Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየዘገየው የአዲስ አበባ ስታዲየም ዕድሳት

የዘገየው የአዲስ አበባ ስታዲየም ዕድሳት

ቀን:

የአዲስ አበባ ስታዲየም ለበርካታ አሠርታት የተለያዩ ሁነቶች ማዕከል ሆኖ ቆይቷል፡፡ ስታዲየሙ አገሪቱ አለኝ የምትለው ሁነኛ የስፖርት ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የተለያዩ አገራዊና ሃይማኖታዊ፣ እንዲሁም ባህላዊ ክንዋኔዎች ሲስተናገዱበት ቆይቷል፡፡ ይሁንና ስታዲየሙ ለታለመለት ዋና ዓላማ ስፖርታዊ ክንውኖች ብቁ ከመሆን ይልቅ የጥራቱ ጉዳይ እያሽቆለቆለ ደረጃው እየወረደ ብሎም ምቹ ወደ አለመሆን እየተንሸራተተ እነሆ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ ከሜዳው ምቹነት መጓደል እስከ ፅዳት አለመኖር ያሉ መሰል ችግሮች የስታዲየሙ መገለጫዎች ከሆኑ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

በዚህም ሳቢያ በኢትዮጵያ በስም ብቻ ስታዲየም የሚለውን ስያሜ ይዞ፣ ነገር ግን ምቹ ካልሆኑ ስታዲየሞች ተርታ በመመደቡ በዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን ማስተናገድ እንዳይችል ከሁለት ዓመት በፊት ዕግድ የጣለበት መሆኑ አይዘነጋም፡፡ በዚህ የተደናገጠ የሚመስለው ስፖርቱን በበላይነት እንዲያስተዳድር ኃላፊነት የተጣለበት መንግሥታዊው አካል ስታዲየሙ እንዲታደስ ውሳኔ ላይ ከደረሰ ሰነባብቷል፡፡

ይህ አካል ዘግይቶም ቢሆን ስታዲየሙ እንዲታደስ ወስኖ የተጫራቾችን የጨረታ ሰነድ ከሰሞኑ ከፍቶ የዝርዝሩን ቅደም ተከተል ይፋ አድርጓል፡፡ ሆኖም ግን መዘግየቱ በብዙዎች ዘንድ ግርታ የፈጠረ ከመሆኑ ባሻገር ዕውን መንግሥት ለዚህ ታሪካዊ ሥፍራ ትኩረት መስጠት እንደምን ተስኖት ቆየ የሚል ጥያቄ ጭሮ መቆየቱ ግን አልቀረም፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ስታዲየሙን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ስፖርት ኮሚሽን በበኩሉ፣ የአዲስ አበባ ስታዲየምን ለማደስና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ለማድረግ አማካሪ ድርጅት በመለየት አጠቃላይ የስታዲየሙን ዲዛይን ሲያስጠና መቆየቱ ይገልጻል፡፡

ኮሚሽኑ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስነበበው ከሆነ፣ ጥናቱን መነሻ ማድረግ በተሠራው ዲዛይን መሠረት በቅድሚያ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በሰጠው አስተያየት መሠረት ዕድሳት ለማድረግ ለግንባታ ተቋራጮች ጨረታ አውጥቷል፡፡ ዕድሳቱ በዋናነት የመጫወቻ ሜዳው፣ የመልበሻና የመታጠቢያ ክፍሎች፣ የተመልካቾች መፀዳጃ ቤቶች፣ የኤሌክትሪክና የሳኒተሪ ሥራዎችን የሚያካትት ይሆናል፡፡

ስታዲየሙን ለማደስ በአጠቃላይ ስምንት ድርጅቶች በጨረታው መሳተፋቸውን የገለጸው የኮሚሽኑ መግለጫ፣ ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ ድርጅቶች ቴክኒካል ግምገማውን በማለፋቸው ዕድሳቱን ለማደስ ያስገቡት የጨረታ ሰነድ ተከፍቶ መታየቱ ተናግሯል፡፡

በቀረበው ፋይናንስ ሰነድ መሠረት ፍሬንድስ ኢንጅነሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ 34,644,748.93 ዕድሳቱን ለማደስ ያቀረበው ዋጋ የመጀመርያው ሲሆን፣ ሁለተኛውና በሬቻ ፊጣ ሕንፃ ሥራ ተቋራጭ 50,336,995.69 ብር ዋጋና ቢጂኤም ኮንስትራክሽን 54,929,226.43 ብር ዋጋ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በዚሁ መሠረት እያንዳንዱ ድርጅት ያቀረቡት የዋጋ ግምቶች የሒሳብ ስህተት መኖር አለመኖሩ በአማካሪ ድርጅቶቹ ተፈትሾ ከተረጋገጠ በኋላ፣ ዝቅተኛ ዋጋ ካቀረበው   ድርጅት ጋር ውል በመዋዋል በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ የሚገባ ስለመሆኑ ጭምር በመግለጫው ተካቷል፡፡ የዕድሳት ሥራው በተሠራው ዲዛይን መሠረት የሚቀጥል ሲሆን የሚዲያ ክፍሎች፣ የክብር ትሪቡን መቀመጫ፣ የወንበር ገጠማና ሌሎች የስዲታየሙ ክፍሎችን በማደስ ለአገልግሎት ምቹ እንደሚደረግ ተነግሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...