Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአፍሪካ ኅብረት ኢትዮጵያን ሳያማክል ያቋቋመውን የምርመራ እንቅስቃሴ እንዲያቆም ጥሪ ቀረበ

የአፍሪካ ኅብረት ኢትዮጵያን ሳያማክል ያቋቋመውን የምርመራ እንቅስቃሴ እንዲያቆም ጥሪ ቀረበ

ቀን:

በአፍሪካ ኅብረት ሥር የሚገኘው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ለሚደረገው ገለልተኛ ምርመራ ባቋቋመው ኮሚሽን ውስጥ ኢትዮጵያን አለማካተቱ መንግሥት ቅሬታ እንደፈጠረበትና ኮሚሽኑም የጀመረውን እንቅስቃሴ እንዲያቆም ጥሪ ቀረበ፡፡

ይህ የተገለጸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግንቦት 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ላይ ነው፡፡ ሚኒስቴሩ በመግለጫው እንዳስታወቀው የአፍሪካ ኅብረት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር ተያይዞ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ በጋራ ምርመራ ለማድረግ ሲያግባባ የቆየ ሲሆን፣ ለቀረበው ጥያቄ ኮሚሽኑ ያቋቋመው የተናጠል መርማሪ ኮሚሽን የሕግ መሠረት የሌለውና መንግሥት እንዲደረግ ይሁንታ ከሰጠው አግባብ ውጪ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በመግለጫው እንዳስነበበው የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት በየካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ከፍተኛ የአገር መሪዎችና የአባል አገሮች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ባደረጉት ስብሰባ፣ ኢትዮጵያ ከአኅጉሩ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በጥምረት በትግራይ ክልል ተፈጽመዋል ስለተባሉት የመብት ጥሰቶች ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛነቷን እንደገለጸች አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም  ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽንና የኅብረቱ፣ የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ሊቀ መናብርት ጋር  ተከታታይ ውይይቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን ጨምሮ ገልጿል፡፡

በተከታታይነት ከተደረገ ውይይት በኋላ ኮሚሽኑ ኢትዮጵያ በጋራ ምርመራ ለማድረግ ያቀረበችውን ሐሳብ መቀበሉን የሚገልጽ ደብዳቤ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መጻፉን መግለጫው አስታውሶ፣ ሆኖም ግን የአፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለሚደረገው ምርመራ በተናጠል ያቋቋመው ኮሚሽን ኢትዮጵያን በማግለል የተዋቀረ መሆኑ መንግሥትን ቅሬታ ውስጥ ከመክተቱ ባሻገር፣ ሕጋዊ አካሄድን የተላለፈ እንደሆነ ሚኒስቴሩ ያወጣው መግለጫ ያስረዳል፡፡

የአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከሳምንት በፊት በበይነ መረብ ባከናወነው 32ኛው ልዩ ጉባዔ በትግራይ ክልል ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ሌሎች ጉዳዮችን ሁኔታ የሚያመላክት አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም ከውሳኔ ላይ መድረሱን ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ አስታውሷል፡፡

በኅብረቱ የተቋቋመው ኮሚሽን መቀመጫውን በጋምቢያ ርዕስ ከተማ ባንጁል አድርጎ ሥራውን እንደሚጀምር፣ በመቀጠል በኢትዮጵያና አጎራባች አገሮች የሚመለከታቸውን አካላት በምርመራው እየሸፈነ ለሦስት ወራት እንደሚቆይና የምርመራው ጊዜም እንደሁኔታው ታይቶ የመራዘሙ ሁኔታ ታሳቢ መደረጉን የወጣው መግለጫ ያሳያል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሌላ በኩል በመግለጫው የጋራ ተልዕኮን ቸል በማለት በኮሚሽኑ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ጠቃሚ ካለመሆናቸው ባሻገር በአኅጉሪቱ በሚገኙ አገሮች ላይ ከሰብዓዊና የዜጎች መብት ጥበቃ ጋር ተያይዞ የሚደረጉ ገለልተኛ ምርመራዎችን እንቅስቃሴ የሚያሳንሱ እንደሆኑ አስታውቋል፡፡ በአንድ አካል ፍላጎት የሚደረጉ ምርመራዎችም የተነሱበትን ዓላማ ከማሳካት ይልቅ ለውዥንብር የሚዳርጉ እንደሆኑም ሚኒስቴሩ ጨምሮ አስረድቷል፡፡

ኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን በጋራ ለሚደረጉ ምርመራዎች ዝግጁ መሆኗን በድጋሚ ለመግለጽ እንደምትሻ ያስታወቀው የሚኒስቴሩ መግለጫ፣ በመሆኑም የአፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ካለኢትዮጵያ መንግሥት ዕውቅናና ፈቃድ ያቋቋመውን የምርመራ እንቅስቃሴ በማቆም አስፈላጊውን የሕግ አካሄድ በተከተለ መልኩ ያቀደውን ምርመራ ለማድረግ እንዲንቀሳቀስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...