Sunday, July 14, 2024

[ክቡር ሚኒስትሩ እንዲጣራ ባዘዙት አንድ መረጃ ላይ የአማካሪያቸውን ሪፖርት አድምጠው ተጨማሪ ውይይት እያደረጉ ነው]

 • ስለዚህ ኩባንያው በአዲስ አበባ አምስት መቶ ሺሕ ቤቶች በዓመት ለመገንባት ነው የተፈራረመው?
 • ስምምነቱ እንደዚያ ነው የሚለው ክቡር ሚኒስትር።
 • በየዓመቱ መቶ ሺሕ ቤት ለመገንባት አስተዳደሩ ያዘጋጀው ቦታ መኖሩ ተረጋግጧል?
 • አዎ ክቡር ሚኒስትር። ነገር ግን ይህን ያህል ቤት ለመገንባት የተዘጋጀ ቦታ አለመኖሩን አረጋግጠናል፡፡
 • ስለዚህ ጉዳይ አስተዳደሩ ምን ይላል?
 • ቦታውን በሒደት እንፈልጋለን ነው የሚለው። 
 • የግንባታ ወጪውንስ እንዴት ነው ለመሸፈን ያሰቡት?
 • አስተዳደሩ ድርሻዬ መሬት ማቅረብ ብቻ ነው ወጪው በኩባንያው ይሸፈናል ይላል።
 • ኩባንያው ወጪ የመሸፈን አቅም አለው?
 • ጭራሽ የለውም፡፡ 
 • እና እንዴት ነው ወጪውን የሚሸፍነው?
 • ፌዴራል መንግሥት የብድር ዋስትና ከሰጠኝ ገንዘቡን ለማግኘት አልቸገርም ነው የሚለው።
 • የብድር ዋስትና ከፌዴራል መንግሥት?
 • አዎ ክቡር ሚኒስትር።
 • ታዲያ ኩባንያው ወደ ከተማ አስተዳደሩ ዘንድ ለምን ሄደ?
 • አምጪዎቹ የሚያውቁት ሰው ያለውከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ነው። 
 • አምጪዎቹ ምን ማለት ነው?
 • ድርጅቱ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ አሳምነው ያመጡ ግለሰቦች ናቸው። 
 • አሳምነው ያመጡ ግለሰቦች ናቸው ነው ያልከው?
 • ለነገሩ አስቸጋሪ ሳይሆን አይቀርም አይመስልህም?
 • ምኑ?
 • ገንዘብ የሌለው ድርጅት አሳምኖ ማምጣት። 
 • ይመስለኛል. . . አስቸጋሪ ነው።
 • ስለዚህ ኩባንያው መንግሥትሚሰጠው ዋስትና ብድር ፈልጎ ግንባታውን ለማካሄድ ነው የተስማማው ማለት ነው?
 • ግንባታው በማን እንደሚያካሂድ በስምምነቱ አልተገለጸም።
 • እንዴት?
 • ኩባንያው ዋስተናውን ይዞ 30 ዓመት የሚከፈል ገንዘብ ለማምጣት ነው የተስማማው። 
 • ቤቱን የተረከበ ነዋሪ የቤቱን ዋጋ አንድ በመቶ ወለድ 30 ዓመት ይከፍላል የሚል ዜና አልነበር እንዴ የተሰማው?
 • እኛ ባጣራነው መሠረት ኩባንያው ገንዘቡን ለሚያመጣበት አንድ በመቶ ወለድ እንደሚያገኝ ነው።
 • ስለዚህ የመንግሥትን የብድር ዋስትና ይዞ ገንዘብ ማምጣትና አንድ በመቶ ኮሚሽን ማግኘት ነው የኩባንያው ኃላፊነት? 
 • ክቡር ሚኒስትር ነገሩ እንደዚያ ነው የሚመስለው። ምክንያቱም የተሰናዳ መሬትም ሆነ ግንባታውን የሚያከናውነው አይታወቅም። 
 • በጠራራ ፀሐይ የተፈረመው ይኽ ነው በል የኩባንያውን የኋላ ታሪክ ቶሎ መርምራችሁ አቅርቡ።
 • እሱን ቀድመን መርምረናል ክቡር ሚኒስትር።
 • እና ምን አገኛችሁ?
 • በበርካታ የአፍሪካ አገሮች የሠራው ሥራ ተመሳሳይ ነው። 
 • ምንድነው የሠራው? 
 • የብድር ዋስትና ይዞ መሰወር፡፡
 • እና ምን ወሰናችሁ? ቶሎ ይህ ስምምነት እንዲፈርስና ሕዝብ እንዲያወቀው አደረጋችሁ?
 • ክቡር ሚኒስትር እሱን ለማድረግ ተቸግረናል።
 • ለምን?
 • ምርጫው ላይ ድምፅ ያሳጣናል። ስለዚህ ለጊዜው እናቆየውና በኋላ ስምምነቱን አፍርሰን ብናሳውቅ ይሻላል። 
 • ወሬው ገና ካሁኑ እየተናፈሰ አይደለም እንዴ? ሲታወቅ ምን ልታደርጉ ነው?
 • ለሱ ዘዴ አበጅተናል። 
 • የምን ዘዴ?
 • አምጪዎቹ ሚዲያ ላይ ቀርበው የሚናፈሰው ወሬ ሐሰተኛ ነው ብለው እንዲያስተባብሉ አድርገናል።
 • እነሱ መናገራቸው ምንድነው ጥቅሙ?
 • ከምርጫው በኋላ በእኛ በኩል ይፋ ለሚደረገው መረጃ ይጠቅማል። 
 •  ከምርጫርው በኋላ ያሰባችሁት ምንድነው?
 • ወኪሎቹ የተናገሩትም ሆነ የኩባንያው አጠራጣሪ መሆናቸውን መንግሥት አረጋግጦ ስምምነቱን እንዲሰረዝ ወስኗል የሚል መረጃ ለመልቀቅ ይመቸናል፡፡
 • መቀጣጫ የሚሆን ጥሩ መፍትሔ ነው!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሥራ መልስ በመኖሪያ ቤታቸው አረፍ ብለው የምሽቱን የቴሌቪዥን ዜና ከባለቤታቸው ጋር እየተከታተሉ ሳለ በአዲስ አበባ 500 ሺሕ ቤቶች ለመግንባት በተስማማው ኩባንያ ላይ የሚሠራጨው ወሬ የተሳሳተ ነው የሚል ዜና ከነምስሉ መታየት ጀመረ]

 • ቀጣፊ 
 • ምን አልክ?
 • ወዲህ ነውእንድ ነገር ትዝ ብሎኝ ነው።
 • ወዲህ ቢሆን ጥሩ ነበር። 
 • ምኑ?
 • አሁን ያልከው
 • ለምን?
 • በየቦታው እነሱ ብቻ ሆኑ እኮ? 
 • እነ ማን?
 • ምን ነበር ያልካቸው ቀጣፊ ነው ያልከው?
 • አንድ ነገር ትዝ ብሎኝ ነውወዲህ ነው አልኩሽ እኮ 
 • ወዲህም ቢሆን ያው ነው 
 • ወዴት?
 • ይኸው በየቀኑ ተመረቀ ለሚሉን፡፡
 • እነ ማን ናቸው?
 • በየሳምንቱ ተመረቀ ብቻሕዝቡ ግን የሚደርስ የለም።
 • ምኑ?
 • ፋብሪካው ነዋ። በየዕለቱ ዘይት ፋብሪካ ተመረቀ ነው ዜናው ሁሉ። 
 • እሱን ነው …?
 • ዜናው ሁሉ ዘይት ፋብሪካ ተመረቀ ሆነ እኮወይስ ስሌላ ዘይት ይሆን የሚያወሩት?
 • ሌላ የምን ዘይት ሊሆን ይችላል ደግሞ?
 • የሞተር ይሆናላ
 • ጀመረሽ ደግሞ ይኼ ማፌዝ?
 • ምን አፌዛለሁ አልጣጣም ቢለኝ ነው እንጂ።
 • እንዴት?
 • የባህር ዳሩ ተመረቀ ብለው እሰይ ብለን ሳናበቃ ሌላ ይነግሩናል።
 • ሌላ ምን?
 • ድሬዳዋ ሌላ ተመረቀ ይሉናልዳግም እሰይ ብለን ሳናበቃ ሌላ ዜና ያመጣሉ፡፡  
 • ሌላ ምን?
 • ደብረ ማርቆስ ተመረቀ ነዋ 
 • ታዲያ ምንድነው ችግሩ? 
 • ዜና ዘይት አይሆን፡፡
 • ምን አልሽ?
 • ዘይቱ ገበያ ላይ የለም አልኩህ፡፡
 • አልዳረስ ብሎ እንጂ ፋብሪካዎቹ እያመረቱ ነው።
 • ከተመረተ ለምን አይዳረስም?
 • ፋብሪካዎቹ የሚያገኙት ጥሬ ዕቃ አነስተኛ ስለሆነ
 • የጥሬ ዕቃም እጥረት አለ ነው የምትለው?
 • እንዲያውም ዋናው ችግር ጥሬ ዕቃው ነው።
 • የዘይቱ ጥሬ ዕቃ?
 • አዎ!
 • እኔ ምለውዘይቱ የእንትን ነው እንዴ?
 • የምን?
 • የዓሳ ዘይት፡፡
 • አሹፊ አንቺ?
 • ኧረ እያሾፍኩ  አይደለምመጀመርያ የአዋጭነት ጥናት ቢሠራ ጥሩ ነበር፡፡
 • የምን አዋጭነት ጥናት?
 • የቱ መቅደም አለበት ተብሎ ቢጠና ጥሩ ነበር?
 • አልገባኝም?
 • መጀመርያ ዓሳውማለቴ ጥሬ ዕቃው ይቅደም ወይስ ዘይቱ የሚለው መጠናት ነበረበት፡፡
 • ብዙ ታወሪያለሽ አንቺበይ ደህና እደሪ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...

በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ሳቢያ አጠቃላይ ገበያው እንዳይታመም ትኩረት ይደረግ!

መንግሥት ነዳጅን ከመደጎም ቀስ በቀስ እየወጣ ነው፡፡ ለነዳጅ የሚያደርገውን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ሳይገኝ ከቀረው አንድ የተቋማቸው ባልደረባ የሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ አባልን አስጠርተው እያናገሩ ነው]

ለምንድነው በዚህ አገራዊ ፋይዳ ባለው ፕሮግራም ላይ ያልተገኘኸው? ክቡር ሚኒስትር ህሊናዬ አልፈቀደልኝም። መቃወምና መተቸት ብቻ ውጤት የሚያመጣ መስልዎህ ከሆነ ተሳስተሃል። አልተሳሳትኩም ክቡር ሚኒስትር? ቆይ የመጀመሪያ ዓመት የችግኝ ተከላ...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላነጋግርህ የፈለኩት ክቡር ሚኒስትር፡፡ እርስዎማ ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግዎትም፣ ምን ገጠመዎት? እኔማ ምን ይገጥመኛል አንተኑ ልጠይቅህ እንጂ? ምን? እውነት ለመናገር የማየው ነገር አሳስቦኛል፡፡ ይንገሩኝ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በቢሯቸው ሆነው ከአማካሪያቸው ጋር ስለወቅታዊ ጉዳዮች እየተነጋገሩ ነው]

ትናንት የሆነውን ሰሙ ክቡር ሚኒስትር? አልሰማሁም፣ ምን ሆነ?  ኬንያውያን የአገሪቱን ፓርላማ ጥሰው መግባታቸውን አልሰሙም? ኧረ አልሰማሁም።  የፓርላማውን በር ጥሰው ገብተው አንደኛውን ክፍል በእሳት አያያዙት፡፡  ምንድነው ምክንያቱ?  የአገሪቱ መንግሥት ያቀረበው አዲስ...