Monday, March 27, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በ550 ሚሊዮን ብር ወጪ የኮንስትራክሽንና የግብርና መገልገያ ዕቃዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ ተከፈተ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኢትዮጵያ ከውጭ ገዝታ የምታስገባቸውን የኮንስትራክሽንና የግብርና ሥራን ያግዛሉ የተባሉ ዘመናዊ የውኃ ማስተላለፊያ ቱቦዎች፣ የውኃ ፓምፖችና ጄኔሬተሮችን በአገር ውስጥ ማምረት የሚችል መገጣጠሚያ ፋብሪካ በ550 ሚሊዮን ብር በአዲስ አበባ ተከፈተ፡፡

ማንቶ ኢንዱስትሪያል የተሰኘው ፋብሪካ የማምረት አቅሙ ቢያንስ 50 በመቶ የሚሆነውን የውኃ ማስተላለፊያ ቱቦዎች፣ የውኃ ፓምፖችና ጄኔሬተሮች በአገር ውስጥ የማምረት አቅም እንዳለው የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አብራር ሙራድ በሐያት ሬጀንሲ ሆቴል ሰኞ ሰኔ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ ተናግረዋል፡፡

የምርቶቹ ዓይነት ፍላት ሆዝ፣ ሴክሽን ሆዝ፣ ወተር ሆዝ፣ ኬሚካል ሆዝ፣ ኤር ፕሬዠር ሆዝና ወተር ሌብል ሆዝ የተሰኙ ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት በአቃቂ ክፈለ ከተማ በሚገኘው ፋብሪካ ወደ 400 የሚጠጉ ሠራተኞች ቀጥሮ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የፋብሪካውን አቅም በመጨመር የምርት መጠኑን ከአገር ውጭ ላሉ ገበያዎች ለመላክ፣ የሠራተኞቹን ቁጥር እስከ 3,000 ለማድረስ አቅዶ እየሠራ እንደሆነ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል፡፡

መንግሥት ለግብርናናአረንጓዴ ልማት የሰጠውን ትኩረት ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ በሁለት ጓደኛሞች የተገነባ ፋብሪካ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

 ይሁን እንጂ ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ በማምረት የሚጠበቅበትን አገልግሎቶች እንዲሰጥ፣ ለግንባታ ማስፋፊያ ቦታ የከተማ አስተዳደሩ ሊሰጠን ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ወቅት በእንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ፣ ፋብሪካውን የመሠረቱት የአዲስ አበባ ወጣቶች የግብርናው ዘርፍ እንዲዘምን ከማድረግ ባሻገር፣ ያለውን የአገር ውስጥ ጥሬ ዕቃ በመጠቀም የግብርና ዕቃዎችን በአገር ውስጥ  እንዲገጣጠሙ ማድረጋቸው የሚበረታታ በመሆኑ በመንግሥት በኩል ዕገዛ የሚደረግላቸው ይሆናል ብለዋል።

በምረቃው ወቅት ፋብሪካው በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ለሚገኙና በግብርና ሥራ ለተሰማሩ 250 አርሶ አደሮች የግብርና መገልገያ ዕቃዎች በስጦታ አበርክቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች