Monday, July 15, 2024

[ክቡር ሚኒስትሩ ከምርጫ ቦርድ ዕውቅና ውጪ ተቋቋሙ የተባሉትን የምርጫ ጣቢያዎች በተመለከተ አማካሪያቸውን ማብራሪያ እየጠየቁ ነው]

 • እንደገመትነው የምርጫ ጣቢያዎቹቦርዱ ናቸው አይደል
 • እንደገመትነው አይደለም ክቡር ሚኒስትር።
 • የመንግሥት ናቸው እንዳትለኝ?
 • ምንም ማድረግ አልችልም ክቡር ሚኒስትር፣ በመንግሥት መዋቅር የተቋቋሙ ናቸው። 
 • የት አካባቢ ያለው የመንግሥት መዋቅር ነው ይህንን ያደረገው?
 • አብዛኛውን ያቋቋመው በደቡብ የሚገኝ ዞን ነው። 
 • ጤና ጣቢያ ያቋቁሙ መስሏቸው መሆን አለበት፡፡ 
 • እንደዚያ  እንዳይባል የተሻለ ጤና ጣቢያ ያላቸውም አቋቁመዋል።
 • የት?
 • በአዲስ አበባ።
 • እንዴት ሊሆን እንደቻለ ያገኛችሁት መረጃ አለ?
 • አዎ፣ መረጃዎችን ሰብስበናል።
 • እሺ?
 • 70 በላይ የሚሆኑትን ጣቢያዎች ያቋቋመው የደቡብ ዞን አመራር ኃላፊነቱን እንደተወጣ ነው የሚከራከረው።
 • የሚከራከረው?
 • አዎ ክቡር ሚኒስትር። 
 • እንዴት?
 • ቦርዱ በዞኑ ጀምሮ የነበረውን የምርጫ ጣቢያ የማቋቋም በፀጥታ ችግር ምክንያት ስላቋረጠ ነው የሚሉት አመራሩ።
 • ቦርዱ ስላቋረጠ ምን?
 • ቦርዱ ስላቋረጠ ዞኑ ያቋቁማል ብለው አቋቋሙ።
 • ምን? እንዴት ይሆናል?
 • ክቡር ሚኒስትር ቦርዱ መረጃውን ባያወጣና ጉዳዩ ባይታወቅ ኖሮ ሌላም ነገር ሊከሰት ይችል እንደነበር ነው የተረዳነው።
 • ምን ይከሰት ነበር?
 • ምርጫ ያካሂዱ ነበር። 
 • ይህ ሁሉ ሲሆን ከፍተኛው የመንግሥት መዋቅር ጉዳዩን ያውቅ ነበር
 • ዞኑ ለአካባቢው ከፍተኛ የመንግሥት መዋቅር ነበር ሪፖርት ያቀርብ የነበረው ግን
 • ግን ምን?
 • እነሱ ከፍተኛ የመንግሥት መዋቅር የሚሉት ስለትክክለኛ የምርጫ ሒደት የሚያውቀው ውስን ነገር ነው። 
 • የትኛው የመንግሥት መዋቅር ነው?
 • ኮማንድ ፖስቱ ነው። 
 • ሪፖርት የሚያቀርቡት ለእነሱ ነበር?
 • ክቡር ሚኒስትር ቦርዱ የተፈጠረውን ስህተት ለማስተካከል ሞክሮ ነበር። 
 • በሚዲያ ከሚለቁት ይሻል ነበር፣ እሺ?
 • አዎ፣ ዞኑ ጣቢያዎቹን እንዲያስረክበው ቦርዱ ጠይቆ ነበር፡፡
 • እሺ? ዞኑ ምን አለ?
 • ለምርጫ ቦርድ አላስረክብም፣ የማስረክበው ለሌላ ነው አለ።
 • ለሌላ ለማን?
 • ለኮማንድ ፖስቱ። 
 • እንዴት ያለ ነገር ነው? እኔ ምለው?
 • አቤት ክቡር ሚኒስትር?
 • ከመቶ ሺሕ በላይ ካድሬዎቻችን በምርጫ ጉዳይ ላይ ሠልጥነው አልነበረም እንዴ
 • ልክ ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • ታዲያ እንዴት ይህንን ስህተት ሊሠሩ ቻሉ?
 • ስህተቱን የሠሩት የሠለጠኑት አይደሉም። 
 • የትኞቹ ናቸው ታዲያ?
 • ያልሠለጠኑ መቶ ሺዎች።

[የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ምርጫውን በተመለከተ በየለቱ የሚያቀርበውን ሪፖርት ይዞ ቢሮአቸው በመገኘት ለዕለቱ ሁለት መረጃዎችን እንደሚያቀርብ በመግለጽ ማብራሪያውን ጀምሯል]

