Monday, July 22, 2024

[ክቡር ሚኒስትሩ በምርጫ ሒደቱ ላይ ከአማካሪዎቻቸው ጋር እየተወያዩ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር ሒደቱ ጥሩ ቢሆንም ፍርድ ቤቶች አስቸግረውናል፡፡
 • ፍርድ ቤቶች ነው ያልከው?
 • አዎ ክቡር ሚኒስትር፡፡ 
 • ምን ተፈጥሮ ነው?
 • የምርጫ ሰሌዳውን ያገናዘበ ውሳኔ እየወሰኑ አይደለም።
 • ምን ማለት ነው?
 • የፓርቲዎች ምዝገባ ከተጠናቀቀ በኋላ ፓርቲዎች እንዲመዘገቡ ይወስናሉ።
 • ችግሩ አልታየኝም፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ይህ ብቻ አይደለም።
 • እሺ?
 • ፖለቲከኞች ያቀረቡትን አቤቱታ እየመረመሩ ይቆዩና የዕጩዎች ምዝገባ ተጠናቆ ወደ ሌላ ተግባር ከተገባ በኋላ በዕጩነት እንዲመዘገቡ ይወስናሉ። 
 • በእኛ ላይ የሚያመጣው ችግር አልታየኝም፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ምርጫ ቦርድ እንዴት ብሎ ወደኋላ ይመለሳል፣ ከተመለሰ ደግሞ ምርጫው ሊጓተት ነው፡፡
 • ለምን ወደኋላ ይመለሳል?
 • ውሳኔው የፍርድ ቤት በመሆኑ ነዋ፡፡
 • የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አከብራለሁ፣ ነገር ግን የጊዜ ሰሌዳው አልፏል በማለት ማለፍ ስለሚችል አትጨነቅ።
 • ቦርዱ እንደዚያ ማለት ይችላል?
 • ይችላል፣ አትጨነቅ። 
 • እንደዚያ ከሆነማ እየደገፉን እኮ ነው፡፡
 • እነ ማን ናቸው?
 • ፍርድ ቤቶቹ፡፡
 • እያገዙን አይባልም፡፡
 • እና
 • እንደዚያ አይባልም፣ በሕግ የተሰጣቸውን ኃላፊነት እየተወጡ ነው። 
 • ልክ ነው ክቡር ሚኒስትር ሥራቸውን እየሠሩ ነው!

[ክቡር ሚኒስትሩ የሕግ አማካሪያቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያቀረበውን ሪፖርት አስመልክቶ ውይይት እያደረጉ ነው]

