Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  የሳምንቱ ገጠመኝየሳምንቱ ገጠመኝ

  የሳምንቱ ገጠመኝ

  ቀን:

  የሰውን ልብ በበጎ አሳምሮ በደንብ መንካት የሚያፈራው ፍሬ ታላቅ ነው። ስቲቭ ጆብስ ከወዳጆቹ ጋር የሰውን ልብ ለመንካት የተጠቀመባት መሣሪያ ትንሽ ነበረች። ያቺ ልብ መንኪያ መሣሪያ በኪስ ውስጥ ልትገባ የምትችለዋ “IPod” ነበረች።

  ጆብስ “IPod” ሲያስተዋውቅሺሕ ሙዚቃ በኪስ ውስጥ” (A thousand music in your pocket) ነበር ያለው። በአንድ ዓረፍተ ነገር የብዙዎችን ልብ መንኪያ መሣሪያ አስተዋውቆ ለገበያ አወጣ። ከዚያ በኋላ ያለውን ማውራት ታሪክ ማንዛዛት ይሆናል።

  የሚገርመው ግን ጆብስ የሌሎችን ልብ በበጎ ጎን ለመንካት የሚያስችለውን መሣሪያ የፈለሰፈው፣ እሱ ራሱ ልቡ በሌሎች ከተሰበረ በኋላ ነው። ጆብስ፣ ጆን ስከሊ የተባለውን የፔፕሲ ሥራ አስኪያጅ አብሮት እንዲሠራ ወደ አፕል አመጣው።

  ሆኖም ስከሊ ከቦርዱ ጋር ሆኖ ጆብስን ከመሠረተው ኩባንያ እንዲባረር አደረገው። ኩባንያ ብትመሠርትም የአክሲዮን ድርሻህ በሌሎች ከተበለጠ በድምፅ ብልጫ ተሸንፈህ ልትባረር ትችላለህ። ጆብስ ላይ የሆነው እንደዚያ ነው። በእኛም አገር ተመሳሳይ ሁኔታ የገጠማቸው ሰዎች አውቃለሁ።

  ቁምገሩ ሰዎች ሊያስቀይሙህና ልብህን ሊሰብሩ ቢችሉም፣ ከዚያ ስሜት ውስጥ ተስፈንጥረህ ወጥተህ በአዲስ ሐሳብ የሰዎችን ልብ ሊያረሰርስ የሚችል ነገር ሥራ። አትቆዝም፡፡

  ጆብስ ከዚያ በኋላ ያሉትን ታሪካዊዎቹን እነ “IPhone, IPad, IMac” መሥራቱን ልብ በል። ሰው ካለፈ በመጪው ዓመት ጥቅምት 10 ቀን ዓመት ይሆነዋል። ጆብስ በሕይወት ቢኖር ስንት አስደናቂ ምርቶች እናይ ነበር።

  በምግብ ራስን የመቻል ዕርምጃ ከአፈር እንክብካቤ ይጀምራል ይባላል። አባባሉ እውነት ቢሆንም በምግብ ራስን መቻል ለአፈር እንክብካቤ ማዳበሪያ ከመጨመር የዘለለ መሆኑ የግብርና ባለሙያ መሆን አይጠይቅም። 40 ዓመታት የማዳበሪያ አጠቃቀም ልምዳችንና ውጤቱን መታዘብ ብቻ ይበቃል።

  አፈር ለተክል የሚሰጠው በውስጡ ያለውን ንጥረ ነገር ነው። አፈሩ ያለው ገንቢ ይሁን መርዛማ ንጥረነገር ካለው ከፍሎ ይሰጣል። ውጤቱም እንደግብዓቱ ተክሉን ገንቢ አለያም ገዳይ ይሆናል። ተክሉም ያገኘውን ንጥረ ነገር ወደ ምግብ ይቀይርልናል።

  ለሰውነት ጤንነት ምግብ ያስፈልጋል፣ ሰውነት ሲታመም ደግሞ መድኃኒት፣ አንዳንዴም ተጨማሪ ቫይታሚንና ማዕድናት ይሰጠዋል። ይህ ከመደረጉ በፊት ግን የሰውነት ጤና ምርመራን ቀድሞ ማወቅ እና ተስማሚ ምግብን መምረጥ ያስፈልጋል። ለአፈርም ይህንን ማድረግ ይገባል። ለዚህ የአፈሩ ኬሚስትሪን ቀድሞ ማወቅና የጎደለውን መሙላት ይጠይቃል።

  የአገራችን አፈር ሁሉ አንድ ዓይነት አይደለም። ለዚህ የ”Soil Map” ማየት ይጠይቃል። አፈሩ ምን ጎደለው? ፖታሽየም፣ ፎስፎረስ፣ ሰልፈር ወይንስ ሌላ? አፈሩ አሲዳማ ነው ወይንስ ሌላ? ናይትሮጅንን ከአየር የሚስቡልን ባክቴሪያዎች አፈሩ ውስጥ አሉ ወይንስ በተደጋጋሚ በማዳበሪያነት በጨመርናቸው አሲዶች አካባቢያቸው ተቀይሮ ጠፍተዋል?

