Friday, June 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናብልፅግና መራጮችን በማዳበሪያና በምርጥ ዘር በማስፈራራትና ዕጩዎችን በማንገላታት ወቀሳ ቀረበበት

ብልፅግና መራጮችን በማዳበሪያና በምርጥ ዘር በማስፈራራትና ዕጩዎችን በማንገላታት ወቀሳ ቀረበበት

ቀን:

ብልፅግና የቀረበበትን ወቀሳ አስተባብሏል

እናት ፓርቲ  በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎችሰባሰብኩት ባለው መረጃ ብልፅግና ፓርቲ ሕዝቡ ካልመረጠው ማደበሪያና ምርጥ ዘር እንደማይቀርብለት በማስፈራራት፣ ዕጩዎችን ለእስርና አንግልት እየዳረገብኝ ነው ሲል ወቀሳ አቀረበ፡፡

 ፓርቲው ዓርብ ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ በበርካታ የአማራ፣ የደቡብ፣ የኦሮሚያ፣ የድሬዳዋ፣ የአዲስ አበባ፣ የቤንሻንጉል ጉምዝና ሐረር  የምርጫ ክልሎች በብልፅግና ፓርቲ ደረሱብኝ ያላቸውን በደሎች ለጋዜጠኞች ይፋ አድርጓል፡፡

- Advertisement -

ብልፅግና ፓርቲ መራጮችን ‹‹አምፖልን ካልመረጣችሁ ትታሰራላችሁ፣ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር አታገኙም›› በማለት ማንገራገርና ማስፈራራት እያካሄደ እንደሆነ፣ የእናት ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሰይፈ ሥላሴ አያሌው (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ለአብነት በአማራ ክልል ኮሶ በር ምርጫ ክልል ሕዝቡ ብልፅግናን እንዲመርጥ በቃለ ጉባዔ ማስፈረም፣ የብልፅግና የምርጫ ምልክቱን ቤተ እምነት በር ላይ መለጠፍ፣ በእንጅባራ ለ12 ቀናት መራጮች እንዳይመዘገቡ ‹‹ከንቲባ ቦታ አልፈቀደም›› በማለት የምርጫ ጣቢያ እንዳይከፈት ተደርጓል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

 በሌላ በኩል በአማራ ክልል ዚገም ወረዳ በእናት ፓርቲ አባላት ላይ በሽጉጥ የመግደል ሙከራ ማድረግ፣ በግምጃ ቤት ምርጫ ክልል የእናት ፓርቲ አባላት ቅስቀሳ ሲያደርጉ ሾፌሩን እስከ ረዳታቸው ለምን ቀሰቀሳችሁ በማለት ለእስራት መዳረጋቸውን፣ እንዲሁም ብልፅግና ፓርቲ በትምህርት ቤትና እምነት ተቋማት የምረጡኝ ቅስቀሳ ማድረጉን እናት ፓርቲ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

  እንዲሁም የገጠር የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን ‹‹ብልፅግናን ካልመረጣችሁን ትሰረዛላችሁ፣ የምርጫ ካርድ የሚሰጠው ለብልፅግና አባል ነው›› በማለት ማስፈራራት፣ ምርጫ ጣቢያ ካርድ ለማውጣት ሰዎች ሲሄዱ ብልፅግናን ነው መምረጥ ያለባችሁ እየተባሉ እንዲገደዱ መደረጉ ተገልጿል፡፡

 በተመሳሳይ ምርጫ ጣቢያ ላይ ካርድ ለማውጣት ሰዎች ሲሄዱ ‹‹ብልፅግናን ነው መምረጥ ያለባችሁ›› እያሉ ማስጨነቅ፣ ካርዱን ወስደው ቀበሌ ሕፈት ቤት መቆለፍ፣ ቤት ለቤት እየሄዱ ለሚፈልጉት ሰው ካርድ መስጠት፣ጎንደር አዘዞ ካርድ ያለ ምዝገባ ለብልፅግና ደጋፊዎች ለሆኑ ብቻ ሲሰጡ እንደነበር ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡

 በሌላ በኩል በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን (አርባ ምንጭና አካባቢው) ካርድ የሚሰጠው ለብልፅግና ፓርቲ አባል ነው፣ ለሌላ ፓርቲ አባል አንሰጥም እያሉ ማስፈራራት፣ በወላይታ የቀበሌው ሊቀመንበር በቦታው ላይ ተቀምጠው ‹‹ከብልፅግና ውጪ ብትመርጡ ነግሬያችኋለሁ›› በማለት ያስፈራሩ እንደነበርና ሰዎችን በሠፈር በማደራጀት የራሳቸው መራጮች ብቻ እንዲወስዱ ማድረግ የሚሉ ክሶች በብልፅግና ፓርቲ ላይ ቀርበውበታል፡፡

እናት ፓርቲ ያቀረበውን ክስ አስመልክቶ የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግኙነት ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በስልክ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ፓርቲያቸው ሕዝቡን በማዳበሪያና በምርጥ ዘር እያስፈራራ ነው ተብሎ የቀረበው ክስ ፈጽሞ ውሸት ነው ብለዋል፡፡

ኃላፊው ብልፅግና ፓርቲ በምንም ዓይነት ተዓምር እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት እንደማይፈጽም በማስታወቅ፣ ከ47 ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ሲወዳዳር በፖሊሲ፣ በአሠራር፣ በመመርያና በአስተሳሰብ ማንም አጠገቡ የሚደርስ ፓርቲ የለም ብለዋል፡፡ ‹‹በማዳበሪያና በምርጥ ዘር እያስፈራሩ እያሉ የሚወቅሱ ፓርቲዎች ሐሳብ ያጠራቸው ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ይህ ዓይነቱ ድርጊት በብልፅግና ፓርቲ ዘመን የሚታሰብ አይደለም፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም ከዕጩዎች ጋር በተገናኘ የሚነሱ ሌሎች ቅሬታዎችን ግን አሠራሩን ጠብቀው ለምርጫ ቦርድ ማቅረብ ይችላሉ ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...