 • የሰብዓዊ መብቶችን በሚከታተለው ተቋም ላይ የሚሰነዘሩ መንግሥታዊ ትችቶች ሊቆሙ ይገባል ስትል ምን ማለትህ ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር ይህንን ተቋም በተሻለ ገለልተኛነት እንዲቋቋም ያደረግነው ለይስሙላ ባለመሆኑ ማስተካከያ እንዲደረግ ነው። 
 • እሱን አይደለም የጠየቅኩት፣ መንግሥታዊ ትችቶች ስትል ምን ማለትህ እንደሆነ እንድታብራራ ነው፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ከሰሞኑ የአንድ ክልል አመራሮች የኮሚሽኑን ሪፖርት ከማጣጣላቸው በላይ ኮሚሽኑ ገለልተኛ አይደለም፣ በአንድ ክልላዊ መንግሥትና ብሔረሰብ ላይ አነጣጥሯል የሚል መግለጫ አውጥተው በሚዲያዎች ተሠራጭቷል።
 • ታዲያ የፌዴራል መንግሥት በክልል ጉዳይ ምን የሚመለከተው ነገር አለ? ራሳቸው ጉዳዩን ቢጨርሱት አይሻልም?
 • ክቡር ሚኒስትር የዚህን ተቋም አስፈላጊነት በማመን በገለልተኝነትና በነፃነት እንዲሠራ ያደረገው የፌዴራል መንግሥት ነው፣ ይህንን በማድረጋችንም ዓለም አቀፍ ዕውቅና ተሰጥቶታል፣ እንደሚያውቁት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጭምር ከተቋሙ ጋር በቅርቡ የጋራ ምርመራ ለማድረግ እየተዘጋጀ ነው። 
 • ስለዚህ?
 • ተቋሙ ያገኘው ተቀባይነት ከውስጣችን በሚነሱ ያልተገቡ ትችቶች እንዳይጠለሽ መጠንቀቅ ያስፈልገናል። 
 • መጠንቀቁ ጥሩ ነው፣ ነገር ግን የፌዴራል መንግሥት ደግሞ በክልሎች ላይ ሥልጣን ስለሌለው ምንም ማድረግ አንችልም። 
 • ዛሬ ምንም ማድረግ ካልቻልን፣ ነገ ሌላውም ክልል ተመሳሳይ ባህሪና ተግባር መፈጸሙ አይቀርም። 
 • ተቋሙ ገለልተኛ ሆኖ አይደል እንዴ የተቋቋመው?
 • ልክ ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • ታዲያ ትችቶቹንም ራሱ ቢከላለከል አይሻልም? እኛ ከተከላከልንለት ገለልተኝነቱ ጥያቄ ውስጥ አይውድቅም?
 • እንከላከልለት የሚል አይደለም እኔ ያቀረብኩት ሐሳብ ማጠንጠኛ፡፡
 • እና ምንድነው?
 •  ያልተገቡ ትችቶች መቀጠል የለባቸውም፣ መቆም አለባቸው ነው ያልኩት። ዛሬ ይህንን ማድረግ ካልቻልን በዜጎች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይባባሳልፈጻሚዎቹንም ተጠያቂ ማድረግ አስቸጋሪ ይሆናል ነው የምለው። ሰብዓዊ መብትን ማረጋገጥ ደግሞ የፌዴራል መንግሥት ኃላፊነት ነው።
 • እሱ ላይ ልክ ነህ። ነገር ግን ያለንበት የምርጫ ወቅት መሆኑንም ከግምት ማስገባት አለብን። 
 • ክቡር ሚኒስትር ይህ ጉዳይ በእጅጉ የሚያስፈልገው በምርጫ ወቅት ነው፡፡
 • ይህ ጉዳይ በይደር ቢቆይ ይሻላል፡፡
 • ጥሩ ይደር። 
 • በሪፖርቱ የተነሳው ሌላኛው ጉዳይ ምን ነበር? … አዎየአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ የመፍትሔ ውሳኔ መቀመጥ አለበት ብለሃል፡፡ የትኛውን አስቸኳይ አዋጅ ነው? 
 • አንድ አስቸኳይ አዋጅ ብቻ እኮ ነው የታወጀው ክቡር ሚኒስትር፡፡ 
 • አንድ ነው አይደል? እኔ እኮ የዘነጋሁት ይኖር ይሆን ብዬ ነው።
 • አይ... አንድ ነው ክቡር ሚኒስትር። 
 • ጥሩ፣ መፍትሔ ይሰጥ ያልክበት ምክንያት ግን አልተብራራምምንድነው ጉዳዩ?
 • ክቡር ሚኒስትር አስቸኳይ አዋጁ ለስድስት ወራት ብቻ ነው የተጣለው፣ ይህ ጊዜም ተጠናቋል። ወይ መራዘም አለበት አልያም አስቸኳይ ሁኔታው ስለተቀረፈ ተብሎ ማብቃት አለበት። 
 • እንዴት እንደዚህ ትላለህ? አስቸኳይ ሁኔታው ተፋፍሞ ቀጥሎ እያየኸው? 
 • ስለዚህ እንዲራዘም ይደረግ፣ አለበለዚያ በዚህ አካባቢ የሚደረግ እንቅስቃሴ በሕግ ተቀባይነት አይኖረውም ክቡር ሚኒስትር።
 • ገባኝ… ግን እንደምታውቀው በውስጥ በምርጫው ሥራበውጭ ደግሞ በዲፕሎማሲ ጫናው ተወጥረናል። 
 • ስለዚህ የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያበቃል ማለት ነው፣ እንቅስቃሴያችንም በዚህ አግባብ መሆን አለበት። 
 • እንደዚያማ አይሆንም፣ ሌላ አካል ሊያራዝመው አይችልም?
 • ሌላ አካል ማራዘም አይችልም፣ ምናልባት በሌላ አካል አዲስ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መጣል ይቻላል፡፡
 • በማን ቢታወጅ ይሻላል?
 • የሚችለው ጊዜያዊ አስተዳደሩ ብቻ ነው፣ ቢሆንም ከሕግ አንፃር የሚኖረውን አንድምታ መመርመር አለብን።
 • እሱማ ማወጅ ይችላል፣ ለእኛም ጥሩ ነው።
 • ለእኛም ጥሩ ነው ሲሉ?
 • ፌዴራል ነው ያራዘመው የሚል ትችት አይመጣብንም።
 • እሱ እንኳን ያው ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • ያው ነው ማለት?
 • ጊዜያዊ አስተዳደሩ የተቋቋመው በፌዴራል መንግሥት ነው፣ ተጠሪነቱም ለፌዴራል ነው መባሉ አይቀርም ለማለት ነው።
 • ቢሆንም የተሻለ ነው፣ ቶሎ ተጠንቶ ይወሰን።
 • ጥሩ፣ አመሠግናለው ክቡር ሚኒስትር!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ ትርፍ ቢያገኝም የውጭ ምንዛሪ ገቢው ቅናሽ ማሳየቱ ተጠቆመ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2016 የሒሳብ ዓመት ያሰባሰበው የውጭ ምንዛሪ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የቅርብ ወዳጃቸው ከሆነች አንድ ባለሀብት የተደወለላቸውን ስልክ አንስተው በኮሪደር ልማቱ ላይ የምታቀርበውን ቅሬታ እየሰሙ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እኔ የኮሪደር ልማቱ ላይ ተቃውሞም ሆነ ጥላቻ እንደሌለኝ የሚያውቁ ይመስለኛል? በዚህ እንኳን አትታሚም።  የእውነቴን ነው ክቡር ሚኒስትር። አውቃለሁ ስልሽ? ለኮሪደር ልማቱ አዋጡ ሲባልም ያለማመንታት አምስት ሚሊዮን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ሳይገኝ ከቀረው አንድ የተቋማቸው ባልደረባ የሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ አባልን አስጠርተው እያናገሩ ነው]

ለምንድነው በዚህ አገራዊ ፋይዳ ባለው ፕሮግራም ላይ ያልተገኘኸው? ክቡር ሚኒስትር ህሊናዬ አልፈቀደልኝም። መቃወምና መተቸት ብቻ ውጤት የሚያመጣ መስልዎህ ከሆነ ተሳስተሃል። አልተሳሳትኩም ክቡር ሚኒስትር? ቆይ የመጀመሪያ ዓመት የችግኝ ተከላ...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላነጋግርህ የፈለኩት ክቡር ሚኒስትር፡፡ እርስዎማ ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግዎትም፣ ምን ገጠመዎት? እኔማ ምን ይገጥመኛል አንተኑ ልጠይቅህ እንጂ? ምን? እውነት ለመናገር የማየው ነገር አሳስቦኛል፡፡ ይንገሩኝ...