Thursday, July 25, 2024

[ክቡር ሚኒስትሩ አሜሪካ የጣለችው ማዕቀብ በፓርቲያቸው ከፍተኛ አመራሮች ላይ የፈጠረው ቁጭት እንዲገመገም ባዘዙት መሠረት፣ የፖለቲካ ጉዳይ አማካሪያቸው የግምገማ ሪፖርቱን ይዞ ውይይት እያደረጉበት ነው] 

 • ክቡር ሚኒስትር ባዘዙት መሠረት በፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ላይ የተደረገውግምገማ ውጤት ደርሷል።
 • በጣም ጥሩ፣ በጥቅሉ ማዕቀቡ የፈጠረባቸው ስሜት ምን ይመስላል?
 • ግምገማው የሚያሳየው አመራሩ የተደበላለቀ ስሜትና መረጃ እንዳለው ነው።
 • ምን ማለት ነው?
 • ገሚሱ አመራሮች ማዕቀብ ስለመጣሉ ካለማወቃቸው ባለፈ ባሉበት አካባቢ ማኅበረሰብንም ሲያደናግሩ ነበር።
 • ምን ብለው ነው የሚያደናግሩት?
 • አክቲቪስቶች የሚያሠራጩት ሐሰተኛ መረጃ ነው እያሉ ነዋ። 
 • ሌሎቹ አመራሮችስ ምን እያለ ነው?
 • ሌሎቹ በተለይም ከፍተኛ አመራሮች ማዕቀብ ስለመጣሉ መረጃ ቢኖራቸውም፣ የተረዱበት መንገድ ግን የተሳሳተ ነው።
 • የተሳሳተ ነው ማለት?
 • የጉዞ ማዕቀብ የተጣለው በአገር ላይ ሆኖ ሳለ፣ ማዕቀቡ እኔን አይመለከትም የሚል ግንዛቤና ሐሳብ በስፋት ሲያራምዱ ተስተውለዋል።
 • እኔን አይመለከትም ሲሉ ምን ማለታቸው ነው?
 • የአገር ውስጥ ጉዞ ለማድረግ ቪዛ አያስፈልገንምየጉዞ ማዕቀቡ እኛን አይመለከትም የሚል ሐሳብ ሲያራምዱ ነበር።
 • ፈጽሞ ሊሆን አይችልም፡፡
 • ከመሠረታዊ የዲፕሎማሲ ዕውቀት የሚቃረን ቢሆንም ሆኗል ክቡር ሚኒስትር።
 • ይህንን መታገስ ይከብዳልበፍጥነት አንድ ነገር መደረግ አለበት።
 • ምን ይደረግ ክቡር ሚኒስትር?
 • እንዲህ ዓይነት ሐሳብ ሲያራምዱ የነበሩ አመራሮች ተለይተው እንዲመደቡ ይደረግ!
 • የት ይመደቡ ክቡር ሚኒስትር?
 • አምባሳደርነት ይመደቡ!
 • ምን አሉኝ ክቡር ሚኒስትር!?
 • በውጭ ሚሲዮኖቻችን በአምባሳደርነት ይመደቡ፡፡ 
 • እኔም እንደዚያ መደረግ አለበት ብዬ እያሰብኩ ነበርዲፕሎማሲን በተግባር መማር አለባቸው…

