Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበኢትዮጵያ በኮቪድ-19  ሕይወታቸውን ያጡት ከአራት ሺሕ በላይ ሆነዋል

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19  ሕይወታቸውን ያጡት ከአራት ሺሕ በላይ ሆነዋል

ቀን:

በግንቦት የመጀመርያ ሳምንት መመርያ ባለመፈጸም ከ1000 በላይ አሽከርካሪዎች ተቀጥተዋል

‹‹ጤና ይስጥልኝ፡፡ የኮቪድ ፅኑ ሕሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ መዘናጋት ብዙዎችን አሳጥቶናል፡፡ ጥንቃቄ ብዙዎችን ዛሬን ያሻግራል፡፡ እባክዎትን ማስክዎን ያደርጉ፣ ሕይወትዎን ያትርፉ!››

ኢትዮ ቴሌኮም የሁለቱ ዓበይት የጤና ተቋማት የጤና ሚኒስቴርም ሆነ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዱካን በመከተል ደንበኞቹ የቴሌፎን የድምፅ ጥሪ ሲያደርጉ ‹‹ከኮሮና ተጠበቁ አትዘናጉ›› የሚል አንድምታ ያለውን የደወል ድምፅ እያስተጋባ ነው፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ማድረግ የሚገቡ ጥንቃቄዎችን ኅብረተሰቡ እንዲተገብር ያለመታከት እያሳሰበ መሆኑ አንዱ ማሳያ ነው፡፡

ይህ ማሳሰቢያ ሲፍታታም ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መስተጋብር ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተፅዕኖ ሳያንስ፣ እርስዎ በመዘናጋትም ሕይወትዎን እንዳያጡ አሊያም እንዳይታመሙና እንዳይሠቃዩ ልብ በሉ የሚል ጥሪ አለው፡፡

በሌላ በኩልም ‹‹ኮቪድ-19 ዛሬም የብዙ ወገኖቻችንን ሕይወት እየቀጠፈ ሰልሚገኝ ራስዎን ከቫይረሱ ይጠብቁ!›› እያለ በየቀኑ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት የሚያሳስበው የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ከተከታታይ መልዕክቶቹ መካከል ‹‹በማንኛውም እንቅስቃሴዎ ጊዜ በኮቪድ-19 ሊያዙ ስለሚችሉ የመከላከያ መንገዶችን ሳይዘናጉ ይተግብሩ!›› የሚለውም ይገኝበታል፡፡

ይሁን እንጂ በጤና ኢንስቲትዩቱ  የግንቦት አጋማሽ አሁናዊ መረጃ እንደሚያሳየው፣ እስካሁን 4,084 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ለ2,691,240 ሰዎች በተደረገው የላቦራቶሪ ምርመራም 269,500 ሰዎች በበሽታው ሲያዙ፣ 230,784 ሰዎች አገግመዋል፡፡ 485 ሰዎች ደግሞ  በጽኑ የታመሙ ሲሆን 34,630 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው አስታውቋል፡፡ የተከታቢዎች ቁጥርም 1,684,450 ደርሷል፡፡

የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአሥር ክፍሎች የቀረበው መመርያ ውስጥ በስብሰባ፣ በቀብር ሥርዓት፣ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት፣ የአደባባይ በዓላት አከባበር ላይ ስለሚወሰዱ ጥንቃቄዎች የሚተነትን ይገኝበታል፡፡

በሌላ በኩል መመርያውን መተግበር የማንኛውም ሰውና ተቋም ግዴታ ሲሆን በተደነገጉት ክልከላዎችና ግዴታዎችን የተላለፈ ሰው አግባብ ባለው የወንጀል ሕግ መሠረት ተጠያቂ እንደሚሆን ይጠቁማል፡፡

በአሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው ቅጣት

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለሥልጣንና የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ በከተማዋ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል የወጣውን መመርያ በተላለፉ 1,002 አሽከርካሪዎች መቀጣታቸውን ሰሞኑን አስታውቀዋል፡፡

