Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአዲስ አበባ የሚሠሩ ቤቶች ለተለያዩ አደጋዎች ተጋላጭ መሆናቸው ተነገረ

በአዲስ አበባ የሚሠሩ ቤቶች ለተለያዩ አደጋዎች ተጋላጭ መሆናቸው ተነገረ

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ ከሚሠሩ ቤቶች 80 በመቶ ያህሉ ለአደጋዎች ተጋላጭ መሆናቻውን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

አብዛኞቹ በከተማዋ የሚገኙ ቤቶች አደጋን የመቋቋም አቅማቸው አሁን ባሉበት ደረጃ ዝቅተኛ መሆኑ ጥናት ቀርቧል፡፡ ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶች 20 በመቶ ብቻ መሆናቸውን ማክሰኞ ሰኔ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ኮሚሽኑ ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ላደረገው ውይይት ባቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ ጠቁሟል፡፡

ጥናቱ በ50,000 እና በ150,000 ኮንዶሚኒየሞች፣ በማኅበራት ቤቶችና በሌሎች የመንግሥትና የግል ቤቶች ላይ መሠራቱን፣ የእሳት አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን የቴክኒክ አማካሪ አቶ ጥላሁን ቶላ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ለቤቶቹ ተጋላጭነት ችግሮች መሠረታዊ መነሻዎች ሦስት መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ጥላሁን፣ እነሱም ቤት አሠሪዎች የአደጋ መከላከልን ግንዛቤ ውስጥ አለማስገባታቸው፣ የባለሙያዎችና የግንባታ ጥራት ችግሮች ናቸው፡፡

በተለይ ቤቶች ሲሠሩ እሳት፣ ጎርፍና መሰል አደጋዎችን መቋቋም እንዲችሉ ግብዓቶችን አለመጠቀምና ችላ ባይነት ምክንያቶች መሆናቸውን አቶ ጥላሁን ጠቁመዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከሚሠሩት ቤቶች አብዛኞቹ ከጭቃ፣ ከእንጨትና የተወሰኑት ከብሎኬት፣ እንዲሁም አልፎ አልፎ ከጡብ የሚገነቡ እንዳሉ አቶ ጥላሁን አስረድተዋል፡፡

የእሳት አደጋዎችን ለመቋቋም ከጡብ የሚሠሩ ቤቶች የተሻሉ ቢሆኑም፣ ሌሎች እሳት የመቋቋም የቆይታ አቅማቸው ከ30 ደቂቃ በታች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ጥናቱን ያቀረቡት አቶ ጥላሁን የጡብ፣ የብሎኬትና የጭቃ ቤቶች የፍሳሽ መውረጃ በተገቢው መንገድ ያልተሠራ በመሆኑ፣ ብዙዎቹ ቤቶች ለጎርፍ አደጋ የተጋለጡ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

የከተማዋ የልማት ዕቅድና የአደጋ ሥጋት የፖሊሲ ማዕቀፎች አስፈላጊ መሆናቸውን የጠቆሙት አማካሪው፣ ማዕቀፉን መነሻ በማድረግ አስገዳጅ ሕጎች አለመኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

የመደበኛ ቤቶችም ሆኑ በተቋማት የሚገነቡ ቤቶች የደኅንነት ደረጃዎችን  ያሟሉ እንዲሆኑ አስገዳጅ ሕግ መኖር አለበት ብለዋል፡፡

አቶ ጥላሁን የፖሊሲ ማዕቀፎችን የከተማ አስተዳደሩ የሚያሰናዳ ቢሆንም፣ ኮሚሽኑ የደኅንነት ደረጃ የፖሊሲ ማዕቀፎችን አዘጋጅቶ ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ ሲንከባለል መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

ለዚህም የአደረጃጀት፣ የከተማ አስተዳደሩ የፖሊሲ ማዕቀፍ የኅብረተሰቡ ለአደጋዎች ያለው ግምት አናሳ መሆን፣ የተቋማትና የባለድርሻ አካላት ያለመናበብ ችግሮች እንዳሉ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ (ክፍል አንድ)

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...