Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ዜና ፍለጋ

ትኩስ ፅሁፎች

አንዱ ሰውዬ በየዕለቱ ጠዋት ጋዜጣ ሻጩ ዘንድ ይመጣና ፕራቭዳ የተባለውን የሶቭየት ኅብረት ጋዜጣ ከገዛ በኋላ፣ የመጀመርያውን ገፅ ተመልክቶ አጠገቡ ካለው ቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ይወረውረዋል፡፡

ይህን ደጋግሞ ሲያደርግ ያየው ጋዜጣ ሻጭ ድርጊቱ ስለከነከነው፣ ‹‹በየዕለቱ የፕራቭዳን ቅጂ ገዝተህ ሳታነበው ቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ውስጥ ትጥለዋለህ፡፡ ለምንድነው ታዲያ የምትገዛው?›› በማለት ጠየቀው፡፡

‹‹እኔ ማየት የምፈልገው የመጀመርያውን ገፅ ብቻ ነው›› አለ ሰውየው፣ ‹‹ዜና ዕረፍት ካለ ለማየት ነው የምፈልገው፡፡››

‹‹ዜና ዕረፍት’ኮ ታዲያ የፊት ገፅ ላይ አይወጣም!››

‹‹እኔ የምፈልገው ዜና ግን የፊት ገፅ ላይ እንደሚወጣ አረጋጋጥልሃለሁ፡፡››

  • አረፈ ዓይኔ ሐጐስ ‹‹ፖለቲከኞች እፈሩ ቀልድ እና ቁምነገር›› [2013]
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች