Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢዜማ ገዥው ፓርቲ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እንቅፋት ነው አለ

ኢዜማ ገዥው ፓርቲ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እንቅፋት ነው አለ

ቀን:

የ2013 ምርጫ እንቅስቃሴን ተከትሎ ገዥው ፓርቲ ብልፅግና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እንቅፋት መሆኑን ቀጥሎበታል በማለት፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኤዚማ) በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ወቀሰ፡፡

ፓርቲው ይህንን ወቀሳ ወደ መንግሥት የሰነዘረው ሐሙስ ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ስታዲዮም አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤቱ፣ ‹‹ከፓርቲ ጥቅምና ፍላጎት የአገር ደኅንነትና ቀጣይነት ይቀድማል›› በሚል ርዕስ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

እስካሁን ኢዜማ ባደረጋቸው የምርጫ እንቅስቃሴዎችና አጠቃላይ ሒደቱ ላይ በርካታ ተግዳሮች እንዳጋጠሙት ከመግለጽ ባለፈ፣ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት እንደሚያነክስ ማስተዋሉንም ገልጿል፡፡

‹‹በተለይ አሁን ያለንበት የምርጫ ወቅት ብዙ ክፍተቶች ያሉበትና መንግሥትም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባበት ያለው ቁርጠኝነት አንካሳ መሆኑን ያስተዋልን ቢሆንም፣ አገራችን ከተደራረቡባት ዘርፈ ብዙ ችግሮች መላቀቅ የምትችለው በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት በመመሥረት መሆኑን በፅኑ እናምናለን፤›› በማለት፣ አሁንም በምርጫው ላይ ያለው ተስፋ ያልተሟጠጠ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ሆኖም ኢዜማ እየሄደበት ያለውና የሚያሳየው ‹‹ትዕግሥት›› እና ‹‹ኃላፊነት›› የተሞላበት አካሄድ በመንግሥት በኩል እንደ ደካማነት መቆጠሩን በመግለጽ፣ ‹‹በሥልጣን ላይ ለመቆየትና ምርጫውን እንደ ከዚህ በፊት የይስሙላ ቅቡልነትና ማራዘሚያ ለማድረግ የሚፈጽማቸውን እኩይ ተግባራት እያስተዋልን ነው፤›› በማለት የተቃውሞ ድምፁን አሰምቷል፡፡

የመራጮች ምዝገባ ከተጀመረበት መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. አንስቶ እስከተጠናቀቀበት ዕለት ድረስ በምዝገባ ሒደቱ ላይ የተለያዩ መስተጓጉሎች እንዳጋጠሙት የገለጸው ኢዜማ፣ ያጋጠሙትን ችግሮች ከመፍታት አንፃር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሄደበትን መንገድ አወድሷል፡፡

‹‹ለምርጫ ቦርድ ካሳወቅናቸው ችግሮች መካከል የተፈቱ ሲኖሩ፣ በምርጫ ቦርድ በኩል ተግዳሮቶቹን ለመፍታት በጎ የሚባሉ ጥረቶችን ስናይ ቆይተናል፤›› በማለት ውዳሴውን ችራል፡፡

ገዥው ፓርቲ በጥቂቱም ቢሆን ዴሞክራሲዊ ሥርዓት መመሥረት የሚያሳስበው ከሆነ፣ ‹‹ከአሁን በኋላ ከሚፈጽማቸው እኩይ ተግባራት እጁን እንዲሰበስብና የሚወሰዱ የዕርምት ዕርምጃዎች ካሉ ሙሉ ተባባሪ እንዲሆን እየጠየቅን፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በአገርና በሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ጉዳት እንደ ቀደሙ ገዥዎች የብልፅግና ፓርቲም ከታሪክ ተጠያቂነት አያመልጥም፤›› ብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...