 • ክቡር ሚኒስትር ለዛሬ የተዘጋጁት ሁለት መረጃዎች ሲሆኑየመረጃዎቹ ይዘት አሉታዊም አዎንታዊም መሆኑን ከወዲሁ አሳውቃለሁ።
 • ከአዎንታዊው ጀምር።
 • አዎንታዊው መረጃ የውጪ ጠላቶቻችን በመጨረሻ እጃቸውን እየሰጡ መሆኑን የሚያበስር ነው።
 • ደስ የሚያሰኝ ዜና ነው። መጀመርያም ኢትዮጵያን መጠምዘዝ እንደማይችሉ ነግረናቸው ነበር፣ እሺ ምንድነው ያደረጉት?
 • ማዕቀብ እስከ መጣል የደረሱት እነዚህ ኃይሎች በመጨረሻ የሽንፈት ፅዋቸውን ማንሳት ጀምረዋል።
 • ማዕቀቡንስ አነሱት?
 • ማዕቀቡን አይደለም ያልኩት ክቡር ሚኒስትር። 
 • ምንድን ነው አነሱ ያልከው?
 • የሽንፈት ፅዋቸውን እያነሱ እንደሆነ ነው የገለጽኩት።
 • ፅዋ አነሱ ይለኛል እንዴ… አታፍርም? 
 • ያልተገባ ጉጉት ፈጥሬ ከሆነ ይቅርታ ያድርጉልኝ ክቡር ሚኒስትር።
 • አሁንም ያልተገባ ጉጉት እየፈጠርክ ነው፣ ለምን እንደነሱ በቀጥታ አትናገርም?
 • እሺ ክቡር ሚኒስትር፣ ማዕቀብ እስከ መጣል የደረሱት እነዚህ ኃይሎች ከምርጫ በፊት ብሔራዊ ውይይት የሚለውን አቋማቸውን ነው ያነሱት። 
 • ምን ይላል ይኼ!? ይህንን ነው አዎንታዊ መረጃ ያልከው?
 • አዎ ክቡር ሚኒስትር። ትልቅ ድል እንደሆነ ነው የሚሰማኝ።
 • አንተ የሚሰማህን ትተህ አሉታዊ ያልከውን ሁለተኛ መረጃ ቀጥል።
 • እሺ ክቡር ሚኒስትር። ሁለተኛው መረጃ አሉታዊ የሚሆነው በቀጥታ የእርስዎን የምርጫ ጣቢያ የሚመለከት በመሆኑ ነው። 
 • ምንድነው እሱ?
 • በሌሎች አካባቢዎች የ4G ኤልቲኢ አገልግሎት ሲስፋፋ እርስዎ የሚወዳደሩበትን አካባቢ በመዝለሉ ቅሬታ ፈጥሯል። 
 • እንዴት ሊዘለል ቻለ? 
 • አዋጭ ባልሆኑ አካባቢዎች ቴክኖሎጂውን እያስፋፉ ባለመሆኑ፣ በዚህ አካባቢም ቴክኖሎጂውን እንደማይዘረጉ ነው የሚገልጹት።
 • አዋጭ ባለመሆኑ አይደለም፣ ይህ ሌላ ነገር ነው፡፡
 • ሌላ ነገር ነው ያሉት?
 • አዎ ይህ የምርጫ ደባ ነው፣ እና ምን መፍትሔ አበጃችሁ?
 • እርስዎ በሚሰጡን አቅጣጫ እንፈጽማለን ብለን እስካሁን ምንም አላደረግንም። 
 • እንዴት? ደባውን እናንተም ቀጠላችሁበት?
 • ክቡር ሚኒስትር እንደዚያ አይደለም፡፡
 • ምንም ማብራሪያ አልፈልግም፣ የምለው በአስቸኳይ እንዲፈጸም ብቻ ነው የምፈልገው።
 • ጥሩ ክቡር ሚኒስትር፣ ያሉትን እናስፈጽማለን።
 • ያላቸውን አቅምና የሰው ኃይል ተጠቅመው ከምርጫው በፊት ቴክኖሎጂውን በአካባቢው እንዲዘረጉ ይደረግ።
 • እንዳሉት ይሆናል ክቡር ሚኒስትር።
 • አድምጠኝ፡፡
 • እየተቀበልኩ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡ 
 • የቴክኖሎጂ ማስፋፊያው በልዩ ሁኔታ እኔ በተገኘሁበት እንዲመረቅ ሁሉም ነገር ይሰናዳ።
 • እንዳሉት ይሆናል ክቡር ሚኒስትር።
 • ጨርሻለሁ! 

 

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...

በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ሳቢያ አጠቃላይ ገበያው እንዳይታመም ትኩረት ይደረግ!

መንግሥት ነዳጅን ከመደጎም ቀስ በቀስ እየወጣ ነው፡፡ ለነዳጅ የሚያደርገውን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ሳይገኝ ከቀረው አንድ የተቋማቸው ባልደረባ የሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ አባልን አስጠርተው እያናገሩ ነው]

ለምንድነው በዚህ አገራዊ ፋይዳ ባለው ፕሮግራም ላይ ያልተገኘኸው? ክቡር ሚኒስትር ህሊናዬ አልፈቀደልኝም። መቃወምና መተቸት ብቻ ውጤት የሚያመጣ መስልዎህ ከሆነ ተሳስተሃል። አልተሳሳትኩም ክቡር ሚኒስትር? ቆይ የመጀመሪያ ዓመት የችግኝ ተከላ...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላነጋግርህ የፈለኩት ክቡር ሚኒስትር፡፡ እርስዎማ ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግዎትም፣ ምን ገጠመዎት? እኔማ ምን ይገጥመኛል አንተኑ ልጠይቅህ እንጂ? ምን? እውነት ለመናገር የማየው ነገር አሳስቦኛል፡፡ ይንገሩኝ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በቢሯቸው ሆነው ከአማካሪያቸው ጋር ስለወቅታዊ ጉዳዮች እየተነጋገሩ ነው]

ትናንት የሆነውን ሰሙ ክቡር ሚኒስትር? አልሰማሁም፣ ምን ሆነ?  ኬንያውያን የአገሪቱን ፓርላማ ጥሰው መግባታቸውን አልሰሙም? ኧረ አልሰማሁም።  የፓርላማውን በር ጥሰው ገብተው አንደኛውን ክፍል በእሳት አያያዙት፡፡  ምንድነው ምክንያቱ?  የአገሪቱ መንግሥት ያቀረበው አዲስ...