Sunday, April 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ከአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና የኢትዮጵያ ተጠቃሚነትና ሥጋቶች

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከአገራዊ ኢኮኖሚ አንፃር ከፊታችን ከሚጠብቁን ብርቱ ተግባራት መካከል  በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና የንግድ ስምምነቶች መሠረት ጠንካራና ተወዳዳሪ ሆኖ መውጣት ይገኝበታል፡፡ አፍሪካውያን የእርስ በርስ የንግድ ልውውጦችን ለማደራጀትና ትልቅ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ቁርጥ ውሳኔ ከሳረፉባቸውና ወደ ትግበራ ከገቡባቸው ጉዳዮች ውስጥ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትልቅ ቦታ የሚሰጠውም ነው፡፡

ለጋራ ገበያ ስምምነቱ ከኤርትራ በስተቀር ሁሉም የአፍሪካ አገሮች ፊርማቸውን ያኖሩ ሲሆን፣ የኢትዮጵያም የንግድ ልውውጡ ውስጥ ለመግባት እየተቀንቀሳቀሰች ነው፡፡

የአፍሪካ አገሮች ታሪፋቸውን ዜሮ በማድረግ እርስ በርስ የንግድ ልውውጥ በሚያደርጉበትና አኅጉራዊ ኢኮኖሚን ለማጠናከር በሚደረገው ርብርብ ውስጥ  ኢትዮጵያ ቀላል የማይባል ውድድር ይጠብቃታል፡፡

ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች በተሻለ ለማምረትና ምርቶቿን ለማቅረብ የምትጓዝበት መንገድ ቢኖርም፣ በዚህ ቀጣና ተወዳዳሪ መሆን ትችላለች ወይ? የሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎች እየተነሱ የተለያዩ መድረኮች እየተዘጋጁና እየተመከረባቸው ይገኛል፡፡  

ሰሞኑንም በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትና ኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን ዝግጅት የተመለከተ አንድ ጥናት በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት በኩል ተሰናድቶ ውይይት ተካሄዶበታል፡፡

ጥናቱ ሰፊ ሽፋን የነበረው ነው፡፡ ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያዎች ቡድን መሪ አቶ ሙሴ ምንዳዬ፣ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት እያደረገች ያለውን ዝግጅትና ከዚሁ ጋር ታሳቢ የሚደረጉ ክንውኖችን የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማነጋገር አሁን ያለውን ሁኔታ አሳይተዋል፡፡

በተለይ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ለመተግበር ያስችላታል ያሉትን መልካም አጋጣሚዎችና ዕድሎች እንዲሁም ተግዳሮቶችን በጥናታቸው አካተዋል፡፡

እንደ መልካም ዕድል ብለው ከጠቀሱት ውስጥ በዋናነት ኢትዮጵያ የተለያዩ የኢኮኖሚ ሪፎርሞችን ማካሄዷን ነው፡፡ ከፕራይቬታይዜሽን ጋር በተያያዘም እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ኢትዮጵያን በዚህ ስምምነት ተጠቃሚ ያደርጋታል የሚል እምነታቸውን አንፀባርቀዋል፡፡

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና በዓለም ካሉ አካባቢያዊ ጥምረቶች ሁሉ በሕዝብ ብዛትና በአገሮች ቁጥር ትልቁ ነፃ የንግድ ቀጣና ስለመሆኑ በማስታወስም፣ ይህም የንግድ ቀጣና አሁን ካለበት የ16 በመቶ የእርስ በርስ ንግድ እ.ኤ.አ. በ2027 ወደ 52.3 በመቶ ለማሳደግ ያለመ መሆኑንና ኢትዮጵያ ከዚህ ሰፊ ገበያ የመጠቀም ዕድሏ የሰፋ የሚሆንበት ዕድል እንዳለ ጠቁመዋል፡፡  

በስምምነቱ መሠረት የአፍሪካ አገሮች 97 በመቶ የሚሆነውን የታሪፍ መሥፈርታቸውን ዜሮ በማድረግ የእርስ በርስ ንግድ የሚያካሂዱበትና ዓለም ላይ ከሚነገድባቸው 5,387 ምርቶች ውስጥ 4,848 ምርቶች ዜሮ ታሪፍ ሆነው የሚሠራበት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጰያ ያሉ አገሮች በአሥር ዓመት ሌሎች ደግሞ በአምስት ዓመት ታሪፋቸውን ዜሮ በማድረግ የሚገበዩበት መሆኑንም አስረድተዋል፡፡  

የአፍሪካን የኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነት ማሳደግ የሚል ዋነኛ ግብ ያለው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት፣ የአፍሪካ አገሮች ትርፋቸውን ዜሮ በማድረግ በሚኖራቸው የንግድ ልውውጥ የኢትዮጵያ አቅምና ተወዳዳሪነት ምንድነው? ከሚለው አንፃር ተወዳዳሪነትን በተመለከተ በተቀመጡ መለኪያዎች፣ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 13ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

ይህ ጥሩ የሚባል ቢሆንም፣ ከዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት አንፃር ሲታይ ከ138 አገሮች 108ኛ ነች፡፡ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷ ዝቅተኛ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነትን ያሳድጋሉ በሚሉ መሥፈርቶች ላይ መሥራት እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

ይህንን ስምምነት ከመተግበር አኳያ በኢትዮጵያ ምን ዝግጅት እየተደረገ ነው? የሚለው ላይ ከመንግሥትና ከግል ዘርፍ ካነጋገሯቸው ተቋማት ውስጥ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አንዱ ነው፡፡ ሚኒስቴሩ የዚህ ስምምነት አስተባባሪም ነው፡፡  

ስምምነቱን ለማስፈጸም የተለያዩ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል፡፡ አንደኛው የፕሮጀክት ዲዛይንና የመሳሰሉትን ለመተግበር የተቋቋመ ቢሆንም፣ ወደ ተግባር አለመግባቱን  መገንዘባቸውን ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ የንግድ ቀጣና ስምምምነቱን እንዴት ነው የምንጠቀምበት? በየትኞቹ ዘርፎች ላይ ነው የምንጠቀመው? የሚለው ጥናት ግን እየተደረገ እንደሆነ የገለጹት አቶ ሙሴ፣ ሊብራላይዝድ የሚደረጉ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው? በሚለው ዙሪያ ደግሞ ዝግጅት እየተደረገ ስለመሆኑ አመልክተዋል፡፡

ከደረጃዎች ምደባ አንፃርም ስምምነቱ አገሮች የሚያወጡትን ማንኛውንም ይነት ደረጃ መግለጽ የሚያስፈልግ በመሆኑ በዚሁ መሠረት የደረጃ ምዘናው ተቋም ተቋቁሟል፡፡

እንደ ተስማሚና ምዘና ያሉ ተቋማት ላቦራቶሪዎቻቸው እየተሻሻሉና እየሰፉ፣ በምሥራቅ አፍሪካ ጥሩ የምዘና ማዕከል ለመገንባት እየተሠራ መሆኑ ነፃ የአፍሪካ የንግድ ቀጣናን ለመቀላቀል እየተደረጉ ካሉ ዝግጅቶች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው ተብሏል፡፡

ከጉምሩክ አኳያ ብዙ የሰው ኃይል አለመገኘቱ እንደ ተግዳሮት ተቀምጧል፡፡ እንደዚህ ያለ ነፃ የንግድ ቀጣና ኢትዮጵያ ስትፈርም የመጀመርያዋ በመሆኑና ከአተገባበር አኳያ ልምድ ስለሌለ ጉድለት ሊኖር እንደሚችል የጠቆመው ጥናት፣ ወደዚህ ስምምነት ለመግባት አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ዝግጅቶች ከሞላ ጎደል እየተከናወኑ ስለመሆናቸው ጠቁሟል፡፡  

በዚህ ስምምነት ዙሪያ አጥኚዎች የተመለከቱት አንኳር ነጥብ ደግሞ የግል ዘርፉ ምልከታ ምን እንደሚመስል መቃኘት ነበር፡፡ እንደ አቶ ሙሴ ገለጻ፣ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ዙሪያ ያነጋገሯቸው አብዛኛው የግል ዘርፉ አባላት ይህንን ስምምነት በበጎ የተመለከቱት መሆኑን ነው፡፡ በዚህ ረገድ አንዳንድ ዘርፎች ተወዳዳሪ መሆን የሚችሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች የቡናና የጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ እንደ ምሳሌ ተጠቅሰዋል፡፡ ናቹራል ፋይበር ላይ ትልቅ ተወዳዳሪ መሆን ይቻላል፡፡ እንደ ቅባት እህሎችና በመሳሰሉት ዘርፎችም ተወዳዳሪ መሆን እንችላለን ብለዋል፡፡ ብዙዎቹ መወዳደር እንችላለን ለውድድሩ እንዘጋጃለን ቢሉም መፈታት የሚገባቸው ችግሮች ካልተፈቱ ውድድሩ ከባድ እንደሚሆን እንደገለጹላቸውም አመልክተዋል፡፡  

በአፍሪካ የንግድ ነፃ ቀጣና የኢትዮጵያ ኩባንያዎች ተወዳዳሪ ለመሆን ያዳግተናል ብለው ከአብዛኛው ግል ዘርፍ የተነሳው ችግር በአገሪቱ ውስጥ ያለው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ነው፡፡ የውጭ ምንዛሪ በተገቢ ጊዜና መጠን አግኝቶ በቂ ጥሬ ዕቃ ማምጣት ካልተቻለና ካልተመረተ መወዳደር አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ከፍተኛ የጥሬ ዕቃ እጥረት ችግር ካልተፈታ እጅግ አስቸጋሪ ይሆናል የሚለውም የተነሳ ጉዳይ ነው፡፡  

የብድር፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እጥረትና ጥርት ያለ የንግድ ፖሊሲ ያለመኖርም ለተወዳዳሪነቱ እንቅፋት እንደሚሆን ተነስቷል፡፡  

በአፍሪካ የንግድ ቀጣና ስምምነት ተወዳዳሪ ሆኖ ለመውጣት ኢትዮጵያን ይፈትናታል የተባለው ሌላው ችግር ሎጂስቲክስ ነው፡፡ ከሎጂስቲክስ አንፃር ያለው ችግር የአብዛኛው የንግድ ኅብረተሰብ ብርቱ ሥጋት ስለመሆኑ መገንዘባቸውን ያመለከቱት አጥኚዎቹ፣ ይህንን ችግር ከተለያዩ አቅጣጫዎች እንዲመለከቱት አድርጓቸዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥናት መሠረት አንድ አገር ወደብ አልባ በመሆኑ ብቻ የትራንዛክሽን ወጪው በ33 በመቶ የሚጨምር መሆኑንም ጠቁመው፣ ይህ ማለት አንድ ምርት 100 ብር የሚያወጣ ቢሆን ወደብ አልባ በመሆን ብቻ ወደብ ካላቸው አገሮች በ33 ብር ይጨምራል በማለት አስታውሰዋል፡፡ በዚህ ዕሳቤ መሠረት 133 ብር ይሆናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሎጂስቲክሱ ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ አለው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢትዮጵያ ሎጂስቲክስ ፐርፎርማንስ (እስከ 2013) ከ160 አገሮች ውስጥ 116ኛ ነች፡፡

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች