Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበኢትዮጵያ ቡና ብቅ ያለው አዲሱ አልጋ ወራሽ

በኢትዮጵያ ቡና ብቅ ያለው አዲሱ አልጋ ወራሽ

ቀን:

በኢትዮጵያ እግር ኳስ በተለይም በፕሪሚየር ሊጉ ለረዥም ዓመታት የነበረው ገዥ አስተሳስብ ለእግር ኳስ ወሳኙ ነገር ግዙፍ ተክለ ሰውነት የሚል ነበር፡፡ ከዚህ በመነሳትም በበርካታ መድረኮች ላይ የሚታዩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾች ከተቀናቃኞቻቸው አንፃር ሲታዩ ደቃቆች የሚለው መለያቸው ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም ሳቢያ በእግር ኳስ ውጤት ለማስመዝገብ ወሳኙ ነገር በኢትዮጵያ የለም፣ እግር ኳስ ለኢትዮጵያውያን ታዳጊዎችና ወጣቶች ተስፋ አይደለም የሚሉ ድምፆች ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደመጥበት ጊዜም ብዙ ነበር፡፡

በዚህም የተነሳ በርካታ የአገሪቱ ክለቦች (ከፕሪሚየር ሊግ እስከ ብሔራዊ ሊግ) ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ተጫዋች ፍለጋ ሲያማትሩና የጨዋታ ሜዳዎችም በአብዛኛው ግዙፍ አፍሪካውያውያን ተጫዋቾች ሲሞሏቸው ቆይቷል፣ በዘንድሮ የውድድር ዓመት ብዛቱ ይቀንስ እንጂ አስተሳሰቡ አሁንም በአንዳንድ ክለቦች ዘንድ መንፀባረቁ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡

ከግብ ጠባቂ እስከ የፊት መስመር ተጫዋቾች ድረስ እነዚህ አፍሪካውያን ተጫዋቾች በየሜዳው ሲገናኙ መመልከት ብቻ ሳይሆን ከቆይታቸው ብዛት አንዳንዶቹ አማርኛን ጭምር የሚናገሩ አልጠፉም፡፡ ይሁንና ይህን አስተሳሰብ በሚገዳደር መልኩ የሚታሰበው የሰውነት ቁመናና ተክለ ሰውነት ሳይኖራቸው፣ ድንቅ ብቃትና ችሎታ ያሳዩን ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች በሁሉም አካባቢ ጠፍቶ ሳይሆን፣ በዋናነት ዕውቀቱ አለን የሚሉ ሙያተኞች (አሠልጣኞች) አጉል ዕይታ በክህሎቱ የታደሉ ታዳጊዎች ከመንገድ እንዲቀሩ ለማድረጉ የአደባባይ ምስጢር ሆኖም ቆይቷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዘንድሮ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ በተለይም በኢትዮጵያ ቡና ብቅ ያለው አቡበክር ናስር ነባሩን አስተሳሰብ ውድቅ ከማድረጉ ባሻገር በእግር ኳሱ ልዩ ተሰጥኦና ብቃቱ ላላቸው ወጣት ተጫዋቾች ተስፋ ሆኗል፡፡ ወጣቱ አቡበክር ለዚህ አንዱ ማሳያ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ፍጻሜውን ሊያገኝ ሁለት ጨዋታ በቀረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ዘመኑ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን ታሪክ አስመዝግቧል፡፡ በለጋ ዕድሜው በርካቶች የሚደግፉትን ኢትዮጵያ ቡናን በአምበልነት መምራት የቻለው አቡበክር፣ ዘንድሮ በከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ስኬት ማጠናቀቁን ተከትሎ ጥያቄው አሁን ላይ እግር ኳስ የሚፈልገው ዕውን የአካል ግዝፈት ወይስ ብቃትና ችሎታን ፈልፍሎ የማውጣት ችግር ወደሚል እንዲሸጋገር አድርጓል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ ለሁለት አሠርታት ያህል ከፍተኛ ጎል በማስቆጠር የሚጠቀሱት ሁለት ተጫዋቾች ብቻ ናቸው፡፡ ከ1990ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ ‹‹ፕሪሚየር ሊግ›› የሚለውን ስያሜ ባገኘበት ወቅት የድሬዳዋ ከተማ ያፈራችው ዮርዳኖስ ዓባይ መብራት ኃይል በአሁኑ ኤሌክትሪክ ገናና በነበረበት ወቅት ማለትም በ1993 ዓ.ም. በሊጉ ያስቆጠረው 24 ጎል ለ16 ዓመታት ያህል በክብረ ወሰንነት ቆይቷል፡፡ ከ2009 የውድድር ዓመት ጀምሮ ደግሞ ጌታነህ ከበደ በደደቢት እግር ኳስ ክለብ እያለ 25 ጎል አስቆጥሮ ላለፉት አራት ዓመታት የኮከብ ጎል አስቆጣሪነቱ ክብር በእሱ ተይዞ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