መመርያውን ለመተግበር በተደረገ ቁጥጥር ከግንቦት 2 ቀን እስከ 10 ቀን ብቻ ትርፍ በመጫን 603 ማስክ አለማድረግ 204 ከታሪፍ በላይ ማስከፈል 91 መስመር ባለመሸፈን 65 ታፔላ ባለመስቀል 38 እና በሥራ ሰዓትመቆም በጠቅላላው 1,002 አሽከርካሪዎች ተቀጥተዋል፡፡

በሚያዝያና መጋቢት ወር ብቻ የወጣውን መመሪያ የጣሱ 10,305 በላይ አሽከርካሪዎች ላይ በመመርያው መሠረት ተቀጥተዋል፡፡ በቀጣይም ክትትሉና ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

ትርፍ በመጫን መተላለፍ፣ ከታሪፍ በላይ ማስከፈል፣ የኮቪድ 19 መከላከያ ተግባራት አለማከናወን፣ በሥራ ሰዓት ያለ ሥራ ቆሞ መገኘትና ታፔላ ሳይሰቅል መሥራት 500 እስከ 2,000 ብር እንደሚያስቀጣ በመመርያው ተደንግጓል፡፡

በሁሉም ክፍላተ ከተማ የንቅናቄ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት በዋና ዋና መናኸርያዎችና መስመሮች ላይ የማስገንዘቢያ ሥራ ሲሠራ መቆየቱንም ሁለቱ ተቋማት ገልጸዋል፡፡

ጥብቁ መመርያ እስከ ምን ድረስ ነው?

የጤና ሚኒስቴር ባወጣው ጥብቅ መመርያ መሠረት ማንኛውም አገልግሎት የሚሰጥ የመንግሥታዊና የግል ተቋም አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ተቋሙ ለሚመጡ ተገልጋዮች ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ ተገልጋዮች ሁለት የአዋቂ ዕርምጃ ተራርቀው የሚቆሙበትን ቦታ ምልክት የማድረግና ተገልጋዮችም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውንና ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት በተቋሙ ላይ ተጥሏል፡፡

 የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ አሽከርካሪ፣ አገር አቀፍም ሆነ የከተማ ውስጥ ትራንስፖርትን በተመለከተ በሕግ ከተወሰነው የመጫን አቅም ልክ ሰዎችን የመጫን፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ያላደረጉ ሰዎችን አገልግሎት መስጠት እንደሌለበት መግለጫው አመልክቶ፣ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አሠሪዎች በተመለከተ በግንባታ ሳይቶች ላይ አስፈላጊውን ንጽህና ለመጠበቅ የሚረዱ እንደ ውኃ፣ ሳሙና፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ፣ ሳኒታይዘር ወይም አልኮል፣ የሙቀት መለኪያ መሣሪያ እንዲሁም የፀረ ተህዋሲያን ግብዓት የማሟላት ግዴታ እንዳለባቸው ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ተተኳሪ ጉዳዮች

ኮቪድ-19 በወረርሽነት ዓለምን ካካለለሁለት ዓመት እልፍ ብሏል፡፡ በእነዚህ ወራት  የዓለም ሕዝብ ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠበቅ፣ ‹‹በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ›› እንዳይያዝ የጤና ባለሙያዎችና ዓለም አቀፋዊም ሆነ አገራዊ ተቋማት ማስገንዘቢያዎችን ከመስጠት ችላ ያሉበት ጊዜ አልነበረም፡፡

ኮቪድ -19 ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል፡፡

ኅብረተሰቡ በሽታው በቀላሉ የሚተላለፍ በመሆኑ ሳይዘናጋ ለተለያዩ ጉዳዮች በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተውና አካላዊ መራራቅን በመተግበር የበሽታውን ሥርጭት እንዲከላከል ኢንስቲትዩቱ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡

ለዚህም የኮሮና ቫይረስ መከላከያን አራቱን ‹‹›› ሕጎች በመተግበር የበሽታውን ሥርጭት ሁሉም እንዲከላከልም ጥሪ አቅርቧል፡፡

አራቱ ‹‹›› ሕጎች

  • መራራቅ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
  • መታጠብ እጅን በተደጋጋሚ በውኃና በሳሙና መታጠብ፣
  • መቆየት አስገዳጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት፣
  • መሸፈን ከቤታችን ወጥተን ስንንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም፡፡
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...