[ክቡር ሚኒስትሩ ምርጫውን የተመለከቱ ዕለታዊ ክስተቶችና መረጃዎች እየቀረቡላቸው ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር አንዳንድ ፓርቲዎች ምርጫው እየተቃረበ ሲመጣ የማፈንገጥ አዝማሚያ ማሳየት ጀምረዋል።
 • የማፈንገጥ አዝማሚያ ማለት?
 • በድንገት ብድግ ብለው የእኛን ፓርቲ ማውገዝና ማስፈራራት ጀምረዋል።
 • ማስፈራራት ማለት?
 • በደል እየተፈጸመባቸው እንደሆነና በዚህም ምክንያት በምርጫው ላይሳተፉ እንደሚችሉ የማስፈራሪያ መግለጫ ያወጡ አሉ።
 • እሺ ሌሎቹስ?
 • አንዳንዶቹ ደግሞ ሥልጣን ላይ ያለው ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ፍላጎት እንደሌለውና ምርጫውን ሥልጣኑን ለማራዘም ብቻ እንደሚፈልገው እየገለጹ ነው።
 • የትኞቹ ፓርቲዎች ናቸው?
 • ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ያግዙናል ብለን ያመንባቸውና የደገፍናቸው ፓርቲዎች ናቸው። 
 • እንዴት የአቋም ለውጥ ሊያደርጉ እንደቻሉ የሚታወቅ ነገር አለ?
 • ጫናው የፈጠረው ተስፋ መቁረጥ ይመስለኛል፡፡ 
 • የቱ ጫና?
 • የጉዞና የዕርዳታ ማዕቀቡ ተስፋ አስቆርጧቸው፣ ወይም ከዚህ ሁኔታ ጋር ራሳቸውን ላለማዛመድ ሊሆን ይችላል። 
 • እንዴት?
 • ከአሜሪካ ጋር ተቆራርጦ ሥልጣን መያዝ አደጋ አለው ብለው ሳይሠጉ አይቀርም፣ ስለዚህ የምርጫ ሒደቱን በመንቀፍ የአሜሪካን ማዕቀብ አንቃወምም የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ሳይሆን አይቀርም።
 • ነው እንጂ፣ ልክ ነህ፣ እንዲያውም እነሱ ሳይሆኑ አይቀርም መግለጫ እንዲያወጡ የገፋፏቸው። 
 • እነ ማን?
 • አሜሪካኖቹ ወይም አውሮፓዎቹ። 
 • ለነገሩ ቢሠጉ አይፈረድባቸውም። 
 • እንዴት?
 • ሥልጣን ቢያገኙም ይህንን ሁኔታ ለማለፍ የሚያስችል አቅምም ሆነ ብልኃቱ የላቸውም። 
 • ስለዚህ የሚያስጨንቅ ጉዳይ አይደለም እያልክ ነው? 
 • ነገሩማ ያስጨንቃል፣ ምክንያቱም እነሱ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም በድንገት የማበር አዝማሚያ እያሳዩ በመሆኑ ጀርባቸው መጠናት አለበት።
 • የትኞቹ ናቸው የማበር አዝማሚያ ያሳዩት?
 • በእስር ላይ የሚገኙ የማይተዋወቁ ፖለቲከኞች። 
 • ምን አደረጉ?
 • የረሃብ ዓድማ እናደርጋለን እያሉ ነው።
 • በምን ምክንያት 
 • በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እንቃወማለን ነው የሚሉት፣ ከዚህ በተጨማሪም ሌላ ጥያቄ አንስተዋል።
 • ምን ጥያቄ አነሱ?
 • ፍርድ ቤቱ ጉዳያቸውን ለጊዜው እንዲያቋርጥና ምርጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ማየት እንዲጀምር እየጠየቁ ነው።
 • ፍርድ ቤቱን ከምርጫ ጋር ምን አገናኘው? መንግሥት ሲቀየር ፍርድ ቤት አይቀየር? ከጥያቄው ጀርባ ምንድነው ያለው?
 • እንደሚመስለኝ ከሆነ ከምርጫ በፊት በፖለቲካ ውሳኔ እንደሚፈቱ አስበው ያቀረቡት ጥያቄ ነው። 
 • በፖለቲካዊ ውሳኔ ማን ይፈታቸዋል? ቢፈቱስ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ማንሳት ለምን አስፈለገ?
 • በአንድ ምክንያት ይመስለኛል። 
 • ምንድነው? 
 • ምክንያቱ ፍርድ ተሰጥቶ በፖለቲካዊ ውሳኔ በመፈታትና ሳይፈረድ በፖለቲካ ውሳኔ በመፈታት መካከል ጠቃሚውን ለመምረጥ ይመስለኛል።
 • በፖለቲካ ውሳኔም ሆነ በሌላ መፈታት መፈታት ያው ነው፣ ምን ልዩነት ይኖረዋል?
 • ልዩነት የሚያመጣው የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ነው።
 • እንዴት ማለት?
 • ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ አይደሉም ብሎ ከወሰነ በኋላ በፖለቲካ ውሳኔ መፈታት ያውና ያው ነው።
 • ጥፋተኛ ብሎ ቢወስንስ?
 • ጥፋተኛ ብሎ ከወሰነና የቅጣት ፍርድ ከሰጠ በኋላ በፖለቲካ ውሳኔ መለቀቅ ግን እንደ መለቀቅ አይቆጥርም።
 • ታዲያ እንደምን ሊቆጠር ነው?
 • በረዥም ገመድ ታስሮ እንደ መለቀቅ ነው።
 • አሃ… አሁን ገባኝ፣ እንዲመስለው አትለኝም እንዴ ታዲያ?
 • እንዲመስለው?
 • አዎ፣ ሁለተኛው አለቃቀቅን እንዲመስለው ብለን ነው እኛ የምንጥራው። 
 • ምን ማለት ነው?
 • የተፈታ እንዲመስለው አድርገህ እሰረው!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...

ግለሰብ ነጋዴዎችን በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ለማድረግ ያለመው ረቂቅ አዋጅ ተከለሰ

በምትኩ የንግድ ተቋማት በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ። ይህንን ደብዳቤ እየውና በጠየቁት መሠረት እንዲፈጸምላቸው አድርግ። ጉዳዩ ምንድነው? ከአንድ ክልል የቀረበ የትብብርና ድጋፍ ጥያቄ ነው። የምን ትብብር...

[ክቡር ሚኒስትሩ የቅርብ ወዳጃቸው ከሆነች አንድ ባለሀብት የተደወለላቸውን ስልክ አንስተው በኮሪደር ልማቱ ላይ የምታቀርበውን ቅሬታ እየሰሙ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እኔ የኮሪደር ልማቱ ላይ ተቃውሞም ሆነ ጥላቻ እንደሌለኝ የሚያውቁ ይመስለኛል? በዚህ እንኳን አትታሚም።  የእውነቴን ነው ክቡር ሚኒስትር። አውቃለሁ ስልሽ? ለኮሪደር ልማቱ አዋጡ ሲባልም ያለማመንታት አምስት ሚሊዮን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ሳይገኝ ከቀረው አንድ የተቋማቸው ባልደረባ የሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ አባልን አስጠርተው እያናገሩ ነው]

ለምንድነው በዚህ አገራዊ ፋይዳ ባለው ፕሮግራም ላይ ያልተገኘኸው? ክቡር ሚኒስትር ህሊናዬ አልፈቀደልኝም። መቃወምና መተቸት ብቻ ውጤት የሚያመጣ መስልዎህ ከሆነ ተሳስተሃል። አልተሳሳትኩም ክቡር ሚኒስትር? ቆይ የመጀመሪያ ዓመት የችግኝ ተከላ...