አዲሱ አልጋ ወራሽ አቡበከር በወቅቱ ከነበረው ሁኔታ አንጻር እንደ ማንኛውም የአዲስ አበባ ታዳጊዎች የነበረውን የእግር ኳስ ፍላጎት ለማርካት የሚፍጨረጨርበት ጊዜ እንደነበር በተጫዋቹ የእግር ኳስ ሕይወት ላይ የተሰነዱ ጽሑፎች ያስረዳሉ፡፡ ወጣቱ እግር ኳሰኛ ከአራት ዓመት በኋላ ያስመዘገበው ስኬት ምናልባትም ወቅቱን ካልጠበቀ ጭብጨባና አድናቆት ተርፎ የሚዘልቅ ከሆነ ወደ ተሻለውና ትልቁ የእግር ኳስ ክብር ሊደርስ የሚችልበት ዕድል እንዳለው የሚናገሩ አሉ፡፡

አቡበከር የውድድር ዓመቱ ሊጠናቀቅ ገና ሁለት ጨዋታ እየቀረው 27 ጎል አስቆጥሮ የጌታነህ ከበደን ከፍተኛ የጎል አስቆጣሪነት ክብር በሁለት ጎል ማሻሻል ችሏል፡፡ ተጫዋቹ ከዚህም በተጨማሪ በቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ብቻ ሳይሆን፣ በአገሪቱ የእግር ኳስ ታሪክ በአንድ የውድድር ዓመት አራት ጊዜ በአንድ ጨዋታ ላይ ሦስት ጎል (ሐትሪክ) መሥራት የቻለ ተጫዋች ለመሆን በቅቷል፡፡

ብዙዎች የተጫዋቹን የግል ክህሎትና ቴክኒካዊ ችሎታ አስመልከቶ፣ ‹‹ፈጣንና ዘመናዊ እግር ኳስ የሚጠይቀውን ዕይታና አዕምሮ የተላበሰ ነው፣ ተከላካዮችን አንድ ለአንድ ሲያገኝ ቀንሶ የማለፍ ልዩ ተሰጥኦ አለው፣ ጎሎችን ከማስቆጠር አልፎ ለጎል የሚሆኑ የተመቻቹ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ የማቀበል ብቃቱም ድንቅ ነው፡፡ በዚያ ላይ በዕድሜው ወጣት መሆኑ ከተጠቀመበት የሚቀረው እጅግ ብዙ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው ግን ሙያው የሚጠይቀውን ዲሲፕሊን አሟልቶ ከቀጠለ ብቻ ነው፤›› በማለት ይናገራሉ፡፡

በሌላ በኩል ፕሪሚየር ሊጉ በሱፐር ስፖርት አማካይነት ቀጥታ ሽፋን ማግኘቱ፣ ተጫዋቾች በሜዳ ላይ የሚያሳዩት እንቅስቃሴ የስፖርት ቤተሰቡ እንዲከታተለው መደረጉ የእያንዳንዱን ተጫዋች ብቃትና ችሎታ ለመመልከት አመቺ መሆኑ፣ አወዳዳሪው አካል የውድድር ዓመቱ ኮከብ ተጫዋቾች ምርጫ ተመልካች የሚታደምበት ቢሆን ምኞታቸው እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎቹ ይናገራሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...