Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊበኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ከ270 ሺሕ በላይ አለፈ

  በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ከ270 ሺሕ በላይ አለፈ

  ቀን:

  ከ1.78 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የኮቪድ መከላከያ ተከትበዋል

  ‹‹በእጅዎ የነኩት ቁስ በኮቪድ-19 የተበከለ ሊሆን ይችላልና እጅዎን በተደጋጋሚ ያጽዱ›› የሚለው የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ነው፡፡

  ይህኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መስተጋብር ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተፅዕኖ ሳያንስ፣ እርስዎ በመዘናጋትም ሕይወትዎን እንዳያጡ አሊያም እንዳይታመሙና እንዳይሠቃዩ ልብ በሉ የሚል ጥሪ አለው፡፡

  በሌላ በኩልም ‹‹ኮቪድ-19 ዛሬም የብዙ ወገኖቻችንን ሕይወት እየቀጠፈ ሰልሚገኝ ራስዎን ከቫይረሱ ይጠብቁ!›› እያለ በየቀኑ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት የሚያሳስበው የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ከተከታታይ መልዕክቶቹ መካከል ‹‹በማንኛውም እንቅስቃሴዎ ጊዜ በኮቪድ-19 ሊያዙ ስለሚችሉ የመከላከያ መንገዶችን ሳይዘናጉ ይተግብሩ!›› የሚለውም ይገኝበታል፡፡

  ይሁን እንጂኢንስቲትዩቱግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ምሽት መረጃ እንደሚያሳየው፣ እስካሁን 4,127 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ለ2,706,146 ሰዎች በተደረገው የላቦራቶሪ ምርመራም 270,527 ሰዎች በበሽታው ሲያዙ፣ 234,426 ሰዎች አገግመዋል፡፡ 443 ሰዎች ደግሞ  በጽኑ ሲታመሙ፣ 31,972 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው አስታውቋል፡፡ የተከታቢዎች ቁጥርም 1,784,146 ደርሷል፡፡

  የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአሥር ክፍሎች የቀረበው መመርያ ውስጥ በስብሰባ፣ በቀብር ሥርዓት፣ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት፣ የአደባባይ በዓላት አከባበር ላይ ስለሚወሰዱ ጥንቃቄዎች የሚተነትን ይገኝበታል፡፡

  በሌላ በኩል መመርያውን መተግበር የማንኛውም ሰውና ተቋም ግዴታ ሲሆን በተደነገጉት ክልከላዎችና ግዴታዎችን የተላለፈ ሰው አግባብ ባለው የወንጀል ሕግ መሠረት ተጠያቂ እንደሚሆን ይጠቁማል፡፡

  ጥብቁ መመርያ እስከ ምን ድረስ ነው?

  የጤና ሚኒስቴር ባወጣው ጥብቅ መመርያ መሠረት ማንኛውም አገልግሎት የሚሰጥ የመንግሥታዊና የግል ተቋም አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ተቋሙ ለሚመጡ ተገልጋዮች ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ ተገልጋዮች ሁለት የአዋቂ ዕርምጃ ተራርቀው የሚቆሙበትን ቦታ ምልክት የማድረግና ተገልጋዮችም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውንና ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት በተቋሙ ላይ ተጥሏል፡፡

   የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ አሽከርካሪ፣ አገር አቀፍም ሆነ የከተማ ውስጥ ትራንስፖርትን በተመለከተ በሕግ ከተወሰነው የመጫን አቅም ልክ ሰዎችን የመጫን፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ያላደረጉ ሰዎችን አገልግሎት መስጠት እንደሌለበት መግለጫው አመልክቶ፣ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አሠሪዎች በተመለከተ በግንባታ ሳይቶች ላይ አስፈላጊውን ንጽህና ለመጠበቅ የሚረዱ እንደ ውኃ፣ ሳሙና፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ፣ ሳኒታይዘር ወይም አልኮል፣ የሙቀት መለኪያ መሣሪያ እንዲሁም የፀረ ተህዋሲያን ግብዓት የማሟላት ግዴታ እንዳለባቸው ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

  ተተኳሪ ጉዳዮች

  ኮቪድ-19 በወረርሽነት ዓለምን ካካለለሁለት ዓመት እልፍ ብሏል፡፡ በእነዚህ ወራት  የዓለም ሕዝብ ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠበቅ፣ ‹‹በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ›› እንዳይያዝ የጤና ባለሙያዎችና ዓለም አቀፋዊም ሆነ አገራዊ ተቋማት ማስገንዘቢያዎችን ከመስጠት ችላ ያሉበት ጊዜ አልነበረም፡፡

  ኮቪድ -19 ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል፡፡

  ኅብረተሰቡ በሽታው በቀላሉ የሚተላለፍ በመሆኑ ሳይዘናጋ ለተለያዩ ጉዳዮች በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተውና አካላዊ መራራቅን በመተግበር የበሽታውን ሥርጭት እንዲከላከል ኢንስቲትዩቱ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡

  ለዚህም የኮሮና ቫይረስ መከላከያን አራቱን ‹‹›› ሕጎች በመተግበር የበሽታውን ሥርጭት ሁሉም እንዲከላከልም ጥሪ አቅርቧል፡፡

  አራቱ ‹‹›› ሕጎች

  • መራራቅ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
  • መታጠብ እጅን በተደጋጋሚ በውኃና በሳሙና መታጠብ፣
  • መቆየት አስገዳጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት፣
  • መሸፈን ከቤታችን ወጥተን ስንንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም፡፡
  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...