Saturday, December 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሕግ ባለሙያዎች ለአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ድጋፍና ጥብቅና የሚቆሙበት ድርጅት ተመሠረተ

የሕግ ባለሙያዎች ለአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ድጋፍና ጥብቅና የሚቆሙበት ድርጅት ተመሠረተ

ቀን:

የሕግ ባለሙያዎች የአካባቢ ጥበቃንና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ እየደረሱ  ያሉ ችግሮችን በበጎ ፈቃደኝነት ድጋፍና ጥብቅና እንዲቆሙ የሚያደርግ፣ ‹‹ቁም ለአካባቢ›› የተሰኘ  የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ተመሠረተ፡፡

ድርጅቱ መልካሙ ኡጎ በተሰኘ የሕግ ቢሮ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት መሆኑን፣ በቦርድ የሚመራና በተቋማትና በግለሰቦች አማካይነት የሚደርሱ የአካባቢ ብክለቶቸችን፣ የአካባቢና ብዝኃ ሕይወት ጉዳዮችን በመከታተል፣ ክስ ለፍርድ ቤትና ለአስተዳደራዊ አካላት በማቅረብ የሕዝብን ጉዳት ለመከላከል የተቋቋመ እንደሆነ፣ ቅዳሜ ግንቦት 7 ቀን 2013 ዓ.ም. በቤስት ዌስተርን አዲስ ሆቴል ይፋዊ የማኅበሩ ምሥረታ ፕሮግራም ላይ ተጠቅሷል፡፡

‹‹ቁም ለአካባቢ›› ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት የሕግ ባለሙያ አቶ መልካሙ ኡጎ በወቅቱ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ በስፋት ያልተለመደ አካባቢን በሚበክሉ፣ በተፈጥሮ ሀብትና በብዝኃ ሕይወት ላይ በማናቸውም ሁኔታ ጉዳት የሚያደርሱ ሰዎችና ተቋማትን ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ለሙግት የሚቀርቡበት ሥርዓት (Enviromental Public Interest Litigation) አለ፡፡ በመሆኑም ድርጅቱ ሊያሳካ ከተነሳቸው ዓላማዎች አንዱ፣ እንዲህ ዓይነት ጉዳዮችን ወደ ፍርድ ቤቶች ወስዶ የጉዳቱ ሰለባ የሆነውን ኅብረተሰብ ከብክለት በፀዳና ንፁህ በሆነ አካባቢ የመኖር መብቱን ለማረጋገጥ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

ምሁራንም ሆኑ የአካባቢ ተቆርቋሪዎች በተለያየዩ መንገዶች ስለአካባቢ ጥበቃ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ቢያደርጉም፣ አንድ ላይ ተሰባስበው የሚሠሩበት ሁኔታ እንደማይስተዋል የገለጹት አቶ መልካሙ፣ ከዚህ ድርጅት ዕውን መሆን በኋላ ግን ፍላጎታቸውን ያሳዩ ስለሆነ እንደ አገር ባለሙያዎች በጉዳዩ ላይ የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡

ቀደም ሲል በአዲስ አበባ የሚገኙ መንግሥታዊ የሆኑ ተቋማት በሚለቋቸው ፍሳሾች ምክንያት የደረሰውን የኅብረተሰብ የጤና ጉዳት ቁጭት ውስጥ ከቷቸው ተቋማቱ ላይ ክስ በመመሥረት ሙግት እንደያዙ ያስረዱት የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ፣ የአካባቢ ብክለትን በተመለከተው አዋጅ ቁጥር 300 መሠረት ማንም ሰው የእኔ ነው ብሎ ከሚነሳባቸው ነገሮች አንዱ በሆነው የአካባቢ ጉዳይ በቀጥታ ክርክር ማቅረብ እንደሚችል የሚፈቅድ ድንጋጌ እንዳለ አስታውሰዋል፡፡

በድርጅቱ ምሥረታ ላይ የተገኙ አንድ የሕግ ባለሙያ እንዳስታወቁት፣ የሕግ ባለሙያዎች በማንኛውም ማኅበረሰባዊ ጉዳዮች ላይ ቀዳሚ በመሆን የተባላሹ ጉዳዮችን ማስተካከል ካሉባቸው ኃላፊነቶች ዋነኞቹ እንደሆኑ አስታውሰው፣ ሙያን ከገንዘብ ምንጭ ባሻገር ለማኅበረሰብ አገልግሎት ማዋል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በተገናኘ ለውይይት መነሻ የሚሆን ጽሑፍ ያቀረቡት መለሰ ዳምጤ (ዶ/ር)፣ ሰዎች አካባቢን ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ለማግኘት፣ ለዘላቂ ልማት፣ ለትምህርት፣ ለምርምር፣ ለውበት፣ ለእምነት፣ እንዲሁም አካባቢን ለራሱ ለአካባቢው ሲባል እንደሚጠብቁ አስታውቀው፣ ‹‹አካባቢን ለራሱ ለአካባቢ›› የሚለውን ሐሳብ የሚያራምዱ ሰዎች፣ አካባቢ የጥቅም ሰጪነት ዋጋ ብቻ ያለው ሳይሆን ውስጣዊ እሴት ጭምር እንዳለው የሚገልጹ ናቸው ብለዋል፡፡

በፍልስፍና፣ በሥነ ምግባር፣ በሳይንስና በሃይማኖት አስተምህሮ አካባቢን መጠበቅና መንከባከብ የሰው ኃላፊነት መሆኑ ተቀምጧል ያሉት መለሰ (ዶ/ር)፣ ‹‹ሕጎቻችንን አካባቢን ለመጠበቅ በሚያስችል መንገድ ከማዋቀርና በየጊዜው እየተወሳሰቡ ከሚሄዱ የቴክኖሎጂ ዕድገቶችና ምርቶች ጋር መሳ ለመሳ መጓዝ እንዲችል ከማስቻል ባሻገር፣ በከፍተኛ ቁርጠኝነትና መተባበር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...