Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለም​​​​​​​የቤኒያሚን ኔታንያሁ የሥልጣን ስንብት

​​​​​​​የቤኒያሚን ኔታንያሁ የሥልጣን ስንብት

ቀን:

በቤኒያሚን ኔታንያሁ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እ.ኤ.አ. ከ1996 እስከ 1999 የመጀመርያውን የሥልጣን ዘመን፣ በኋላም ከ2009 እስከ 2021 ለተከታታይ አሥራ ሁለት ዓመታት እስራኤልን መርተዋል፡፡ በ2019 ሚያዝያ ላይ በተደረገ ምርጫ ከጥምር ፓርቲዎች በቂ ድጋፍ ባለማግኘታቸው ማሸነፍ አልቻሉም ነበር፡፡ በቀጣይም ለእሳቸው አመርቂ ያልሆኑ ሁለት ምርጫዎችም ተከናውነዋል፡፡

በሦስተኛው ምርጫ በወቅቱ የተቃዋሚ መሪ ከነበሩት ቤኒ ጋንትዝ ጋር በመሆን ብሔራዊ ጥምር መንግሥት መሥርተው ነበር፡፡ ነገር ግን ስምምነታቸው ባለመፅናቱ እስራኤል ደግሞ ምርጫ በመጋቢት አካሄደች፡፡ የናታንያሁ ሊኩድ ፓርቲ ትልቁ ቢሆንም፣ ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳግም መንግሥት መመሥረት ስላቃታቸው ኃላፊነቱ በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠውን የሽ አቲድ ፓርቲ ለሚመሩት ያር ላፒድ ተሰጠ፡፡

በቤኒያሚን ኔታንያሁ ላይ ተቃውሞ መነሳት የጀመረው በግራ ክንፍና በመሀል ሰፋሪ ብቻ ሳይሆን፣ በቀኝ ክንፍ ፓርቲዎችም ጭምር መሆኑ ከሥልጣናቸው ለመነሳታቸው እንደ አንድ ምክንያት ይጠቀሳል፡፡ በተለይ ከሊኩድ ፓርቲያቸው ጋር ተመሳሳይ የፖለቲካ ርዕዮት የሚከተሉት ቀኝ ዘመም ፓርቲዎችም ኔታንያሁ ላይ ተቃውሞ ማሰማታቸው ለስንብታቸው ምክንያት ነው፡፡

​​​​​​​የቤኒያሚን ኔታንያሁ የሥልጣን ስንብት

የሊኩድ ቀኝ እጅ የነበረው ያሚኒያ ፓርቲ ያለው መቀመጫ ሰባት ቢሆንም፣ ለኔታንያሁ ወሳኝ ነበር፡፡ ሆኖም በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠውን ፓርቲ የሚመሩት ሚስተር ላፒድ የያማኒያን ፓርቲ የመጀመርያ ግባቸው ኔታንያሁን ከሥልጣን ማንሳት ወደነበሩ ሌሎች ፓርቲዎች መሳባቸውና መጣመራቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩን የተከታታይ የ12 ዓመታት ሥልጣንን ለማክተም ወሳኝ ሆኗል፡፡

ሚስተር ላፒድ የያማኒን ፓርቲ ወደ ጥምረታቸው ለማምጣትም ለሳምንታት  ከፍተኛ ድርድር ከተደረገ በኋላ አብላጫ ድምፅ ለማግኘት የሚፈለገውን 61 መቀመጫ በመሙላት ስምንት ፓርቲዎች ተጣምረው በፊርማቸው አረጋግጠዋል፡፡ ይህ የሆነው ከ14 ቀናት በፊት ሲሆን፣ ውሳኔያቸውን ያሳወቁት የአገሪቱ ፓርላማ ጥምረት ፈጥሮ መንግሥት ለመመሥረት ያስቀመጠው ቀነ ገደብ ሊያበቃ ግማሽ ሰዓት ያህል ሲቀረው እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሁለት ዓመታት ውስጥ በተደረጉት አራት ምርጫዎች ውስጥ አልፈው የሥልጣን መንበሩን የያዙት አዲሱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት፣ ‹‹በእስራኤል ታሪክ ታይቶ አይታወቅም›› የተባለውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት ፈጥረው ነው፡፡

እሑድ ሰኔ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. በተካሄደ ድምፅ የመስጠት ምርጫ አክራሪው የቀኝ  ክንፍ 60 ድምፅ በማግኘት ነው ያሸነፈው፡፡ የኔታንያሁ ሊኩድ ፓርቲ 59 ድምፅ ሲያገኝ አንድ ድምፅ ተዐቅቦ መኖሩ ለቤኔት ሥልጣን አጎናፅፏል፡፡

የእስራኤል ፓርላማ (ካንሴት) ምርጫ ከተጠናቀቀ በኋላ ተሰናባቹ ኔታንያሁ የሚስተር ቤኔትን እጅ ጨብጠዋል፡፡ ባደረጉት ንግግርም፣ ‹‹ተመልሰን ወደ ሥልጣን እንመጣለን›› ብለዋል፡፡

የቀኝ ክንፉ ሊኩድ ፓርቲ መሪና ተቃዋሚ ሆነውም የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡ 60 ድምፆች በማግኘት ድል የተቀናዳጀው የአዲሱ ጥምረት መሪና ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኔት ባደረጉት ንግግር፣ ‹‹የሚለቀስበት ቀን አይደለም፡፡ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመንግሥት ለውጥ የተደረገበት ነው፡፡ ማንም እንዳይፈራ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን፡፡ ምሽቱን በጭፈራ ለማሳለፍ የምትፈልጉ በሌሎች ሕመም አትደንሱ፡፡ እኛ ጠላቶች አይደለንም፡፡ አንድ ሕዝብ ነን፤›› ብለዋል፡፡

የ49 ዓመቱ ቤኔት፣ የያሚና ፓርቲ መሪ ሲሆኑ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የሚዘልቁት እስከ 2023 መስከረም ነው፡፡ የሁለት ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸውን ሲጨርሱና የስምንት ፓርቲ ጥምረት ሲመሠርቱ ሥልጣን ለመጋራት በተስማሙት መሠረት፣ ሥልጣኑን ለመሀል ዘመሙ የሽ አቲድ ፓርቲ መሪ ያር ላፒድ ያስረክባሉ፡፡

መንግሥታቸው ለሁሉም ሕዝብ እንደሚሠራ የገለጹት ቤኔት፣ በትምህርት፣ በጤናና የተንዛዙና የማያስኬዱ ሥራዎችን ለማስቀረት የሚያስችል ሪፎርም እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡

ሚስተር ቤኔት ለእነዚህ ዘርፎች ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሠሩ ቢያስታውቁም፣ የፍልስጤም ኢየሩሳሌም ይገባኛል ጥያቄ ከፓርቲያቸው ጥምረት አንፃር ፍጭት ውስጥ ሊከታቸው እንደሚችል ይገመታል፡፡

ከስምንቱ ጥምር ፓርቲዎች በርዕዮተ ዓለም ደረጃ ሰፊ ልዩነት ያላቸው አሉ፡፡ በጥምረቱ ውስጥ የሚገኘውና የመጀመርያው ገለልተኛ ዓረብ ፓርቲ የሆነው ራማ ፓርቲ እንዲሁም ግራ ክንፍ ‹‹ነን ዓረብ እስራኤል ፓርቲ›› እስራኤል በፍልስጤም ላይ ባላት ፖሊሲ ላይ ሊገዳደሩ የሚችሉ ናቸው፡፡

በእስራኤል የአይሁድ ሠፈራን የሚቃወሙና የማይቃወሙ መኖር ሌላው ክርክር ሊያስነሳ የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ በሶሻል ፖሊሲ ላይ የግብረ ሰዶማውያን መብት እንዲጠናከር የሚፈልጉና የማይፈልጉ ፓርቲዎች መኖራቸውም ቤኔት በሚመሩት ጥምረት መካከል ልዩነት ከሚንፀባረቅበት አጀንዳ ይጠቀሳል፡፡

አንዳንድ ፓርቲዎች በአማኞች ላይ የሚጣሉ ገደቦችን ማላላት የሚፈልጉ መሆናቸው፣ በፓርቲዎቹ መካከል ፍጭት የሚፈጥሩና ሚስተር ቤኔትን የሚፈትኑ ጉዳዮች ይሆናሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በተለይ ቤኔት በፍልስጤም ላይ ያላቸው አቋም ከኔታንያሁም የከረረና ስንዝር መሬትም ለመስጠት ሆነ የፍልስጤምን ጥያቄ ለመቀበል የማይፈልጉ መሆናቸው ጥምረታቸውን ይፈትነዋል፡፡

እስራኤል በዌስት ባንክና በምሥራቅ ኢየሩሳሌም ከግማሽ ሚሊዮን በላይ አይሁዶችን ማሥፈሯም አሁን አገሪቱን በሚመራው ጥምር ፓርቲ ውስጥ መከራከሪያ አጀንዳ ሆኖ መነሳቱ አይቀሬ ነው፡፡

ይህ በፍልስጤምና በእስራኤል በኩል ለዓመታት መወዛገቢያ ሆኖ የከረመ ጉዳይ በቤኔት ቦታ የማይሰጠውና የማይቀበሉት ቢሆንም ከጥምሩ ፓርቲያቸው ውስጥ አጀንዳው መምጣቱ አይቀርም፡፡

 

(ጥንቅር በምሕረት ሞገስ)

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...