Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ሆ!   ብሎ     ሀ¡

ትኩስ ፅሁፎች

በአሰፋ ጉያ

የጥቅምቱ ድግስ

እንደ ንፋስ ንፍስ

እንደ ጎርፉ ግስግስ

ትርምስ – ትርምስምስ

እዛም – እዚም ድርምስ

ባህርማዶ ድርስ

መሀል አገር ምልስ

ሆ! ብሎ ወደፊት! አራት ኪሎ ድርስ

ሀ¡ ብሎ የኋሊት¡ አራት ቦታ ግምስ፡፡

የሸገር – ያድሱ

የምርጫ ድግሱ

በዲስኩር ታጅቦ

በቃላት ተውቦ

ጀግንነት ጀግኖ ሆ! ብለው

ሆ! ብለው

አንድ ላይ ፎክረው

ምለው ተማምለው

‹‹አራት ኪሎ›› ብለው

‹‹ከቦታው›› ሲደርሱ አራት ላይ ተከፍለው

የኋሊት ነጎዱ ሀ¡ ብለው ሀ¡ ብለው፡

ድንገት ተሰባስበው

ከተማን ከትመው

‹‹ምርጫ! ምርጫ! ብለው

ግለው ተጋግለው

ፈነዱ ቸኩለው፡፡

ሆ! ብለው ጀምረው

የኋሊት ተጓዙ ሀ¡ ብለው

ሀ¡ ብለው፡፡

ሰሜን ነህ! ደቡብ ነህ

ምሥራቅ ነህ! ምዕራብ ነህ

ወጣት ሽማግሌ ብለው ተናንቀው፣

ግራ ነህ – ቀኝ ነህ – መሀል-ተባብለው

ሰላም – ብረት ብለው

ጣት ለጣት ተቃስረው

የኋሊት ተጓዙ አራት ላይ ተከፍለው

ሀ¡ ብለው ሀ¡ ብለው፡፡

 

  1. ሰኞ ከቀኑ 8 ሰዓት በለንደን የሰዓት አቆጣጠር እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 7 ቀን 2005፣ ጥቅምት 28 ቀን 1998 ዓ.ም.፡፡ በፈረንሳይ የዘር፣ የቀለምና የሃይማኖት ቁርሾ ያገረሸበት፣ የኢኮኖሚ ጥያቄ የጦዘበትና በፈረንሳይ ከተሞች አመጽ የፈነዳበት ሰሞን፣ በለንደን ከተማ ለጋይፎን መታሰቢያ ሰማዩ በርቺት የተጠቀጠቀበት ማግስት፣ በአገሬ የመንግሥትና የተቃዋሚዎች ፍጥጫ በከተሞች የተካረረበት ወቅት ነበር፡፡

አሰፋ ጉያ ‹‹ሰምና ወርቅ›› (2012)

****

መኖር ሲያስጠላ

ጥያቄ፡- ‹‹ኰምዩኒስት ፓርቲው ሥልጣን ከያዘ ወዲህ በሕይወት መኖር አስጠልቶኛል፡፡ ራሴን ላጠፋ የምችልበትን መንገድ ልትነግረኝ ትችላለህ?

መልስ፡- ‹‹በፓርቲውና በሕዝቡ መካከል ያለው ትልቅ ገደል ውስጥ ዘለህ መግባት ትችላለህ፡፡››

****

አጭሩ ቀልድ

ጥያቄ፡- ‹‹እጅግ በጣም አጭሩን ቀልድ ልትነግረኝ ትችላለህ?››

መልስ፡- ‹‹እንዴታ፣ ኰምዩኒዝም ነዋ፡፡››

****

‹‹ኦ! ሕዝብን ነው?››

ባንድ ወቅት ሳይንቲስቶች ሙከራ ማካሄድ በመፈለጋቸው ከተለያዩ አገሮች ሁለት ወንዶችና አንዲት ሴት በማቧደን ሰው በማይኖርበት ደሴት ለያይተው አሰፈሯቸው፡፡ ከዚያም ከአንድ ዓመት በኋላ ሊጎበኟቸው ሄዱ፡፡

እንግሊዛዊው ሰውዬ ከባለቤቱ ጋር በሰላም በመኖር ላይ የነበረ ሲሆን፣ ሁለተኛውን ሰውዬ ከሴቲቱ ጋር ማንም ስላላስተዋወቀው አርፎ በብቸኝነት ኑሮውን ይገፋል፡፡

ሦስቱ ፈረንሳዮች በአንድነት እየኖሩ ነበር፡፡

ኩራተኞቹ አይሁዶች አንዲት ተጨማሪ ሴት ገዝተው ሁለት ጥንዶች በመሆን ይኖራሉ፡፡

ሳይንቲስቶቹ በመጨረሻ ወደ ሩስያውያኑ ሄዱ፡፡ በዚያ ሁለት ወንዶች ከቢሮ ጠረጴዛቸው በስተጀርባ ተቀምጠው አዩ፡፡ ጠረጴዛቸው ጫፍ ላይ ‹‹ፕሬዚዳንት›› እና ‹‹ምክትል ፕሬዚዳንት›› የሚሉ ጽሑፎች ተቀምጠው ይታያሉ፡፡ ሴቲቱ ግን በአካባቢው አትትይም፡፡ ሳይንቲስቶቹ በመገረም የት እንዳለች ጠየቁ፡፡

‹‹ኦ! ሕዝብን ነው? እዚያ ማዶ አለችላችሁ፡፡ ማሳውን እየቆፈረች ነው፡፡››

በሶሺያሊዝምና በኰምዩኒዝም መካከል የሚገኘው የሽግግር ሥርዓት አልኰሊዝም ይባላል፡፡

****

መቅደሙ ይበጃል

ሰውዬ እየሮጠ ወደ ሩስያው የስለላ ድርጅት ኬጂቢ ቢሮ ሄዶ፣ ‹‹በቀቀኔ (ፓሮቴ) ጠፍቶብኛል›› አለ፡፡

‹‹ይኼ እኛን አይመለከትም፡፡ ፖሊስ ጣቢያ ሄደህ አመልክት፡፡››

‹‹ይቅርታ ጌታዬ፣ እዚያ ማመልከት እንዳለብኝ አውቃለሁ፡፡ እዚህ የመጣሁት ከበቀቀኔ ጋር በሐሳብ እንደምንለያይ ለመግለጽ ነው፡፡››

አረፈ ዓይኔ ሐጐስ ‹‹ፖለቲከኞች እፈሩ ቀልድና ቁምነገር››

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች