Saturday, May 18, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልየአማራ ባህል ማዕከል በሕዝብና በባለሀብቶች ትብብር ይሠራል ተባለ

የአማራ ባህል ማዕከል በሕዝብና በባለሀብቶች ትብብር ይሠራል ተባለ

ቀን:

የአማራ የባህል ማዕከልን በአዲስ አበባ ከተማ ለመገንባት ለተነሳው ለአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) የከተማው አስተዳደር 42,200 ካሬ ሜትር ቦታ አስረክቧል፡፡

አልማ በሕዝብና በባለሀብቶች ትብብር ለሚያስገነባው ማዕከል ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር፣ ግንቦት 15 ቀን 2013 ዓ.ም. በአንድነት ፓርክ ሲካሄድ፣ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታውን ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር አስረክበዋል፡፡

በአዲስ አበባ የሚገነባው የባህል ማዕከል የአማራን ባህል፣ ወግ፣ ሥርዓትና ትውፊት የሚያንፀባርቅ እንደሚሆን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ላደረገው ሁሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

ምክትል ከንቲባዋ በበኩላቸው ልማት የሁሉንም ትብብርና አንድነት የሚጠይቅ መሆኑን ጠቅሰው፣ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ባህሎች የሚታዩባት ለማድረግ ጥረቱ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የባህል ማዕከሉ በሕዝብና በባለሀብት ትብብር እንደሚገነባ የገለጸው አልማ፣ በ1984 ዓ.ም. የተመሠረተና በክልሉ ዘርፉ ብዙ የማኅበረሰብ አገልግሎት እየሰጠ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

አልማ ከ92 ሺሕ በላይ በጎ ፈቃደኞች ያሉት ሲሆን 2.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሀብት ሥራ መሰብሰቡን ተጠቁሟል፡፡

ሌሎችም ክልሎች በአዲስ አበባ ከተማ የባህል ማዕከል ግንባታ ለማከናወን ሒደት ላይ መሆናቸውም ተጠቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