶ የሚሸፍን ነው፡፡ ይህም የደቡብ ክልል፣ የአማራ ክልል፣ የሲዳማ ክልልና የደቡብ ምዕራብ ሕዝቦች ሕዝበ ውሳኔን ያካትታል። ቀሪውና 55 በመቶ የሚሸፍነው የኅትመት ሥራ ዱባይ በሚገኘው አል-ጉህራር ማኅበር እየተከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ለአራት ቀናት በቆየው ጉብኝትም የብልፅግና ፓርቲ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ የኅብር ኢትዮጵያ ተወካይ (ኅብር)፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ)፣ እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከፍተኛ አመራሮች መሳተፋቸውን፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና ስማቸው ያልተገለጸ ሚዲያዎች  የጉብኝቱ አካል እንደነበሩ ገልጿል።

ይህ በዚህ እንዳለ ምርጫ ቦርድ ማናቸውም የመራጮች ምዝገባ ቁጥሮች በሌሎች አካላት መገለጽ እንደማይችሉ አስታውቋል፡፡

ከቦርዱ ውጪ የሚገለጹ ማናቸውም ዓይነት የመራጮች ምዝገባ ቁጥሮች ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን በማስታወቅ፣ ‹‹የመራጮችን መረጃ የሚያስተላልፉ አካላትም ከቦርዱ የሚያገኙትን ቁጥር ብቻ እንዲጠቀሙ እናበረታታለን፤›› ብሏል።

የመጪው የመራጮች ምዝገባ ከትግራይ ክልል በስተቀር፣ በአሥር ክልሎችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች እስከ ዓርብ ግንቦት 6 ቀን 2013 ዓ.ም ሲካሄድ ቆይቶ ተጠናቋል።

ቦርዱ በተለያዩ ጊዜያት የተመዘገቡ ጊዜያዊ መራጮችን ቁጥር እያሳወቀ መሆኑን አስረድቶ፣ የምዝገባውን መረጃ በሚያጠናቅርበት ወቅት የምርጫ ክልል ማስተባበሪያ መዋቅሮቹን በመጠቀም መሆኑን፣ ከምርጫ ጣቢያ የሚገኙ መረጃዎችን በማጠናቀር ወደ ማዕከል የኦፕሬሽን ዴስክ የሚላከውም በምርጫ ክልል ማስተባበሪያ ቢሮዎች አማካይነት ነው ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...