Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየኦሮሚያ ልማት ማኅበር ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የልማት ሥራዎችን ማከናወኑን...

የኦሮሚያ ልማት ማኅበር ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የልማት ሥራዎችን ማከናወኑን አስታወቀ

ቀን:

ማኅበሩ 50 ሺሒ ካሬ ሜትር መሬት ከከተማ አስተዳደሩ ተረክቧል

የኦሮሚያ ልማት ማኅበር በተለያዩ የክልሉ ሥፍራዎች ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን የልማት ሥራዎች መሥራቱን አስታወቀ፡፡ ዓርብ ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ዓመታዊ ኮንፍረንሱን ባጠቃለለበት መርሐ ግብር፣ ዘንድሮ ብቻ 300 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡንና ከ55 ሺሒ በላይ አባላት መመዝገቡን ገልጿል፡፡

ማኅበሩ ባለፉት 28 ዓመታት ከ4,135 በላይ የልማት ፕሮጀክቶቸን ከአሥር በሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ማከናወኑን ያስታወቁት የኦሮሚያ ልማት ማኅበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ኢቲቻ 874 ትምህርት ቤቶች፣ የተለያዩ መንገዶችና 2,000 የውኃ ፕሮጀክቶች መገንባታቸውን፣ በዚህም 26 ሚሊዮን ያህል የክልሉ ሕዝብ ተጠቃሚ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ማኅበሩ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን 700 ተማሪዎችም እያሠለጠነ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የልማት ማኅበሩ በተለይ በአዲስ አበባ ሊገነባ ላቀደው ሕንፃና የተለያዩ የልማት ሥራዎች፣ 50 ሺሕ ካሬ ሜትር መሬት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተረክቧል፡፡ ቀደም ብሎ የተለያዩ ልማታዊ ሥራዎችን ለማከናወን የግንባታ ዲዛይኖችን ለከተማ አስተዳደሩ ማስገባቱን፣ በተረከበው መሬት የመኖሪያ ቤቶች፣ የባህል ማዕከል፣ የመዝናኛ ሥፍራ፣ እንዲሁም ግዙፍ የመኪና ማቆሚያ ለመገንባት ማቀዱን ገልጸዋል፡፡

ማኅበሩ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች የተጀመሩ መሠረተ ልማቶች ቢኖሩም፣ አብዛኛው የገጠሩ ኅብረተሰብ በመሠረተ ልማት ዕጦት ምክንያት ከፍተኛ ችግር ውስጥ በመግባቱ ሳቢያ ክፍተቶችን ለመድፈን በ1985 ዓ.ም. የተመሠረተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተለይ በገጠር የሚኖሩ እናቶች የጤና ተቋማት በማጣታቸው ሳቢያ በወሊድ ጊዜ እየተቸገሩና ሕፃናት እየሞቱ መቆየታቸውን፣ በንፁህ የመጠጥ ውኃ ዕጦት ምክንያት ለተለያዩ በሽታዎች በመጋለጣቸው ምክንያት፣ በክልሉ በሚኖረው ሕዝብ የተቋቋመ የልማት ማኅበር መሆኑን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

ማኅበሩ በኦሮሚያ ክልል 7.1 ሚሊዮን አባላት ሲኖሩት፣ ገቢያቸውን ከግምት በማስገባት ለማኅበሩ ገቢ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡ በቀጣይ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለማስፋፋት፣ የተገነቡና በቀጣይ የሚገነቡ ትምህርት ተቋማትን ወደ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ለማሳደግ ግብ አድርጎ እየሠራ መሆኑን፣ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የሚገኘውን ኦዳ የቴክኖሎጂና የሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያ የግንባታ ምዕራፍ ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...