ቡና ቤቶች በምርጫ ቀን የሚዘጉት ሰዎች በሞቃት ድምፃቸውን እንዳያባክኑ መሆኑ ይገባኛል፡፡ ቤተ መጻሕፍት ግን ለምን ይዘጋሉ?
- አርተር ዲ ህላቫቲ
******
ሰዎች ከአደን በኋላ፣ በጦርነት ጊዜ፣ ወይም ከምርጫ በፊት የሚዋሹትን ያህል ፈጽሞ አይዋሹም፡፡
- ኦቶ ቮን ቢስማርክ
*****
ዴሞክራሲ አከራካሪ ጉዳዮች በሌሉበትና ዕጩዎች ተመሳሳይ ሊሆኑ በሚችሉበት ሁኔታ ብዙ ወጪ ፈሶ በርካታ ምርጫዎች የሚካሄዱበት መሆኑ ይታወቃል፡፡
- ጐር ቪዳል
*****
ምርጫ እየተቃረበ ነው፡፡ ሁለንተናዊ ሰላም እንዲሰፍን በመታወጁም ቀበሮዎች የዶሮዎችን ሕይወት ለማራዘም ከልብ የመነጨ ፍላጐት የሚያሳዩበት ጊዜ ነው፡፡
- ቲ.ኤስ.ኢልየት
*****
ምርጫ የጦርነትን ያህል (ምንም እንኳን ደም ባይፈስም) አስፈሪና አስጠሊታ እንዲሁም የሞራል ዝቅጠት የሚንፀባረቅበት ነው፤ ሁሉንም ሰው ለማጉደፍና ለማጨመላለቅ የሚያስችል በቂ የቆሻሻ ገንዳ ያለበት፡፡
- ጆርጅ በርናርድ ሾው
******
ሕዝቡ ምርጫ መካሄዱን ካወቀ ይበቃል፡፡ ድምፁን ስለሰጠ ምንም ነገር አያመጣም፡፡ የምርጫ ካርዱን የሚቆጥሩት ወሳኞቹ ሰዎች የኛ ናቸው፡፡
- ጆሴፍ ስታሊን (አምባገነኑ የሶቭየት ኅብረት መሪ)
- አረፈ ዓይኔ ሐጐስ ‹‹ፖለቲከኞች እፈሩ ቀልድና ቁምነገር››