Wednesday, July 24, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የቴሌኮም አገልግሎቶች ለመስጠት ፈቃድ የተሰጠው ጥምረት ኃላፊዎች ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እናሰርፃለን አሉ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎቶች መስጠት የሚያስችለው ፈቃድ በመንግሥት የተሰጠው ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ የተሰኘው የኩባንያዎች ጥምረት ኃላፊዎች፣ በመጪዎቹ አሥር ዓመታት ከ8.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ የቴሌኮም ኢንቨስትመንት ውስጥ በመሰማራት፣ በኢትዮጵያ ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሥርፀት እንደሚሠሩ አስታወቁ፡፡

የቮዳፎን ግሩፕ አባል በሆነው ሳፋሪ ኮም የሚመራው ይህ ጥምረት እ.ኤ.አ. ከ2022 የመጀመያ ሩብ ዓመት ጀምሮ በአር ዓመት ውስጥ የፈቃድ ዋጋ፣ ካፒታልና ራ ለማንቀሳቀስ የሚጠቀመውን ገንዘብ ጨምሮ በተጠቀሰው የኢንቨስትመንት ፍሰት የቴሌኮዩኒኬሽን አገልግሎት በኢትዮጵያ ለመጀመር በማቀድራሱን የቻለ አንድ ኩባንያ እንደሚያቋቁም ጥምረቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል

የሳፋሪኮም ዋና ራ አስፈጻሚ ፒተር ዴግዋ ‹‹የቴሌኮም የመገናኛ አውታሮችን በመዘርጋት ዲጂታል የኑሮ ዘይቤን ለማቅረብ ከኢትዮጵያ ዝብ ጋር መራት የምንችልበት ዕድል በማግኘታችን እጅግ ደስተኞች ነን። ባለፉት መታት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ኃይልና በደንበኞቻችን ላይ የነበረውን አዎንታዊ ተዕኖ ተገንዝበናል፤›› ብለዋልጥምረቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በመራት ተመሳሳይ ለውጦችን በማምጣት፣ ለባለ አክሲዮኖቻችን ቀጣይነት ያለው የኢንቨስትመንት ትርፍ እንደሚያስገኝ ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል። 

የቮዳኮም ዋና ራ አስፈጻሚ ሻሚል ጁሱብ በበኩላቸው የጥምረቱ አጋሮች በተለይ በጤና፣ ትምህርትና ግብርና ዘርፎች ለውጥን መረት ያደረጉ የቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን በማቅረብ የተካኑ መሆናቸውን ገልጸዋል‹‹ቮዳኮም እ.ኤ.አ. በ2025 ብቻ 100 ሚሊዮን አፍሪካውያንን በቴሌኮም ለማስተሳሰር የገባውን ቃል ለማሳካት መጠነ ሰፊ የዲታል ዕቀፍ ማስፋያዎችን በማከናወን፣ ኢትዮጵያውያን የኑሮ ደረጃ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ይፈልጋል፤›› ብለዋል።

የቮዳፎን ግሩፕ ዋና አስፈጻሚ ኒክ ሪድ ‹‹በዓለም ላይ ለቴሌኮም ገበያ ውድድር በራቸውን ለመክፈት ከመጨረሻዎቹ አገሮች ተርታ ለሆነችው ኢትዮጵያ ይህ ወሳኝ የዕድገት ደረጃ ነው። እጅግ ግዙፍ የምጣኔ ብትና የልማት ዕድገት አቅም ያለበት አገር እንደ መሆኗ የተቋሞቻችን ጥምረት ረቀቁ የመገናኛ አውታሮና በዲጂታል አገልግሎቶቹ ይህንን ምቅ አቅም ያጎለብታል፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡

በአፍሪካ የሲዲሲ ሊቀመንበር ትንቢተ ኤርሚያስ፣ ‹‹ዘመናዊ፣ የተረጋጉና በማደግ ላይ ያሉ ምጣኔ ብቶች ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው አስተማማኝ መረተ ልማትና ለዓለም አቀፍ ንግድ በር በመክፈት የተገነቡ ናቸው። ከከተማ እስከ ገጠር ነዋሪው፣ ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ ንግድ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወሳኝ የገቢ ዕድሎችን የሚፈጥሩ ዘመኑ የደረሰባቸው የዲጂታል አውታረ መረብ መስመሮችን ለመዘርጋት ተዘጋጅተናል፤›› ብለው፣ ይህም ለአገሪ ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ለመላው የኢትዮጵያ ዝብ መልካም የምራች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የኢንቨስትመንት ጥምረ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማገዝ እንዲሁም የዜጎቿን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የራሱን ድርሻ የማበርከት ዓላማን ሰንቆ የተነሳ መሆኑ በመግለጫው ተወስቷል

‹‹ከ112 ሚዮን በላይ የሚኖባትና ከአፍሪካ በዝብ ብዛት ሁለተኛዋ አገር ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ለቴሌኮም ኢንስትሪው ውድድር በራቸውን ዘግይተው ከከፈቱት አገሮች አንዷ ሆናለች፤›› ያለው የጥምረቱ መግለጫ፣ኢትዮጵያ መንግት እ.ኤ.አ. በ2019 የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳው አካል አድርጎ ባስጀመረው ጠንካራ የለውጥ ደት የአራር ማሻሻያው (ሪፎርሙ) የራ ዕድሎችን ማበራከት፣ ድህነትን መቀነስና የአገሪን ኢኮኖሚ ሁሉን አካታች በሆነ መንገድ ቀጣይነቱን ማረጋገጥ ዓላማው አድርጎ የተነሳ መሆኑን አስታውሷል

ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ የተሰኘው የኩባንያዎች ጥምረት ቮዳኮም ግሩፕ፣ ቮዳፎን ግሩፕ፣ ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽን የተባሉ ግዙፍ የንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያዎች እንዲሁም ሲዲሲ ግሩፕ የተሰኘ የዩናይትድ ኪንግደም የልማት ዋዕለ ነዋይ አቅራቢ ተቋምን የሚያካትት ነው፡፡ ቅዳሜ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥምረቱ ያስገባውን ሰነድ በማየት፣ በኢትዮጵያ ፈቃድ እንዲሰጠው መወሰኑ ይታወሳልለተሰጠውም ፈቃድ ለመንግሥት 850 ሚሊዮን ዶላር እንደሚከፍል መዘገቡ አይዘነጋም፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች