Sunday, January 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየወልቂጤ ከነማ ቅሬታና የፋሲል ከነማ ሽንፈት

የወልቂጤ ከነማ ቅሬታና የፋሲል ከነማ ሽንፈት

ቀን:

የዘንድሮ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ያሸነፈው ክለብ የታወቀው ጨዋታው ሊጠናቀቅ አራት ጨዋታ እየቀረው መሆኑ ይታወቃል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ በጊዜ መታወቁ የጨዋታውን ድምቀት እንዳያደበዝዘው ሥጋት ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን በደረጃ ሠንጠረዡ ግርጌ የሚገኙ ክለቦች የውዝግብ መንስዔ መሆኑ ሊጉን አነጋጋሪ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ‹‹የችግሩ ተጠቂ ሆኛለሁ›› ያለው የወልቂጤ እግር ኳስ ክለብ ለፌዴሬሽኑ የቅሬታ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡

22 ጨዋታ አድርጎ በ22 ነጥብ በደረጃ ሠንጠረዡ 11ኛ ላይ የሚገኘው ወልቂጤ ከነማ፣ በፕሪሚየር ሊጉ 23ኛ ሳምንት ጨዋታቸውን ያደረጉት የሊጉ አሸናፊ ፋሲል ከነማና ድሬዳዋ ከነማ መካከል የተደረገው ጨዋታ በተለይ ፋሲል ከነማ ‹‹ከአቅም በታች ተጫውቷል›› በሚል ክስ ማቅረቡ ተሰምቷል፡፡ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት አዳማ ከነማና ጅማ አባ ጅፋር መውረዳቸው ያረጋገጡ ክለቦች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ወልቂጤ ከነማ ባለፈው ሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባስገባው የቅሬታ ደብዳቤ፣ ‹‹የሊጉ አሸናፊ ፋሲል ከነማ እንደ ወልቂጤ ሁሉ በመውረድ ሥጋት ውስጥ ከነበረው ድሬዳዋ ከነማ ጋር ባደረገው ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ ውጤቱ የሊጉ ጨዋታ ሊጠናቀቅ አራት ጨዋታ እየቀረው አሸናፊ መሆኑን ያረጋገጠውን ፋሲልን የሚመጥን አይደለም፡፡ ስለሆነም የጨዋታው አጠቃላይ እንቅስቃሴ በገለልተኛ አካል መታየት ይኖርበታል፣›› የሚለው ከቅሬታው መካከል ይጠቀሳል፡፡

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 23 ጨዋታ ያደረገው ድሬዳዋ ከነማ በ28 ነጥብ በደረጃ ሠንጠረዡ 9ኛ ላይ ተቀምጧል፡፡ 22 ጨዋታ ያደረገው ሌላው የመውረድ ሥጋት ውስጥ የገባው ሲዳማ ቡና 25 ነጥብ ይዞ ይከተላል፡፡ የውድድር ዓመቱ መርሐ ግብር ሊጠናቀቅ የቀረው የሁለት ጨዋታ ዕድሜ ብቻ ነው፡፡

ከዚህ አኳያ ወልቂጤ ከነማ ያቀረበው ቅሬታ አወዳዳሪው አካል ከሕግ አኳያ ገና ውሳኔ የሚሰጥበት ቢሆንም ብዙም የሚያዋጣው እንዳልሆነ የሚናገሩ አልጠፉም፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ ወልቂጤ ከነማ ከዚህ ይልቅ በቀጣይ ሊኖር ይችላል ተብሎ በአወዳዳሪው አካል ቀደም ሲል ውሳኔ የተሰጠበትን ዕድል ለመጠቀም ቢዘጋጅ እንደሚሻለው ይመክራሉ፡፡

የሊግ ካምፓኒው ቀደም ሲል የትግራይ ክለቦችን በሚመለከት በሰጠው መግለጫ፣ ፕሪሚየር ሊጉ 16 በነበረበት ወቅት የሊጉ አካል የነበሩት ሦስቱ የትግራይ ክለቦች (መቐለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ሽረ እንዳሥላሴ) በ2014 የውድድር ዓመት ወደ ሊጉ ተቀላቅለው ለመወዳደር ፈቃደኛ ከሆኑ የመወዳደር ዕድሉ ይኖራቸዋል፡፡ ክለቦቹ ባለው ሁኔታ የማይወዳደሩ ከሆነ ግን በእነሱ ምትክ ከፕሪሚየር ሊጉ የወረዱት ሦስቱ ክለቦችና በከፍተኛው (ሱፐር) ሊጉ ከየምድቡ ሁለተኛ ሆነው ያጠናቀቁት ሦስቱ ክለቦች ጋር እንዲጫወቱ ተደርጎ በሚያስመዘግቡት ውጤት መሠረት ሦስት ክለቦች ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲቀላቀሉ የሚደረግበት አሠራር እንደሚኖር መግለጹ አይዘነጋም፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...