  የግብርና ሚኒስቴር ውስጥ ያሉ የግብርና ባለሙያዎች ለዘመናት “Soil Map” በእጃቸው ሳይኖር ስለግብርና ምርት መጨመር ስልት ሲያወሩን ስንሰማ ከርመናል። ይህ አሳዛኝ ነው። አጥጋቢ ውጤትም አላገኘንበትም።

  ህንድና ብራዚል ይህንን የግብርና ምርት እጥረት ችግር እንዴት ፈቱት? የሚለውን መፈተሽ ይገባል። ህንድ የአረንጓዴ አብዮት ዘመቻዋ በግለሰብ የተመራ ነው። ብራዚል ለምርት አይስማማም የተባለ መሬትን የአኩሪ አተር አምርታበት፣ ከዓለም ቁንጮ አኩሪ አተር አምራቾች ተርታ በመሠለፍ አሜሪካን በዓለም ገበያ ትገዳደራለች።

  የግብርና ሚኒስቴርና ውስጡ ያሉት ባለሙያዎች ከዚህ ልምድ መማር እንዴት አቃታቸው? ምግባችን ጤናማ እንዲሆን የምግቡ መነሻ አፈርና ውኃ የሚፈለገውን ንጥረ ነገር የያዘና ጤናማ ሊሆን ግድ ነው።

  ለመሆኑ የብዙ ኢንዱስትሪዎች ቆሻሻ ማስወገጃ በሆነው በአቃቂ ወንዝ የተመረተ ሰላጣ ምን ያህል ጤናማ ይሆናል? አትክልት ተራ ገበያ ላይ የሚቀርበው ሰላጣና ሽንኩርት በውስጡ ያለው የ”Heavy Metals Load” እና ተህዋስያን ደረጃ በአካባቢ ጥበቃ ይሁን በጥራትና ደረጃዎች ድርጅት ለመፈተሽ ለምን አልተቻለም?

  በሆላንዶቹ የተቋቋመው ብሾፍቱ ያለው የጀነሲስ እርሻ ጣቢያ ከጉድጓድ ውኃ ጤናማ ሰላጣ ማምረት ከቻለ፣ ሌሎች ገበሬዎቻችን እንዲያ ማድረግ ለምን ተሳናቸው? መርቲ ላይ በጃንሆይ ዘመን የተሠራውን የቦይ/ካናል መስኖ ኢራኖችና ቤልጂየሞች ሲጠቀሙበት የእኛ ሰዎች ለምን አልተጠቀሙበትም? ውኃ ለመጠጥ ችግር መሆኑ ቢታወቅም፣ ይህንን የጉድጓድ ውኃና የካናል ዝርጋታ ልምድ እንዴት ወደኛ ማሸጋገር አቃተን?

  ዓይን ካልተከፈተ ችግር ነው። ዓይን ለመክፍት ግን በከበርቻቻ ዳንኪራ ለሚባክን ጊዜ የግብርናው አመራሮች ጊዜ ወስደው ህዝቡ አውቆ እስኪገባው ማስተማር ነበረባቸው። የኢጣልያ ተራድኦ ድርጅት በበለስ ወንዝ ላይ ተሠርቶ የነበረው የጣናበለስ ፕሮጀክት በሦስት ዓመት ውስጥ ካስመዘገበው ውጤት እንዴት ልምድ መውሰድ አቃተን?

  ማዳበሪያ አምጥቶ በማከፋፈል ብቻ የኢትዮጵያን የእርሻ ምርት ለማሻሻል ሲሞከር 40 ዓመት አለፈው።መሬቱም እንደ ሰው ጉቦ ለመደከማለት ያለፈ ጠብ ያለ ጭማሪ አላየንም።

  አንድ ነገር ተሞክሮ ውጤት ካላመጣ ሌላ አማራጭ ማየት ስለምን ያቅተናል? አዲስ ነገር መፍጠር ቢያቅተን ከሌሎች መማር እንዴት ያቅተናል? ውጭ አገር ሄደን ያየነው ባይገባን፣ አንብበን ባይገባን ፈረንጆቹ እዚህ በራሳችን ሜዳ መጥተው የሠሩትን ዓይተን መረዳት እንዴት ያቅተናል?

  ፖለቲካ ጥቂቶችን ቢያበላ እንጂ ሁሉን አይመግብም። ሁሉን መመገብ የሚችለው ምርታማነት መጨመር ነው። ምርታማነትን የማሳደጊያ መንገዱ እንደ ነፈዝ ተመሳሳይ ድርጊትን እየሠሩ የተለየ ውጤት በመጠበቅ አይደለም።

  ምርታማነትን ለማሳደግ የ”PDCA” የዕድገት ማሻሻያ ሞዴል መጠቀም ነው (PDCA – Plan Do Check Adjust)::

  እንዲያው ግን ያየንውን ለመድገም ለምን ከበደን? ኧረ ዓይናችን ይከፈት:: ከሁሉ በፊት ትክክለኛ አመራር በቦታው ይቀመጥ። አመራርን በጥበብ ቀይሮ ካድሬን ወደ ፖለቲካ ሕፈት ቤት አዛውሮ አገርን ለመመገብ መትጋት ያሻል።

  (ቱጌ. ጂ. ከበደ በፌስቡክ ገጹ እንዳሠፈረው)

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...