Tuesday, January 31, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለ22 ሳምንታት የተከናወነው ብሔራዊ የማኅበረሰብ ተኮር መድረክ በርካታ ጥያቄዎች ተነሱበት

ለ22 ሳምንታት የተከናወነው ብሔራዊ የማኅበረሰብ ተኮር መድረክ በርካታ ጥያቄዎች ተነሱበት

ቀን:

በሰላም ሚኒስቴርና በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካይነት ላለፉት 22 ሳምንታት ሲካሄድ በቆየው ብሔራዊ የማኅበረሰብ ተኮር መድረክ በርካታ የማኅበረሰቡ ጥያቄዎች እንደተነሱበት ተገለጸ፡፡

በሰላም ሚኒስቴር የሃይማኖትና ዕምነት ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ፍሰሐ እንዳስታወቁት፣ የሰላም ሚኒስቴር ያስተባበረው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሁሉም ክፍላተ ከተሞች ከአምስት ወራት በላይ ብሔራዊ የማኅበረሰብ ተኮር የምክክር መድረክ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ ኅብረተሰቡ የትኛውም አካል አጀንዳ ሳይሰጠው ከግለሰብ እስከ አገር አቀፍ ደረጃ ያሉ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት፣ በማኅበረሰቡ ከሚቀረፉት እስከ በላይ አካል መፈጸም የሚገባቸውን ጉዳዮች ለይቶ በማውጣት ለመፍትሔ ማቅረቡን አስታውሰዋል፡፡  

በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም እሴት ግንባታ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመሥገን እጅጉ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ በዋናነት ተቋማቸው ያስተባበረው ብሔራዊ የማኅበረሰብ ተኮር የምከክር መድረክ ላለፉት ሃያ ሁለት ሳምንታት ተደርጓል፡፡ ማኅበረሰቡ ያሉበትን ችግሮች በግልጽ አውጥቶ በመሞገት በራሱ፣ የሚፈቱትን በራሱ፣ በመንግሥት ሊፈቱ የሚገባቸውን መንግሥት እንዲፈታ በማሰብ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ እንደነበረ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

መግባባትን፣ መወያየትንና እንዲሁም ችግሮችን ማንሳት በራሱ እንደ አንድ ዕርምጃ ይቆጠራል ያሉት አቶ ተመስገን፣ በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገው የማኅበረሰብ ተኮር ውይይት ነዋሪዎች በየአካባቢያቸው፣ በየወረዳቸው በከተማና በአገር ደረጃ መነሳት ያለባቸውን ችግሮች በስፋት እንዳነሱ አስረድተዋል፡፡

የምክክር መድረኩ በየሳምንቱ ውይይት ከሚደረግባቸው 8,803 የብሎክ አደራጃጀቶች ተነስቶ ወደ ወረዳዎች እንደሚሸጋገር በወረዳው የሚፈቱትን መፍትሔ በመስጠት፣ ወደ ቀጣዩ ዕርከን የሚሄዱትን ደግሞ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ እንዲፈቱ የማድረግ ሥራ እንደተሠራና በመጨረሻም ጉዳዩን ወደ ማዕከላዊ የከተማ አደረጃጀት በማምጣት፣ ለሁሉም የሴክተር ክፍሎች እንደሚቀርብና መፍትሔ እንደሚበጀትለት ገልጸዋል፡፡ በከተማ አስተዳደሩ ባሉት ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የማይመለሱ ጥያቄዎችንና ችግሮችን ደግሞ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ መንግሥት ፖሊሲ ቀርፆ ምላሽ እንዲያገኙ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡

በመድረኮቹ ላይ መልስ የሚፈልጉ ከሕግ ማስከበሩ ሒደት ጋር የተነሱ ችግሮች እንደነበሩ፣ ይህም መንግሥት ሕግ ለማስከበር ለምን ዘገየ ከሚለው የትግራይ ክልል ነዎሪዎች የሚገጥሙዋቸውን ችግሮች ለመቅረፍ መንቀሳቀስ አለበት የሚሉ፣ የመልካም አስተዳደር ችግር ተብለው ከተለዩት ደግሞ የኑሮ ውድነት፣ የከተማ ቤት ኪራይ መናርና የትራንስፖርት እጥረት ችግር ሊፈታ ይገባል የሚሉ ጥያቄዎች መነሳታቸው ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በመድረኮቹ ላይ ሚናው የማስተባበር እንደሆነ ያስታወቁት የሰላም እሴት ግንባታ ዳይሬክተሩ፣ ሁሉንም ጥያቄዎች መመለስ ባይቻልም የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ዞሮ ዞሮ በሰላምና በፀጥታ ሁኔታ ላይ ተፅዕኖ ስለሚያሳድር፣ ቢሮው ኃላፊነቱን እንደተረከበና ነገር ግን ለችግሮች እልባት የሚሰጡት የሚመለከታቸው አካላት እንደሆኑ አስታውቀዋል፡፡

በአጠቃላይ ለሃያ ሁለት ሳምንታት ከተደረገው ውይይት በመነሳት የሰላምና የፀጥታ አስተዳደር ቢሮው የተነሱትን ጥያቄዎች ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት እያቀረበ እንደሚገኝ፣ የተነሱት ችግሮች መፈታት አለመፈታታቸውን እግር በእግር እየተከተሉ የመቆጣጠር ሥራ ከዚህ በኋላ እንደሚከናወን አቶ ተመሥገን ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...