Tuesday, February 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየከተማ አስተዳደሩ የ20/80 እና 40/60 የጋራ ቤት ዕጣ ሊያወጣ መሆኑ ተጠቆመ

የከተማ አስተዳደሩ የ20/80 እና 40/60 የጋራ ቤት ዕጣ ሊያወጣ መሆኑ ተጠቆመ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን (ኮንዶሚኒየም) ዕጣ በዚህ ሳምንት መገባደጃ ወይም በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ሊያወጣ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

ሪፖርተር ከምንጮቹ ለማረጋገጥ እንደቻለው፣ ዕጣ የሚወጣበት እያንዳንዱ የቤት ዓይነት ባይገለጽም፣ ከሁለት ሺሕ በላይ ቤቶች ለዕጣ ተዘጋጅተዋል፡፡

ምንም እንኳን ሁከትና ብጥብጥን አስከትሎ የነበረውና በወቅቱ ምክትል ከንቲባ በነበሩት ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) አማካይነት የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ ወጥቶባቸው የነበሩ 51,299 የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለዕድለኞቹ ቁልፍ ተሰጥቶ ያልተጠናቀቀ ቢሆንም፣ አሁንም ዕጣ መውጣቱ በተለይ ለ1997 ዓ.ም. ተመዝጋቢዎች ትልቅ ተስፋ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በአጠቃላይ በ2005 ዓ.ም. 650 ሺሕ ዜጎች የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለማግኘት ተመዝግበው የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ ከ200 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ያለሟቋረጥ እየቆጠቡ ያሉ ናቸው፡፡ በ1997 ዓ.ም. የተመዘገቡና ዕጣ እየጠበቁ የሚገኙት ነዋሪዎች 18,000 ናቸው፡፡

በተለይ በ1997 ዓ.ም. ተመዝግበው ላለፉት 16 ዓመታት በመጠባበቅ ላይ ያሉት ነዋሪዎች ሰሞኑን ይወጣል በተባለው ዕጣ ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደሚካተቱም ተጠቁሟል፡፡

የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. በአጠቃላይ 51,229 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የወጣባቸው ሲሆን፣ 32,653 ያህል የ20/80 እና 18,576 የሚሆኑ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ናቸው፡፡

በ2005 ዓ.ም. የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ተመዝጋቢዎች ውስጥ አቅምና ፍላጎት ያላቸው ተመዝጋቢዎች፣ በማኅበር በመደራጀት በጋራ መገንባት እንደሚችሉና የቤቱን ግምት 70 በመቶ ቅድሚያ እንዲከፍሉ አስተዳደሩ ባመቻቸላቸው ዕድል በርካቶች መመዝገባቸው ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የካቲት አብዮት – ጥያቄዎችሽ ዛሬም እየወዘወዙን ነው!

በበቀለ ሹሜ አጭር መግቢያ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ከ1960ዎች ወጣቶች ርዝራዦች አንዱ...

የሰሞኑ የ“መኖሪያ ቤቶች” የጨረታ ሽያጭ ምን ዓይነት ሕጋዊ መሠረት አለው?   

በዳዊት ዮሐንስ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ አየር ላይ ከሚንሸረሸሩ ዜናዎች...

ሁለቱ ወጎች፡ ከሰማየ ሰማያት አድርሶ መላሹ ቋንቋ! እስከ በዓሉ ቤርሙዳ

በተክለ ጻድቅ በላቸው ሰማየ ሰማያት አድርሶ መላሹ ቋንቋ! ከሁለት ሦስት ዓመት...

ለትግራይ ክልል ድርቅ ተፈናቃዮች አፋጣኝና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲደረግ ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዩች ቋሚ...