Wednesday, May 22, 2024

የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ምርጫ የመታዘብ ሥልጣንና የምርጫ ቦርድ የይለፍ ካርድ ክልከላ ሲመዘን

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

‹‹የኢትዮጵያ ሰባዓዊ መብት ኮሚሽን እንዳይታዘብ የተከለከለበትን ምርጫ ምኑን ምርጫ እንደሚሉት እኔ አላውቅም።›› 

ምርጫ ቦርድ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የምርጫ መታዘቢያ የይለፍ ካርድ የመከልከሉን ዜና የተመለከቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ተከታታዮች፣ ዜናው በተጋራበት የሪፖርተር ማኅበራዊ ገጽ የአስተያየት መስጫ ሳጥን ላይ የተሰማቸውን ምክንያታዊ አስተያየት አስፍረዋል። 

ከላይ የተጠቀሰውም ከተሰጡት አስተያየቶች መካከል አንዱ ሲሆን ደረጄ ነገራ የተባሉ አስተያየት ሰጪ ያቀረቡት ነው። ሌሎች የሪፖርተር አንባቢያን ደግሞ የሚከተሉትን ከታች የተቀመጡ አስተያየቶችን አጋርተዋል።

‹‹ቦርዱ ምን ነካው? ሕግ ምናምን ብሎ ከማሰናከልምርጫው ሒደት ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ተፅዕኖ እስካልኖረ ድረስ ለኮሚሽኑ ቢፈቅድለት ተገቢ ይመስለናል፡፡ አሊያ ቦርዱ የመንግሥትን ፊት ወይም የውስጥ መስመርን ትዕዛዝ ተቀብሎ የሚሠራ እንዳይመስልበት›› በማለት ተስፋዬ አባይነህ የተባሉ አስተያየት ሰጪሳባቸውን አስፍረዋል። 

እመቤት ተሾመ የተባሉ ሌላ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 210/92፣ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1224/2012

የኮሚሽኑን ሥልጣንና ተግባር እንደሚደነግግ በመጠቆም በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 11 ሥ ኮሚሽኑ በምርጫ ወቅት የሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅን ክትትል የማድረግ ሥልጣንና ተግባር እንደሚኖረው መደንገጉን ይገልጻሉ። 

ይህንን አዋጅ እንደማስረጃ በመጥቀስም፣ ‹‹የቀድሞ ዳኛ፣ የአሁን ምርጫ ቦርድ ኃላፊ ብርቱካን ሚደቅሳ ከላይ የተጠቀሰው አንቀጽ ምን ማለት ይመስልዎታል›› በማለት አስተያየታቸውን በጥያቄ መልክ ያነሳሉ።

በማከልም ኮሚሽኑ ለሥራው ቅልጥፍና ትብብር ጠይቆ እንደሆነ እንጂ የዜጎች የመመረጥና የመምረጥ መብት እንዴት እየተፈጸመ እንደሆነ በምርጫ ጣቢያ ተገኝቶ መከታታል በሕግ የተሰጠው ሥልጣን መሆኑን ይከራከራሉ፡፡

‹‹እንደኔ ከሆነ ምርጫ ቦርድ መብት አስፈጻሚ ተቋም ስለሆነ ኮሚሽኑ ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ ወይም ፍቃድ በምርጫ ጣቢያ ተገኝቶ መከታተል ሥልጣኑ ነው፡፡ ማድረግ ያለበትም ፍቃድ ወይም ትብብር መጠየቅ ሳይሆን መታወቂያ የያዙ ባለሙያዎቹን በምርጫ ጣቢያ እንዲገኙ ማድረግ ብቻ ነው›› በማለት እመቤት ይሞግታሉ። 

ምርጫ ቦርድም የኮሚሽኑን ሥልጣን አውቆ የኮሚሽኑ ባለሙያዎች ሲመጡ ትብብር እንዲደረግላቸው ለምርጫ አስፈጻሚዎች ቀጭን ትዕዛዝ መስጠት እንዳለበት፣ ይህንንም የሚያደርገው ግዴታው በመሆኑ እንደሆነ በመጥቀስ ለኮሚሽኑ አለመተባበር የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል ጭምር መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

ገለታ ጋሞ የተባሉ ሌላ አስተያየት ሰጪ ከላይ የተመለከተውን አስተያየት በተወሰነ መልኩ የተጋሩ በሚመሰለው አስተያየታቸው የሚከተለውን ብለዋል፣ ‹‹ቦርዱ ለኮሚሽኑ መታወቂያ መከልከሉ ትክክል ነው። ኮማሽኑ በራሱ ሥልጣን (ማንዴት) መብቶች መከበራቸውን ወይም መጣሳችውን መከታተል ሲችል ፈቃድ መጠየቅም አልነበረበትም››። 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ መርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት፣ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የይለፍ ካርድ ጥያቄ በሰጡት የጹሑፍ ምላሽ በአዲሱ የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ኮሚሽኑ በምርጫ ወቅት የሰብዓዊ መብት፣ ክትትል ለማድረግ ሥልጣን  እንደተሰጠው የሚገነዘቡ መሆኑን ገልጸዋል። 

ነገር ግን በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የሥነ ምግባር አዋጅ ላይ በምርጫ ወቅት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች መግባት ወይም መገኘት እንዲችሉ በቦርዱ የይለፍ ፈቃድ ወይም ባጅ ይሰጣቸዋል ተብለው ከተገለጹት ውስጥ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባለመጠቀሱ የይለፍ ካርዱን ቦርዱ ለመስጠት እንደሚቸገር ገልጸዋል።

በዚህ አዋጅ መሠረትም በምርጫ ጣቢያዎች ለመገኘት እንዲችሉ ቦርዱ የይለፍ ካርድ ይሰጣቸዋል ተብለው የተጠቀሱት የፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች፣ የምርጫ ታዛቢዎችና ጋዜጠኞች መሆናቸውን ጠቁመዋል። 

‹‹በመሆኑም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋዜጠኛ ወይም ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲና የግል ወኪል ስላልሆነ ቦርዱ የይለፍ ካርድ የሚሰጥበት የሕግ አግባብ ባለማግኘቱ ጥያቄውን ተቀብሎ ማስተናገድ ያልቻለ መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን›› በማለት በአቶ ውብሸት አያሌው የተላከው ደብዳቤ ያጠቃልላል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (/) የቦርዱ ክልከላ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ ሰኔ 8 ቀን 2013 ዓ.ም. በላኩት ደብዳቤ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ በዚሁ ደብዳቤያቸውም ቦርዱ ውሳኔውን እንዲያስተካክል ጠይቀዋል።

በተሻሻለው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ መሠረት ለኮሚሽኑ ከተሰጡ ሥልጣኖች አንዱ በምርጫ ወቅት የሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅን በተመለከተ ክትትል ማድረግ እንደሆነ በማስታወስ ይህንን ኃላፊነቱን ለመወጣትም በምርጫ ጣቂያዎች መገኘትን የሚጠይቅ እንደሆነ አስረድተዋል።

‹‹ኮሚሽኑ የተሰጠውን ኃላፊነት የሚወጣው በምርጫ ጣቢያዎች ጭምር በመገኘትና የክትትልና የምልከታ ሥራ በማካሄድ ነው። ለዓብነትም የምርጫ ጣቢያዎችና የምርጫው ሒደት ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ መሆኑን ለማረጋገጥ በምርጫ ጣቢያ ውስጥ በመገኘት በምልክታና ክትትል የሚጣራ ነው፤›› ብለዋል።

በተሻሻለው የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀጽ 39 መሠረት ማንኛውም አካል ለኮሚሽኑ ሥራ አስፈላጊውን ድጋፍ የማድረግ ግዴታ ያለበት መሆኑን የጠቀሱት ዋና ኮሚሽነሩ፣ ቦርዱ የኮሚሽኑን የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ሥራ ማገዝ ማቀላጠፍና መተባበር የሚጠበቅበት ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል።

በአዋጅ ሥልጣን የተሰጠው የብሔራዊ ሰብዓዊ መብቶች ተቋም በምርጫው ዕለት በምርጫ ጣቢያዎች ጭምር በመገኘት የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ክትትል እንዳያደርግ መከልከል የምርጫው ሒደትና ውጤቱ ተዓማኒነትና ተቀባይነት ላይ ጭምር ጥያቄ የሚያስነሳ ነው፤›› ሲሉ ለማሳሰብ ሞክረዋል።

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ አቋሙን አልቀየረም። የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ቦርዱ ለኮሚሽኑ የይለፍ ካርድ የሚሰጥበት የሕግ አግባብ አለመኖሩን ተናግረዋል።

