Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበቴሌቪዥን የሚደረጉ የምርጫ ክርክር አጀንዳዎች ለገዥው ፓርቲ ያደሉ ናቸው የሚል ወቀሳ ቀረበ

በቴሌቪዥን የሚደረጉ የምርጫ ክርክር አጀንዳዎች ለገዥው ፓርቲ ያደሉ ናቸው የሚል ወቀሳ ቀረበ

ቀን:

በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ባሉ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሚቀርቡ የምርጫ ክርክር መድረክ የሚነሱ አጀንዳዎች፣ ለገዥው ፓርቲ ያደሉ ናቸው በሚል የፖለቲካ ፓርቲዎች ወቀሳ አቀረቡ፡፡

በአንድ የሕዝብ ሚዲያ የቀረቡ ሰባት ርዕሰ ጉዳዮች (አጀንዳዎች) ለገዥው ፓርቲ በሚመች መንገድ የተመረጡ በመሆኑ በድጋሚ እንዲስተካከል ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ጥያቄያቸው ሳይሰማ መቅረቱን የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ ተናግረዋል፡፡

አብንን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች በክርክር ሒደት ውስጥ ያላቸውን ወቀሳ ያቀረቡት፣ ማክሰኞ ግንቦት 10 ቀን 2013 ዓ.ም. የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት ከአሀዱ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

ሃይማኖትና ማንነትን የሚያጠለሽ ነገር በክርክር ሒደት ከቀረበ ተቆርጦ እንደሚወጣ ስምምነት መደረጉን አቶ ጣሂር አስረድተው፣ ከስምምነት ውጪ የፓርቲው የመጀመርያ ዙር ክርክር ተቆርጦ መውጣቱ ተገቢ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ የአብን የክርክር ሐሳብ ከሃይማኖትም ሆነ ከማንነት ጋር ግጭት የሚፈጥር እንዳልነበረ አስረድተዋል፡፡

በክርክር ሒደቱ በተለይም የከተማ ልማት ጉዳይን በተመለከተ ውይይቱን የመራው ጋዜጠኛ፣ ለገዥው ፓርቲ አድሎአዊነቱ በግልጽ የታየበት መሆኑን አቶ ጣሂር ጠቁመዋል፡፡

አወያዮች ጥያቄ ማቅረባቸው ተገቢነት ቢኖረውም፣ ጥያቄዎቹ ከሚነሱት ጉዳዮች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው መሆን እንደሚኖርባቸው፣ አወያዮች ደግሞ ገለልተኞች መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡

‹‹በዚህም ሚዲያዎቹ ከሞላ ጎደል የስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ገለልተኛነት ጥላ እንዲያጠላበት እያደረጉ ያሉ ተቋማት ናቸው፤›› ሲሉ አቶ ጣሂር ገልጸዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ በአካል ጉዳተኞችና በሴቶች አጀንዳ አመራረጥ ላይ ክፍተት እንዳለባቸው በመጠቆም፣ በፓርቲዎች በኩል መሻሻል ያለበት ጉዳይ እንዳለ አስረድተዋል፡፡

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙሉጌታ አበበ፣ በደቡብ ክልል በደራሼና በወላይታ ስድስት አባሎቻቸው በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት መታሰራቸውን፣ በማዕከላዊ ጎንደር ዕጩዎቻቸው የመግደል ሙከራ እንደተደረገባቸው ተናግረዋል፡፡ በእንዲህ ዓይነት የተጣበበ የፖለቲካ ምኅዳር የምርጫ ቅስቀሳ ሒደቱ ፈታኝ ነው ሲሉ አቶ ሙሉጌታ አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል በውጭ ጉዳይ፣ በፋይናንስና በኢንቨስትመንት፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ እንዲሁም ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ክርክር የቀረበ ቢሆንም፣ ሰብዓዊ መብትና በሕግ የበላይነት ላይ ሚዲያዎች መሥራት እንዳይችሉ መደረጋቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ተወካይ አቶ ሰለሞን ተሰማ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሰላም ዕጦት ያሠጋል የሚል ጉዳይ እንዳይነሳ ገዥው ፓርቲ በሚገኝበት የክርክር መድረኮች ላይ የመፈለግ አዝማሚያ እንዳለ አቶ ሰለሞን ጠቁመዋል፡፡

የሴቶች፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የሕፃናት፣ የታዳጊዎችና የሥራ አጥነት አጀንዳዎች ለመከራከሪያነት አለመካተታቸው ጉድለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...