Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትከአምስት ዓመት በኋላ የተሰበረው የአልማዝ አያና ክብረ ወሰን እና የቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ

ከአምስት ዓመት በኋላ የተሰበረው የአልማዝ አያና ክብረ ወሰን እና የቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ

ቀን:

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከሚታወቁባቸው የሩጫ ውድድሮች አምስትና አሥር ሺሕ ሜትር በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡ ከሻምበል ምሩፅ ይፍጠር (ማርሽ ቀያሪው) እስከ አልማዝ አያና በሁለቱም ፆታ ኢትዮጵያን አትሌቶች በኦሊምፒክም ሆነ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከቅርብ ተቀናቃኞቻቸው ኬንያውያን ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው የአገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ የሚያደርጉበት ብቸኛው መታወቂያቸው ተደርጎ ሲነገርላቸው ቆይቷል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተለይም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ በኢትዮጵያውያን ተይዞ ለዓመታት የዘለቁ ‹‹በሁለቱም ርቀት›› የዓለም ክብረ ወሰን በሌሎች አገሮች አትሌቶች እየተወሰዱ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለቶኪዮ ኦሊምፒክ እያዘጋጃቸው ከሚገኙት ብሔራዊ አትሌቶች መካከል በአምስትና በአሥር ሺሕ ሜትር የመጨረሻዎቹን አትሌቶች ለመለየት ባለፈው እሑድ ሔንግሎ ላይ በአጠቃላይ 50 አትሌቶች የማጣሪያ ውድድር እንዲያደርጉ ወደ ሥፍራው መላኩ ይታወቃል፡፡

ይሁንና በአሥር ሺሕ ሜትር የተወዳደረችው በትውልድ ኢትዮጵያዊት በዜግነት ኔዘርላንዳዊት የሆነችው ሲፋን ሐሰን ከአምስት ዓመት በፊት በተደረገው የሪዮ ኦሊምፒክ ላይ በአልማዝ አያና (29፡17.45) ተይዞ የቆየውን የዓለም ክብረ ወሰን በመስበር (29፡06.82) ማሸነፏ የሳምንቱ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ ሌሎች አገሮች ምን ያህል እንደተዘጋጁ የሚያመላክት ተደርጎም ተወስዷል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባደረጉት ስምምነት መሠረት ከመካከለኛ ርቀት ጀምሮ እስከ ማራቶን በአጠቃላይ ከ120 በላይ ብሔራዊ አትሌቶች ሆቴል ተቀምጠው ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ ይሁንና ይህ ዓይነቱ ዝግጅት በኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ታሪክ የመጀመሪያ ቢሆንም በዚህ መሐል በሁለቱ ተቋማት መካከል ከምርጫና መሰል ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የተፈጠረው ችግር በተለይ ለስፖርት ቤተሰቡ ግራ አጋቢ ሆኖ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ የቆዩት አትሌቶች ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ ባለፈው እሑድ በአውሮፓውያን ታላላቅ ማናጀሮች አማካይነት በተዘጋጀው የአምስትና አሥር ሺሕ ሜትር የማጣሪያ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ ሥፍራው የተጓዙት፣ በአምስት ሺሕ ሜትር ወንድ 13፣ ሴቶች 12 በድምሩ 25 አትሌቶች ሲሆኑ፣ በአሥር ሺሕ ሜትር እንደዚሁ ወንድ 13 ሴቶች 12 በድምሩ 25 መሆናቸው ፌዴሬሽኑ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያሰፈረው መረጃ ያመለክታል፡፡

የውድድሩ አስፈላጊነት በዋናነት ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ተሳትፎ የሚያበቃውን ሰዓት (ሚኒማ) ማግኘት ቢሆንም፣ የሲፋን ሐሰንን ጨምሮ በሌሎችም ተመሳሳይ ውድድሮች በኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለዓመታት ተይዘው የነበሩ የየርቀቱ ክብረ ወሰኖች በሌሎች አገሮች አትሌቶች የበላይነት ሲጠናቀቁ ብቻ ሳይሆን፣ በአዳዲስ ክብረ ወሰኖች ጭምር መሆኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስና የዘርፉ ሙያተኞች ቆም ብለው ራሳቸውን እንዲፈትሹ የሚያስገድድ መሆኑ ይወሳል፡፡

የአልማዝ አያናን የአሥር ሺሕ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ያሻሻለችው ሲፋን ሐሰን፣ ቀደም ባሉት ዓመታት እንደ ቀደሙት እንደ ደራርቱ ቱሉ፣ መሠረት ደፋር፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ አልማዝ አያናና ሌሎችም በኢትዮጵያ ብሔራዊ አትሌቲክስ ቡድን ውስጥ ለመካተት አቅሙ ስላልነበራቸው ለሌሎች አገሮች ሮጠው ዕድላቸውን ለመጠቀም ሲሉ ዜግነታቸውን የቀየሩ መሆናቸው ልብ ሊባል እንደሚገባ ጭምር የሚናገሩ አልጠፉም፡፡

ችግሩን አስመልክቶ ማንነታቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፌዴሬሽኑ ባለሙያ እንደሚናገሩት ከሆነ፣ ‹‹ቀደም ባሉት ዓመታት የነበረው የአሠልጣኝና ሠልጣኝ ግንኙነት አሁን ላይ በፍጹም የለም፡፡ በተለይ የታላላቅ አትሌቶች ፍላጎት ካልታከለበት በስተቀር በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሚሾሙ ብሔራዊ አሠልጣኞች በአትሌቶች ያላቸው ተሰሚነት እጅጉን አናሳ ነው፡፡ ይህ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ አደገኛ ነው፤›› ምክንያቱንም ሲያብራሩ ብዙዎቹ አትሌቶች የሚሠለጥኑት በሚፈልጉት አሠልጣኝና በትዳር አጋሮቻቸው ጭምር መሆኑ ለፌዴሬሽኑ ኃላፊዎች አዲስ አይደለም ብለው፣ ችግሩን ተከትሎ በተደረጉ ተደጋጋሚ ግምገማዎች አሠልጣኞቹና ሌሎች ድጋፍ ሰጪ ሙያተኞች አሠራሩ ሊፈተሽ እንደሚገባው ይጠቁማሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹በየቦታው ምርት እየገዙ የሚያከማቹ ከበርቴ ገበሬዎች ተፈጥረዋል››

አቶ ኡስማን ስሩር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር...

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...