የምርጫ ቦርድን አቋም በተመለከተ፣ እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱትን ጨምሮ ሌሎች ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች የሰጡትን ተመሳሳይ ይዘት ያለው አስተያየት በማንሳት ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሰብዓዊ መብቶች ክትትልና ምርመራ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ምሥጋናው ሙሉጌታ፣ ኮሚሽኑ የይለፍ ካርድ የጠየቀው ምርጫውን ለመታዘብ ሳይሆን የምርጫ ወቅት የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃን ለመከታተል እንደሆነ ይገልጻሉ።

‹‹እኛ የምርጫ ታዛቢ ነን አላልንም። የይለፍ ካርድ የጠየቅነው ምርጫ ለመታዘብ አይደለም። የጠየቅነው የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ለማድረግ ነው። እንደሚታወቀው በምርጫ ሒደት ወቅት አንድ የምርጫ ጣቢያ ኃላፊ በዛ ሒደት ውስጥ አለቃ ነው። የይለፍ ካርድ የጠየቅነው በየምርጫ ጣቢያው ንትርክ ውስጥ እንዳንገባ ብለን ነው። እኛ እንደ አንድ ተቋም የምርጫውን ሒደት ለማደናቀፍ አንፈልግምጥያቄውን ያቀረብነውም በዚህ ምክንያት ነው፤›› ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ ሒደት እየተከናወነበት ባለበት ወቅት ተስተውለዋል ያላቸውን ጣልቃ ገብነቶች በተለይም የዝቅተኛ የመንግሥት ዕርከን ሠራተኞች (ወረዳ፣ ቀበሌወዘተ) ተፈጽመዋል ያላቸውን በመለየት ግንቦት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋዊ የሆነ ማሳሰቢያ ሰጥቶ ነበር።

ቦርዱ በግንባር ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ በነጻ የስልክ ጥሪ መስመር የሚመጡ ጥቆማዎችን በመከታተል፣ የክትትል ቡድኑን በማሰማራት የምዝገባ ሒደቱ ላይ ባደረገው ግምገማ፣ዝቅተኛ የመንግሥት ዕርከን ላይ የሚገኙራተኞች ምርጫ ጣቢያ ላይ ያለምንም ከቦርዱ የሚሰጥ የፓርቲ ወኪልነትን የሚያሳይ መታወቂያ ይገኙ እንደነበር፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን መረጃ መጠየቅና በአንዳንድ ሁኔታዎች የመራጮች ምዝገብን ለመጎብኘትና መረጃዎችን ለመውሰድ ጥረት በማድረግ ጣልቃ መግባታቸውን እንደተረዳ ገልጿል፡፡

ይህ ድርጊት ተገቢ እንዳልሆነ የገለጸው ቦርዱ፣ ‹‹በተለይ ወደ ድምፅ መስጫ ቀን እየተጠጋን በመጣን ጊዜ የምርጫ ሒደቱን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያውከው ከመሆኑም በላይ በምርጫ ሕጉም ሆነ በወንጀለኛ መቅጫ የተቀመጠ ወንጀል ነው፤›› በማለት አሳስቧል።

በመሆኑም ማንኛውም የዝቅተኛው መንግሥትርከንራተኛ (የቀበሌ፣ የወረዳ አመራሮችና ሌሎች) ወይም ያልተፈቀደለት ማንኛውም ሌላ አካል ምርጫ ጣቢያ ውስጥም ሆነ 200 ሜትር ርቀት ዙሪያ ላይ እንዳይገኝ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

‹‹የዕውቅና ባጅ ከተሰጣቸው ፓርቲ ወኪሎች ውጪ ማንኛውም አካል የመራጮች ምዝገብና ተመዝጋቢዎች መረጃን አስመልክቶ ምርጫ ጣቢያም ሆነ የምርጫ ክልል አስፈጻሚዎችን እንዳይጠይቅ፣ እንዲሁም በምርጫ ጣቢያው ውስጥና 200 ሜትር ርቀት ዙሪያ እንዳይገኝ›› ሲል ማሳሰቢያ የሰጠው ቦርዱ ይህ ሆኖ ቢገኝ የምርጫ ወንጀል በመሆኑ ጥሰቱን የፈጸሙ ግለሰቦች በምርጫጉና በወንጀለኛ መቅጫ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ልዩ የደኅንነት ሁኔታ ተከስቶ ቢሆንም እንኳን የመንግሥት ኃላፊዎች ከቦርዱ የበላይ ኃላፊዎችውቅና ካላገኙ በስተቀር ወደ ምርጫ ጣቢያ ወይም ከተከለለው 200 ሜትር ርቀትን ማለፍ እንደማይችሉ ገልጿል።

