Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበአዋጅ ሊቋቋም ታስቦ የነበረው የበጀት ድጎማና የገቢ ክፍፍል  ኮሚሽን አያስፈልግም ተባለ

በአዋጅ ሊቋቋም ታስቦ የነበረው የበጀት ድጎማና የገቢ ክፍፍል  ኮሚሽን አያስፈልግም ተባለ

ቀን:

የፌዴራል ድጎማ፣ በጀትና የጋራ  ገቢዎች ክፍፍል ሥርዓትና ተቋማዊ  አደረጃጀትን ለመወሰን በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ የበጀት ክፍፍሉን የበለጠ ግልጽና ፍትሐዊ ለማድረግ ያግዛል በሚል እንዲቋቋም ታስቦ የነበረው፣ ‹‹የድጎማና የጋራ ክፍፍል ኮሚሽን›› ከረቂቁ እንዲወጣ ተደርጎ አዋጁ ፀደቀ፡፡

 ፓርላማው ረቂቅ አዋጁን ኅዳር 4 ቀን  2012  .ም.  ባካሄደው  መደበኛ  ስብሰባ  ውይይት አድርጎበት ለዝርዝር ዕይታ ለሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች  ለገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መምራቱ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ረቂቁ በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ ነበር፡፡ ለረጅም ጊዜ  ውይይት  ተካሂዶበት  መጨረሻ የኮሚሽን ማቋቋም አስፈላጊነት ታምኖበት ነበረ፡፡ ነገር ግን  በሥራ ላይ ያለው  የፌዴሬሽን  ምክር ቤት  ጽሕፈት  ቤትን  ይበልጥ  በማጠናከር ሥራዎችን ማከናወን እንደሚቻል መታመኑን፣ የሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ  ሰብሳቢ አቶ አቡ በክሪ ለምክር ቤቱ ገልጸዋል፡፡

በረቂቅ አዋጁ እንዲቋቋም ታስቦ የነበረው ኮሚሽን በምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ  አቅራቢነት በፓርላማው የሚሾሙና ለአምስት ዓመታት የሚያገለግሉ ኮሚሽነርና ምክትል ኮሚሽነር የሚኖሩት ሲሆን፣ ተጠሪነታቸው ለምክር ቤቱ እንዲሆን የሚያደርግ ነበር፡፡

ኮሚሽኑ ከድጎማና ከጋራ ገቢዎች  ጋር  በተያያዘ  የሚቀርቡ ጥናቶቸን መሠረት  ደረገ ምክረ  ሐሳብ  ማቅረብ፣ የፌዴራል  መንግሥት  ለክልሎች  ድጎማ  የሚደለድልበትን  ወይም  ለክልሎች  የጋራ  ተብለው  የተመደቡ ገቢዎች  የሚከፋፈሉበትን  ቀመር  አስመልክቶ  ምክረ  ሐሳብ  ማቅረብ  ኃላፊነቶች  እንዲወስድ ተደርጎ ሊቋቋም ታስቦ ነበር፡፡

በተጨማሪም በፌዴራል መንግሥት ባለቤትነት የሚዘረጉ  የመሠረተ ልማት  አውታሮች  ላይ  ያለውን  ፍትሐዊ  ሥርጭትን  አስመልክቶ፣  ጥናት  ማቅረብና  የፌዴራል  ድጎማና  የጋራ  ገቢዎች   ማከፋፈያ  ቀመሮችን  አተገባበር  መከታተል የሚሉትም ይገኙበታል፡፡

የፌዴራል መንግሥት  የድጎማ  በጀትና  የጋራ  ክፍፍል  ሥርዓት  የሚወስነው  አዋጅ፣  በምክር ቤቱ አባላት በሁለት ተቃውሞና በአንድ ድምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡

አዋጁ የሀብት ክፍፍሉን ሒደት  የበለጠ  ግልጽነትና  ፍትሐዊነት የሰፈነበት እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በዚህ አዋጅ መሠረት የፌዴራል መንግሥቱ ለክልሎች የሚሰጠውን ድጎማ ጥቅል ዓላማና  ውስን  ዓላማ ያለው በሚል በሁለት ተከፍሏል፡፡

የጥቅል ዓላማ  በጀት  ድጎማ  በአጠቃቀሙ  ላይ  ቅድመ  ሁኔታ  የማይቀመጥበት፣ ክልሎች  ከራሳቸው  ተጨባጭ  ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት  ቅድሚያ  ለሚሰጡት ጉዳይ  እንዲጠቀሙበት የሚፈቅድ የድጎማ ዓይነት ነው፡፡

 ውስን  ዓላማ  ያለው  የበጀት  ድጎማ  በሌላ  በኩል   የተገደበና  አንድ  የተወሰነ  ወይም የተለየ ዓላማን  ለማሳካት  ታስቦ፣  በፌዴራል  መንግሥት  ለክልሎች  የሚሰጥ  የድጎማ ዓይነት እንደሆነ በአዋጁ ተጠቅሷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...