Sunday, April 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመንገዶች ባለሥልጣን በመንገዶች ዲዛይን ላይ ፖለቲካዊ ጫና እየበዛብኝ ነው አለ

መንገዶች ባለሥልጣን በመንገዶች ዲዛይን ላይ ፖለቲካዊ ጫና እየበዛብኝ ነው አለ

ቀን:

ለመንገዶች ግንባታ በሚዘጋጁ የዲዛይን ሥራዎች ከመሐንዲሶች ሙያዊ ውሳኔ በበለጠ የፖለቲካ ጫና አላሠራው ማለቱን፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

በመላ አገሪቱ በግንባታ ላይ ያሉና በዕቅድ የተያዙ አዳዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶች ውይይት ተደርጎባቸውና የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሶባቸው ወደ ሥራ እንዲገቡ እየተደረጉ አለመሆናቸውን፣ በፕሮጀክቶች  ሥራ ሲጀመር በመንገድ ዲዛይን ላይ የፖለቲካ ጫና እየበዛ በባለሙያዎች ለማሠራት መቸገራቸውን፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ተገኝ (ኢንጂነር) አስታውቀዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ፣ ‹‹የመንገድ ዲዛይን ሲዘጋጅ መንገዱ በዚህ ይለፍ ወይም በዚያ ይለፍ በሚል ያልተገባ ጫናና ግፊት በማድረስ የመንገዶችን ዲዛይን እንድንቀይር እየተገደድን ነው፤›› በማለት፣ ለሕዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት  የከተማ ልማት፣  ኮንስትራክሽንና  ትራንስፖርት  ጉዳዮች  ቋሚ ኮሚቴ ሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ተናግረዋል፡፡ 

ፓርማላው የትራንስፖርት ሚኒስቴርን የዘጠኘ ወራት ሪፖርት ለመገምገም በጠራው በዚሁ መድረክ ላይ የተገኙት የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች የሕዝቡ ጥያቄ የመንገድ ግንባታ ሆኖ ሳለ፣ መንገዱ በቤታቸው ጠርዝ ወይም በቤታቸው በኩል አልፎ እንዲሄድ የሚፈልጉ እየበዙ መጥተዋል ብለዋል፡፡

አቶ ካሳሁን እየበዙ ናቸው ባሉት በመንገድ ዲዛይንና ወሰን ማስከበር ሰበብ እየደረሰ ያለው ከባድ የሆነ አገራዊ ኪሳራ ለማስቀረት፣ በ2014 ዓ.ም. አዳዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ዕቅድ እንዳልተያዘ ተናግረዋል፡፡

ይህም የሆነው በ2015 ዓ.ም. መገንባት ላለባቸው መንገዶች አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች በማከናወን የመሸጋገሪያ ዓመት እንዲሆን ታስቦ ነው ብለዋል፡፡ በአንዳንድ የመንገድ ፕሮጀክቶች የዲዛይን ችግርና የወሰን ማስከበር መሰናክሎች በመብዛታቸው ምክንያት፣ በዕቅዳቸው መሠረት የግንባታ ሒደታቸው 90 በመቶ መድረስ በነበረባቸው ወቅት ከ18 በመቶ ማለፍ የተሳናቸው የመንገድ ድርጅቶች ቁጥር ብዙ እንደሆነ ሚኒስትር ዴኤታው አመላክተዋል፡፡

በየዓመቱ ለ40 ያህል አዳዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ ዕቅድ የሚያዝ ቢሆንም፣ ሙሉ የዲዛይንና የወሰን ማስከበር ሥራ አልቆላቸው በተያዘላቸው ጊዜ ወደ ግንባታ የሚገቡት የመንገድ ፕሮጀክቶች ከአሥር እንደማይበልጡ ሀብታሙ (ኢንጂነር) ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት 21 የመንገድ ፕሮጀክቶች በመንገድ ዲዛይን ችግርና በወሰን ማስከበር መሰናክሎች ምክንያት ግንባታቸው መቋረጡን፣ 92 የመንገድ ግንባታ አማካሪዎች ላይ ዕርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል፡፡

በ2013 ዓ.ም. በፀጥታ ምክንያት 24 የመንገድ ፕሮጀክቶች የቆሙ መሆናቸውን፣ በወሰን ማስከበርና በዲዛይን መስተጓጎል ምክንያት የ61 ፕሮጀክቶች ግንባታ መዘግየቱንም አክለው ገልጸዋል፡፡

ባለሥልጣኑ በአሁኑ ጊዜ ከግማሽ  ትሪሊዮን  ብር በላይ  ዋጋ ያላቸው  ከ200 በላይ  የመንገድ  ፕሮጀክቶችን እንደሚያንቀሳቅስ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኦቲዝምን ለመቋቋም በጥምረት የቆሙት ማዕከላት

ከኦቲዝም ጋር የሚወለዱ ልጆች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ...

አወዛጋቢው የወልቃይት ጉዳይ

የአማራና ትግራይ ክልሎችን እያወዛገበ ያለው የወልቃይት ጉዳይ ዳግም እየተነሳ...

ተጠባቂው የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የውድድር መለኪያ የሆነው የሞባይል ገንዘብ ዝውውር በኢትዮጵያ

የሞባይል ገንዘብ ዝውውር የሞባይል ስልክን በመጠቀም ሊገኙ የሚችሉ የፋይናንስ...

የአማራና ደቡብ ክልሎች ለሠራተኛ ደመወዝ መክፈል መቸገራቸውን የፓርላማ አባላት ተናገሩ

በአማራና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት...