Monday, June 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

የቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

ቀን:

ገንዘቤ ዲባባ ውድድር አቋርጣለች

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ውስጥ ሆኖ ለሚጠበቀው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን ጨምሮ አገሮች ዝግጅቶቻቸውን እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ በይፋ ሊጀመር ከሁለት ወር ያልበለጠ ጊዜ የሚቀረው ታላቁ የኦሊምፒክ ጨዋታ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ‹‹ይካሄዳል አይካሄድም›› የሚለው ያደጉ አገሮችን ሳይቀር በእጅጉ ያስጨነቀ ጉዳይ ሆኖ ነው የቆየው፡፡

ለዚህ እንደ ምክንያት የሚነገረው ደግሞ አዘጋጆቹ ጃፓናውያን ሳይቀር ተናፋቂው የኦሊምፒክ ጨዋታ በጃፓን ምድር እንዳይካሄድ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ ማሰማታቸው ዋነኛው ነው፡፡ ይህም የዝግጅቱን ዕጣ መና እንዳያስቀረው ተሠግቷል፡፡ ይሁንና በዚህ ወቅት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚያሳትፋቸውን መሥፈርት (ሚኒማ) ለማሟላት በጽናት  እንደቀጠሉ ናቸው፡፡
በቼክ ሪፐብሊክ ኢስትራቫ ግንቦት 11 ቀን 2013 .. በተካሄደው የኮንትኔንታል ቱር ዎርልድ ሊዲንግ ውድድር ላይ 3,000 ሜትር መሰናክል የተወዳደረው ጌትነት ዋለ ርቀቱን 809.49 በሆነ ጊዜ በመግባት አዲስ  ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸንፏል፡፡ በሴቶች 1,500 ሜትር ደግሞ ፍሬሕይወት ኃይሉ ርቀቱን 404.20 በሆነ ጊዜ በመግባት ለቶኪዮ የሚያበቃትን ሰዓት (ሚኒማ) ማግኘት መቻሏ ታውቋል፡፡

ምሽቱን በኦስትራቫ በተካሄደው በዚሁ ውድድር፣ በሴቶች አንድ 1,500 ሜትር ለአሸናፊነቱ ትልቅ ቅድመ ግምት የተሰጣትና በታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ታላላቅ ስኬቶችን በማስመዝገብ የምትታወቀው ገንዘቤ ዲባባ ውድድሩን ለማቋረጥ መገደዷ ግን ብዙዎችን ማስደንገጡ አልቀረም፡፡ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት በርቀቱ ተሳተፈችው ሒሩት መሸሻ በበኩሏ 407.52 በመግባት የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት በመሆን ማጠናቀቅ መቻሏ የኢትዮጵያን ተሳትፎና ተስፋ ያለመለመ ሆኗል፡፡

በሌላ በኩል ‹‹ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በረዥም ርቀት ካልሆነ ለመካከለኛ ርቀት የተፈጠሩ አይደሉም፤›› በሚል ለዓመታት ሲንፀባረቅ የቆየውን አስተሳስብ ጭምር በማሸነፍ፣ ምናልባትም አቅሙ ያላቸው ሙያተኞች ከተገኙ በቀጣይ በኦሊምፒክና በዓለም ሻምፒዮኖች ታላላቅ ድሎችን ማስመዝገብ የሚችሉ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ትልቅ ምልክት የሰጠችውና 800 ሜትር የተወዳደረችው ወጣቷ ድርቤ ወልተጂ ያስመዘገበችው ውጤት ይጠቀሳል፡፡ አትሌቷ ርቀቱን 159.79 በማጠናቀቅ ሁለተኛ በመሆን ውድድሯን አጠናቃለች፡፡ በወንዶች 1,500 ሜትር  የተወዳደረው ሌላው ተስፈኛ ሳሙኤል አባተ ርቀቱን 336.32 በሆነ ጊዜ ገብቶ ሦስተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ከሰሞኑ የአትሌቲክስ ድልና አሸናፊነት ጎን ለጎን ትልቅ ሥጋት ሆኖ እየተነገረ የሚገኘው፣ ከኦሊምፒክ ዝግጅትና ሥልጠና ጋር ተያይዞ የሚሰማው ነው፡፡ በብሔራዊ አትሌቶች መካከል አለመተማመንና መከፋፈሎች እንዲፈጠር የሚያደርጉ ምልክቶች በግልጽ መታየት መጀመራቸውን የዘርፉ ሙያተኞች ይናገራሉ፡፡

በዚህ ጉዳይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው እነዚሁ ሙያተኞችና አሠልጣኞች፣ ‹‹አንዳንድ ነባርና ታዋቂ አትሌቶች ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በሾማቸው ብሔራዊ አሠልጣኞች መሠልጠን አቁመዋል፡፡ ዝግጅት የሚደርጉት በፈለጉት ሰዓትና ጊዜ ራሳቸው በመረጡት አሠልጣኝ ነው። ፌዴሬሽኑም ሆነ ብሔራዊ አሠልጣኞች ለችግሩ የሚወስዱት የመፍትሔ አማራጭ በአብዛኛው ልመና ነው፤›› በማለት ፌዴሬሽኑ አፋጣኝ የማስተካካያ ዕርምጃ ሊወስድ እንደሚገባው ይመክራሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ የአሠልጣኞቹንም ሆነ የፌዴሬሽኑን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...