Friday, July 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበአዲስ አበባ ምርጫን በማስታከክ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ምርጫን በማስታከክ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

ቀን:

በሰኔ ወር አጋማሽ ከሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮው ኃላፊ አቶ ባዩ ሽጉጤ እንዳስታወቁት፣ የሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም.  አገራዊ  ምርጫ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከናወን ለማድረግ በዕቅድ የተደገፈ ቅድም ዝግጅት እንደተደረገና ከምርጫው በፊት፣ በምርጫው ዕለትና ምርጫው እንደተጠናቀቀ የሚያጋጥሙ  ከፀጥታ ጋር የተያያዙ ችግሮች ካሉ ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ቢሮ ኃላፊው ከአምስት ወራት በላይ ሲካሄድ በነበረው የብሔራዊ ምክክር መድረክ ማጠናቀቂያ ፕሮግራም ላይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተገኙበት ዕለት ሪፖርተር አነጋግሯቸው እንደገለጹት ‹‹አገራዊ ምርጫውን ለማደናቅፍ የሚችል ኃይል ማን ነው? በተናጠልም ሆነ በህቡዕ እንዲህ ዓይነት ድርጊት የሚፈጽሙ አካላት እነ ማን ናቸው?›› የሚሉት ጉዳዮች በጥናት ተለይተው የሚመለከታቸው አካላት ዕርምጃ እየወሰዱ እንደሆነ  ያስታወቁት  ኃላፊው፣ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከጎዳና ተዳዳሪዎችና በልመና ከሚተዳደሩ ግለሰቦች ጋር በመመሳሰል የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመካላከል እንዲቻል፣ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በልመናና በጎዳና ተዳዳሪነት በሚተዳደሩ ግለሰቦች ላይ ትኩረት ያደረገ የተሃድሶ ሥልጠና ከወዲሁ እየተሰጠ እንደሚገኝ ያስታወቁት የቢሮ ኃላፊው፣ በወንጀል ድርጊቶች ተሳትፎ ያላቸውን ለሚመለከተው የሕግ አካል በማቅረብ፣ የተቀሩትን ደግሞ ወደ መደበኛ የሥራ እንቅስቃሴ በማስገባት የሚያጋጥመውን የፀጥታ ሥጋት ለመቀነስ እየተሠራ እንደሆነ አክለዋል፡፡

በምርጫ ካርድ አወሳሰድ ወቅት በከተማዋ የተከናወነው የምርጫ እንቅስቃሴ ሰላማዊ እንደነበረ ሁሉ፣ በምርጫው ዕለትም ኅብረተሰቡ በወሰደው ካርድ የፈለገውን አካል እንዲመርጥ ያለውን የሰላምና ፀጥታ እንቅስቃሴ ማጠናከር አስፈላጊ ነው ያሉት ኃላፊው፣ ይህንኑ ተግባር ከኅብረተሰቡ ጋር በመሆን ለማከናወን በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል፡፡ በአዲስ አበባ የሚከናወነውን ምርጫ ለማደናቀፍ የሚሠሩ ኃይሎች ካሉ ለመከላከል የሚያስችል ዝግጅት መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

ከምርጫ በኋላም የሚመለከተው አካል የምርጫውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ሆኑ መንግሥት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በዚህ ወቅትም ግርግር ለመፍጠር የሚሞክሩ ኃይሎች ካሉ ኅብረተሰቡ በመቃወም ለሕግ አጋልጦ እንዲሰጥ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚከናወነው ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን ከሁሉ በላይ የሰላምና የፀጥታው ኃይል ማለትም ፖሊስ፣ ቁጥራቸው ከስድስት ሺሕ በላይ የሆኑ የደንብ ማስከበር አባላት፣ እንዲሁም በየአካባቢው የተዋቀሩ የሕዝብ ቅጥር ጥበቃዎች ቅንጅት ወሳኝ እንደሆነ ያስረዱት አቶ ባዩ፣ ይህንን መሠረት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከወዲሁ ከፍተኛ ቅድመ ዝግጅት እንዳደረገ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አቶ ሰብስብ አባፊራ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ከአዋጅና መመሪያ ውጪ ለዓመታት ሳይካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ...

ቀጣናዊ ገጽታ የያዘው የኢትዮ ሶማሊያ ውዝግብ

ከአሥር ቀናት ቀደም ብሎ በተካሄደው የፓርላማ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ፣...

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በዓረቦንና የጉዳት ካሳ ክፍያዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መጣሉን ተቃወሙ

በአዲሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ውስጥ የኢንሹራንስ ከባንያዎች ለሚሰበስቡት...