Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ‹‹ዳግም ትኩረት ለኮቪድ-19›› የአዲስ አበባ ንቅናቄ

‹‹ዳግም ትኩረት ለኮቪድ-19›› የአዲስ አበባ ንቅናቄ

ቀን:

ከዓለም እስከ አገር አቀፍ ወረርሽኝ ሆኖ የበርካቶችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል፡፡ ኮቪድ-19፡፡ ወረርሽኙ ከተከሰተ ሁለተኛ ዓመቱን አሳልፏል፡፡

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ቫይረስ መገኘቱ ከተረጋገጠ ወዲህ፣ እስከ ግንቦት 12 ቀን 2013 .. ድረስ 4,048 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ የኮቪድ-19 ላቦራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው 2,672,100 ሰዎች ሲሆኑ፣ 268,035 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል በአሁኑ ወቅት የኮቪድ ቫይረስ ያለባቸው ግለሰቦች ቁጥር 39,992፣ ከበሽታው ያገገሙት 223,993 ሰዎች እንደሆኑ፣ 523 ሰዎች ደግሞ በኮቪድ-19 ቫይረስ ተይዘው በጽኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡ በመከላከያ ክትባት ንቅናቄውም 1,534,280 ሰዎችን መከተብ ተችሏል፡፡

የኮቪድ ወረርሽኝ ከተንሰራፋባቸው ከተሞች ዋነኛዋ አዲስ አበባ ናት፡፡ ይህንን ገጸታ ያስተዋለው የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ፣ በከተማዋ ለሁለት ወራት የሚዘልቅ ‹‹ዳግም_ትኩረት ለኮቪድ-19›› ከተማ አቀፍ የንቅናቄ መርሐ ግብሩን ይፋ አድርጓል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ንቅናቄው ይፋ ሲደረግ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ  ዮሐንስ ጫላ (/ር) የኮቪድ-19 ሥርጭትን መቆጣጠርና የሞት መጠኑንም መቀነስ የሚቻለው ሁሉም ተቋማት በቅንጅት ሲሠሩ ነው ብለዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከግንዛቤ ንቅናቄዎች በተጨማሪ የሆስፒታሎችን የመመርመር አቅምን ማሳደግ፣ የክትባት ሽፋኑን ተደራሽ ማድረግና የፅኑ ሕክምና ማዕከላትን በማሳደግ ላይ እየሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪና የኮቪድ-19 መከላከል ግብረ ኃይል ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር ዓባይ፣ አሁን ያለውን የኮቪድ-19 ሥርጭት በተለመደ የአደጋ ምላሽ አካሄድ መመለስ አይቻልም ብለዋል፡፡

የቫይረሱን ሥርጭት የበለጠ ሊያስፋፉ የሚችሉ ክንውኖች እንዳይኖሩ አመራሩ ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ከአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ለተከታታይ ሁለት ወራት በሚቆየው የዳግም ትኩረት ለኮቪድ-19 ንቅናቄ በመመርያ የተቀመጡ ክልከላዎችን እና የመከላከል ስታንዳርዶችን ሳያሟሉ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማትና ኃላፊዎች ላይ አስፈላጊው ዕርምጃ ይወሰዳል፡፡

ኢንስቲትዩቱ በሰጠው ጥብቅ ማሳሰቢያ፣  ከመቼውም ጊዜ በበለጠ  አሁን ማስክን በሚገባ ማድረግ፣ ሁልጊዜ የእጆችንንጽሕና መጠበቅ፣ ከሰዎች ጋር ያለውን ርቀት መጠበቅና ከሚፈጠሩ የሰዎች መሰባሰብ  ራስን መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡  በራስና በቤተሰብ፣ በጎረቤትና  በማኅበረሰብ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ሞት፣ማኅበራዊና  ሥነ ልቡናዊ ቀውስ፣ ምጣኔ ሀብታዊ  ችግሮችን ለመከላከል የመከላከያ መንገዶችን በአግባቡ በመተግበርና በማስተግበር  የወረርሽኙን  የሥርጭት መጠን እንዲገታም ጥሪውን አቅርቧል፡፡

እያንዳንዱ ግለሰብ፣ ቤተሰብ፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የጤና ባለሙያዎች፣ መምህራንና ሌሎችም  ባለድርሻ አካላት ተደጋግሞ የሚገለጹትን የመከላከያ መንገዶችን እንዲተገብሩም አሳስቧል፡፡

‹‹ከኮቪድ ተጠበቁ!››

እርስዎ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን በአግባቡ እየተገበሩ ነው?

  • ማስክ ሳያደርጉ በፍፁም አይንቀሳቀሱ
  • የእጅዎን ንፅህና በአግባቡ ይጠብቁ
  • በቂ የአየር ዝውውር በሌለበትና ሰው በተሰበሰበበት ቦታ አይገኙ

ይኼንን በመተግበር ራስዎንና ቤተሰብዎን ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ይታደጉ።

አራቱ ‹‹›› ሕጎች

  • መራራቅ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
  • መታጠብ እጅን በተደጋጋሚ በውኃና በሳሙና መታጠብ፣
  • መቆየት አስገዳጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት፣
  • መሸፈንከቤታችን ወጥተን ስንንቀሳቀስ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም፡፡
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...