በግብፅ ካይሮ በተካሄደው የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) 19ኛ ጠቅላላ ጉባዔና ምርጫ ላይ አልጄሪያዊው ሙስጠፋ ባህራፍ በድጋሚ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡
በምርጫው ሒደት በ38 ድምፅ ያሸነፉት አልጀሪያዊው ሙስጠፋ ባህራፍ ለቀጣዩ አራት ዓመታት አኖካን በፕሬዚዳንትነት ያስተዳደራሉ፡፡ ተፎካካሪ ሆነው ለምርጫ የቀረቡትና 15 ድምፅ ያገኙት ሩዋንዳዊቷ ሊዲያ ኒስካራ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር)፣ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቷ ኮማንደር ብርሃኔ አደሬና ዋና ጸሐፊው አቶ ዳዊት አስፋው በአኖካ ጉባዔ ላይ መታደማቸውን ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ገልጿል፡፡
ከሳምንታት በፊት ባካሄደው የአኖካ ዞን አምስት አገሮች ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር ምርጫ አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር) ፕሬዚዳንት አድርጎ መምረጡ ይታወሳል፡፡