በማከልም ለቦርዱ የምርጫ አስፈጻሚዎች መመርያ የሰጠ ሲሆን፣ ‹‹ማንኛውም የዝቅተኛ የመንግሥት ዕርከንራተኞች ወይም ሌሎች ያልተፈቀደላቸው አካላት ከምርጫ ጣቢያ ውስጥም ሆነ 200 ሜትር ርቀት ውስጥ እንዳይገኙ እንዲያደርጉ፣ ከቦርዱ ሠራተኞችናላፊዎች ውጪ ምንም ዓይነት ትዕዛዝም ሆነ አቅጣጫ በፍጹም እንዳይቀበሉ በዚሁ አጋጣሚ እናሳስባለን፤›› ብሏል።

የሰብዓዊ መብት ክትትልና ምርመራ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ምሥጋናውበምርጫ ጣቢያዎች መገኘት የሚችሉት በቦርዱ የይለፍ ካርድ (ባጅ) የተሰጣቸው ብቻ ናቸው የሚል መመርያ ለምርጫ አስፈጻሚዎች የሚሰጥ በመሆኑና የኮሚሽኑ የክትትል ባለሙያዎች በዚህ ምክንያት ከምርጫ አስፈጻሚዎች ጋር ንትርክ ውስጥ እንዳይገቡና በዚህም ምክንያት በምርጫው ሒደት ላይ እክል እንዳይፈጠር በሚልሳቤ ኮሚሽኑ የይለፍ ካርድ መጠየቁን ያስረዳሉ።

ኮሚሽኑ እስካሁን የይለፍ ካርዱን እንዳላገኘ የሚገልጹት አቶ ምሥጋናው ይህ ግን የኮሚሽኑ ባለሙያዎች የምርጫ ወቅት የሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅ ላይ ክትትል እንዳያደርጉ የሚያግደው እንዳልሆነ አስረድተዋል።

ኮሚሽኑ በቅድመ ምርጫ ወቅት ከቦርዱ ጋር በመተባበር እየሠራ መቆየቱን ያስታወሱት አቶ ምሥጋናው፣ በዚህ ሒደትም ውስጥ በሁለቱ ተቋማት መካከል ጥሩ መግባባት እንደነበር ገልጸው፣ አሁን ላይ ቦርዱ የኮሚሽኑን ጥያቄ ለምን እንደከለከለ ለመረዳት እንደቸገራቸው ተናግረዋል።

‹‹ኮሚሽኑ ምርጫ ለመታዘብ አልጠየቀምምርጫ ታዛቢም አይደለንም›› የሚሉት አቶ ምሥጋናው፣ ‹‹ምርጫ ቦርድ የእኔን ሕግ ብቻ ነው የማከብረው ማለትም አይችልም፤›› ብለዋል። 

ኮሚሽኑ በተቋቋመበት በቀድሞው አዋጅ መሠረት የሲዳማ የክልልነት ሕዝበ ውሳኔ ላይ የሰብዓዊ መብት ክትትል ኮሚሽኑ ማድረጉን የገለጹት አቶ ምሥጋናውአሁን በተሻሻለው የማቋቋሚያ አዋጅ በምርጫ ወቅት የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ክትትል የማድረግ ሥልጣን በተሰጠው ወቅት፣ ከምርጫ ቦርድ ጋር የተሻለ ግንኙት ሊፈጠር ሲገባ የተፈጠረው ነገር መከሰቱ ግር እንዳላቸው ገልጸዋል።

የይለፍ ካርዱን ኮሚሽኑ ባያገኝም በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የክትትል ባለሙያዎቹን እንደሚያሰማራ ተናግረዋል።

በዚህም መሠረት ከዘጠና እስከ መቶ የሚደርሱ የኮሚሽኑ የክትትል ባለሙያዎች 34 አካባቢዎች እንደሚሰማሩና በቆይታቸውም ከድምፅ መስጫው ቀን በፊት ያሉ ሁኔታዎችን፣ እንዲሁም በድምፅ መስጫው ቀንና በኋላ ባሉት ቀናቶችም በመቆየት ክትትል እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል።

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -